የኢትዮጵያ እና የቡርኪና ፋሶ ቀጥታ ስርጭት (ኢትዮጵያ 0 – ቡርኪናፋሶ 4)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጨዋታው ተጅምሯል። በተጀመረ በአምስተኛው ደቂቃ ሳላዲን ሰይድ ለሽመልስ በቀለ በቄንጥ ያቀበለውን ኳስ ሞከረው። የኢትዮጵያውያውን የመጀመሪያ የጎል ሙከራ… ያለቀለት ኳስ አንግል ገጭቶ ተመለሰ… አወጡት። ገና ከመጀመሩ ጨዋታው መድመቅ ጀመረ። ኢትዮጵያ ዜሮ ቡኪናፋሶ ዜሮ። የኢትዮጵያ ጥቁር አንበሶች የሚገርም ጨዋታ ነው የሚጫወቱት። እንዳለፈው ጊዜ ቢጫ ማልያ አድርገዋል። አዳነ መጫወት አልቻለም። ሊቀየር ነው። በንዴት መሬቱን እየመታ ነው። መጫወት ስላልቻለ፤ አሰልጣኙ ሊቀይረው ነው። አዳነ… ሜዳውን ለቅቆ ሲወጣ እያለቀሰ ነበር። በሃይሉ አሰፋ፤ በአዳነ ተቀይሮ ገብቷል። 15ኛው ደቂቃ ላይ ነን። ጨዋታው ቀጥሏል።

Adane left the field

Adane left the field

በጠዋቱ ጨዋታ ናይጄሪያ እና ዛምቢያ አንድ እኩል ስለወጡ፤ በዚህ ጨዋታ ኢትዮጵያ ማሸነፍ ይጠበቅባታል።እራሳቸው ጎል ውስጥ የሚጫወቱት ጨዋታ የሚያሳቅቅ ነው። ጎል ስር ሲቀባበሉ፤ የቡርኪና ፋሶ ተጫዋች ነጥቆ አቀበለ። ሆኖም ኦፍ ሳይት ተባለ። ኦፍ ሳይት ባይሆን ድንቅ ጎል ትሆን የነበረች ኳስ ናት። ኢትዮጵያውያኑ ጎላቸው ስር መቀባበሉን ማቆም ሳይኖርባቸው አይቀርም። አሁን 30ኛው ደቂቃ ላይ ናቸው ተመጣጣጣኝ ጨዋታ እየታየ ነው። የአዳነ መውጣት የኢትዮጵያን ቡድን ቀዝቀዝ ያደረገው ይመስላል። ጨዋታው በፉክክር እንደቀጠለ ነው።
35ኛው ደቂቃ ላይ ቡርኪናፋሶ ተቀባብለው ኢትዮጵያ ላይ አገቡ። ቡርኪናፋሶ 1 – ኢትዮጵያ 0።
ቀደም ሲል እናዳልነው ኢትዮጵያውያኑ ወደፊት ከመግፋት ይልቅ እራሳቸው ሜዳ ላይ የሚጫወቱት ነገር የግብ ዋጋ አስከፍሏል። አሁን 44ኛው ደቂቃ ላይ አስራት መገርሳ በ በያሬድ ተቀይሮ ገብቷል። የመጀመሪያው ጨዋታ ሊያልው ጥቂት ደቂቃ ቀርቷል። አይናለም ጥሩ የመከላከል ስራ እየሰራ ነው። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ነው። 1 – 0 እንደሆኑ እረፍት የሚወጡ ይመስላል። ከ እረፍት በኋላ ጥቁር አንበሶቹን በተሻለ ሁኔታ እንጠብቃለን።

