“የእሪታ ቀን” እውቅና ባይሰጠውም… (ደብዳቤውን ይዘናል) አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂድ ገለጸ

(EMF) በአንድነት ፓርቲ አማካኝነት – መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ሊደረግ የነበረው የ እሪታ ቀን በአዲስ አበባ መስተዳድር ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ ሰልፈኞቹ የሚሄዱበት ስፍራ የተከለከለ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉን ጥያቄ እውቅና አንሰጠውም ብሏል። ቀበና መድሃኔአለም ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስቶ በፒያሳ እና ቸርችል ጎዳና አድርጎ፤ ጥቁር አንበሳ ድላችን ሃውልት ጋር ይጠናቀቅ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት… መንገዱ የባቡር መስመር የሚዘረጋበት፣ ትራፊክ የሚበዛበት እና ሆስፒታል የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ ነው፤ ለሰልፉ እውቅና የነፈገው። ይህ በ’ንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰልፉን የሚያካሂድ መሆኑን ገልጿል። አሁን ዘግይቶ ከፓርቲው የደረሰን ዘገባም ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው።

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) “የእሪታ ቀን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተያዘለት ቀንና ቦታ እንደሚካሄድ ለመገናኛ ብዙሀን ካሳወቀበት ከትላንትናው እለት ማለትም መጋቢት 24/2006 ዓ.ም ጀምሮ ለከተማዋ ነዋሪዎች ስለሰልፉ ዓላማ የሚገልፅ በራሪ ወረቀት እያሰራጨ ይገኛል፡፡እስካሁን ድረስ ከ10.000 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶች ተሰራጭተዋል ፡፡ የነገውን ቅስቀሳ የአንድነት ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ እና የአዲስ አበባ ከተማ የአንድነት ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤት አባላት ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ደብዳቤ - ኤፕሪል 3 2014

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 3, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.