የኢትዮጵያ Dreamliner አውሮፕላን በቆመበት ጨሰ

EMF –
Ethiopian Airlines Boeing 787

Ethiopian Airlines Boeing 787

ዛሬ የለንደን አውሮፕላን ማረፊያ ተጨናንቆ ነበር የዋለ። ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው Dreamliner አውሮፕላን ቦይንግ 787 Dreamliner አውሮፕላን በቆመበት ሲጨስ በመታየቱ ነው። በዚያ ምክንያት ወደ ብሪትሽ አየር መንገድ ይመጡ የነበሩ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ተደርጎ ነበር። በዚህም ምክንያት የሌሎች አውሮፕላኖች መነሻ እና መድረሻ ሰዓት የተስተጓጎለ መሆኑ ታውቋል። በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም ሰው አላሳፈረም። ሁኔታው ግን “በፓይለቱ ምክንያት ነው” የሚል ምክንያት እንዳይሰጡ እንጂ፤ ቦይንግ አምራች የሆነውን የአሜሪካ ኩባንያ ኪሳራ ውስጥ የሚጨምረው ይሆናል። በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ 50 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ሲኖሩ፤ በባትሪው ላይ እንከን በመገኘቱ ሁሉም አውሮፕላኖች ለስድስት ወራት ስራቸውን አቁመው እንደነበር ይታወሳል። አሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የተፈጠረው ችግር ዋናውን አምራች ኩባንያ አጣብቂኝ ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ይገመታል።
Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 12, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የኢትዮጵያ Dreamliner አውሮፕላን በቆመበት ጨሰ

  1. jV7gxb

    August 7, 2013 at 10:37 AM

    353494 983870bathroom towels need to be maintained with a excellent fabric conditioner so that they will last longer:: 548584