ከ15 ደቂቃ እንደገና ተመልሰዋል። ኢትዮጵያውያን እንደገና ለማጥቃት እየሞከሩ ነው። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የተጨነቀ ይመስላል። ኢትዮጵያውያን በረዥሙ መጫወት ጀምረዋል። አሁን ኢትዮጵያ ጎል አካባቢ ቅጣት ምት አግኝተዋል። ጥሩ ሙከራ ነበር። በረኛው ግን ይዟታል። አሁን ጨዋታው ከተጀመረ 5 ደቂቃ ሆኗል። ጨዋታው እንደቀጠለ ነው። ሽመልስ በቀለ በጌታነህ ከበደ ተቀይሮ ገብቷል። ጌታነህ ከበደ ሌላ አጥቂ ነው። ጥቁር አንበሶቹ እያጠቁ ናቸው።
የቡርኪና ፋሶ በረኛ ከመስመር ወጥቶ ኳስ ስለያዘ፤ ቀይ ተሰጥቶታል። አሁን ቡርኪናፋሶ በአስር ተጫዋች ጨዋታውን ይቀጥላል። ለኢትዮጵያ ጥሩ አጋጣሚ ነው። አሁን ከቅርብ ርቀት የኢትዮጵያ ቡድን ቅጣት ምቱን ሊመታ ነው። ሆኖም የቡርኪና ፋሶ በረኛ አድኖታል። 15ኛው ደቂቃ ላይ ነው – ጨዋታው ቀጥሏል። ቡርኪና ፋሶ አንድ ለዜሮ እየመራ ነው።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሃያ ደቂቃ ይቀራቸዋል። ቡርኪና ፋሶ አስገራሚ ጎል አስቆጠረ። ሁለት ለዜሮ እየተመራን ነው። አስር ቁጥሩ በግራ እግሩ የሚገርም ሹት ነው ያደረገው።
ቡርኪናፋሶ በሚገርም ቅብብል 3ኛ ጎል አስገቡ። 6 ቁጥሩ 3ኛውን ጎል አገባ። ኢትዮጵያ 0 – ቡርኪና ፋሶ 3። አሁን ከምድቡ ቡርኪና ፋሶ እየመራ ይመስላል። በዚሁ ከቀጠሉ የኢትዮጵያ ቡድን ከምድቡ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ቡርኪና ፋሶ በአስር ተጫዋች እያጠቁ ናቸው። ሁለቱን ጎል ያስቆጠሩት በአስር እየተጫወቱ ነው።

ethio fan crying
አዲስ ተቀይሮ የገባው 11 ቁጥሩ 4ኛ ጎል ኢትዮጵያ ላይ አስቆጠረ። ውጤት 4 – 0።
ቡርኪና ፋሶ በአስር ተጫዋች አሸንፏል። ሁሉም ንጹህ ጎሎች ነበሩ። ምንም ምክንያት ማቅረብ አያስፈልግም። ተሸንፈናል። ዘጠና ደቂቃ አልቆ፤ ጨዋታው ተጠናቋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ኳስ ቡድን፤ አሁንም የማለፍ እድል አለው።

ማክሰኞ የሚደረገው የቡድን ሶስት ጨዋታ፤ የኢትዮጵያን እድል ይወስነዋል። ማክሰኞ ጠዋት ዛምቢያ በቡርኪና ፋሶ ከተሸነፈች፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ናይጄሪያን ካሸነፈች ሶስት ነጥብ በማግኘት ወደሚቀጥለው እሩብ ፍጻሜ የማለፍ እድል አላት። ማክሰኞ ዛምቢያ ቡርኪና ፋሶን ካሸነፈች ግን፤ ኢትዮጵያ ናይጄሪያን በሰፊ የግብ ልዩነት ካላሸነፈች በስተቀር እድሏ የተሟጠጠ ይሆናል። በመሆኑም የናይጄሪያ እና የዛምቢያ መሸነፍ፤ እነሱን በ2 ነጥብ ሲያስቀራቸው፤ ኢትዮጵያ ግን 3 ነጥብ በማግኘት ጥቁር አንበሶቹ ያልፋሉ ማለት ነው። ስለዚህ ተስፋ የሚያስቆርጥ እና አበቃላቸው የሚያሰኝ ስሜት ሊኖር አይገባም። ቡርኪና ፋሶ እና ዛምቢያ እኩል ቢወጡና ኢትዮጵያ ነይጄሪያን 1-0 ብታሸንፍም ወደሚቀጥለው ዙር ታልፋለች።

በነገርዎ ላይ የኢትዮጵያ ቡድን ወደ እሩብ ፍጻሜ አልፎ ስምንቱን ከተቀላቀለ 10 ሚሊዮን ብር፤ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፎ አራቱ ውስጥ ከገባ 20 ሚሊዮን፤ ዋንጫ ካገኘ ደግሞ አርባ ሚሊዮን ዶላር… እንደታቀደው በአጠቃላይ አልፎ ዋንጫ ካገኘ ከሰባ ሚሊዮን ብር በላይ የስፖርት ፌዴሬሽኑ ለመሸለም ቃል ገብቶላቸዋል።

ማክሰኞ ከናይጄሪያ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ “መልካም እድል” ተመኝቶ ከማለፍ ውጪ ሌላ የምንለው የለንም። ደህና ሁኑልን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 25, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.