የኢትዮ-ኤርትራን ችግር ለመፍታት የሚረዱ ነጥቦች (አማኑኤል ዠሰላም)

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ አስመራ ድረስ ሄደዉ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ ለአልጃዚራ ገልጸዋል። «በአልጀርሱ ስምምነት ተቋቁሞ የነበረው የድንበር ኮሚሽን የወሰነዉን ዉሳኔ፣ ኢትዮጵያ አክብራ፣ የባድመን ከተማ ጨምሮ የኤርትራ ናቸው ከተባሉት መሬቶች ሁሉ ለቃ እስካልወጣች ድረስ፣ አልነጋገርም» ሲል የነበረዉ የኤርትራ መንግስት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም አስተያየት የሰጠው ኦፌሳላዊ ምላሽ ባይኖርም፣ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ከዚህ በፊት የነበራቸውን አቋም በማለዘብ ከኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ችግር ለመፍታት ፍቃደኛ እንደሆኑም የሚያሳዩ ዘገባዎችን እያነበብን ነዉ።

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች አብረዉ የኖሩ፣ የተዋለዱ፣ በባህል በቋንቋ በሃይማኖት የተዛመዱ ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው። ስር የሰደደ የታሪክ ዝምድና ያላቸው፣ አንድ ወቅትም የአንድ አገር ሕዝብ የነበሩ እንደመሆናቸው፣ በመካከላቸው ያላቸዉን ችግሮች እስከአሁን መፍታት አለመቻላቸው የሚያሳዝን ነዉ። በእዉኑ ያሉን ልዩነቶች ይሄን ያህል የከረሩ ናቸዉን ? አንዱ አሸናፊ ሌላዉ ተሸናፊ ሳይሆን፣ ሁሉም አሸናፊ የሚሆነበትን መፍትሄ ማግኘት ያቅተናልን ? እስከመቼስ ኤርትራንና ኢትዮጵያን የሚያካልለዉ ድንበር፣ የልማትና የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚታዩበት አካባቢ መሆኑ ቀርቶ፣ የፈንጂና የታንክ መናኸሪያ ይሆናል ?

Read story in PDF .

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 19, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.