የኢትዮጵያ እና ናይጄርያ ጨዋታ ቀጥታ ስርጭት ናይጄርያ 2 – ኢትዮጵያ 0

ኢ.ኤም.ኤፍ – (10፡00 AM)። ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርጉት የመጨረሻ ጨዋታ ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ቡድን ቢጫ ማልያውን አድርጎ ነው የገባው። አጀማመሩ ላይ የናይጄርያ ቡድን ማጥቃት እያደረገ ነው። እስካሁን የጎላ እንቅስቃሴ አይታይም። ሙሉውን የጨዋታ እንቅስቃሴ ለሚቀጥሉት 90 ደቂቃዎች በጽሁፍ እናስተላልፋለን። አብራችሁን ቆዩ።
10፡06 AM – የናጄርያ ቡድን ሊገባ የሚችል ኳስ ሞክሮ ሲሳይ ባንጫ አወጣበት። ናይጄሪያዎች አሁንም እያጠቁ ነው። የኢትዮጵያ ቡድን እንደከዚህ በፊቱ ኳስ ይዞ ወደፊት ሲሄድ አይታይም። በአብዛኛው ናይጄሪያዎቹ በኢትዮጵያ ሜዳ ላይ እየተጫወቱ ናቸው። ጨዋታው ከተጀመረ አስር ደቂቃ አልፏል። የኛ ቡድን ተጫዋቾች ተረጋግተው ለመጫወት ሲሞክሩ ይታያል። የኢትዮጵያ ቡድን አሰላለፍ 4-4-2 ነው። አሁን በትክክል እንደምናየው ናይጄርያ እያጠቃን ነው። አልፎ አልፎ ወደ ሳላዲን ኳስ እንዲደርሰው ቢደረግም፤ የናይጄርያ ተከላካዮች ሳላዲንን አላጫወቱትም። 10፡15 ላይ ናይጄርያ ሌላ አደገኛ ሙከራ አድርጎ ነበር። ሆኖም ሲሳይ ባንጫ በግሩም ሁኔታ በእግሩ መትቶ አውጥቷታል።

አይናለም ኃይሉ በሆዱ ኳስ አቁሞ እጁ ነካችበት። ፍጹም ቅጣት ምት የሚያሰጥ አልነበረም። ጋቦናዊው ዳኛ ለናይጄርያ የመጀመሪያውን ፍጹም ቅጣት ምት ሰጡ። የኬንያው የመስመር ዳኛ ፍጹም ቅጣት መሰጠቱን የደገፉ ይመስላል። በሌላ በኩል ኤርትራዊው የመስመር ዳኛ በዚህ ጉዳይ ምንም ያሉት ነገር የለም። ቪክቶር ሞሰስ (የሊቨር ፑሉ ተጫዋች) ኳሱን ሊመታ ነው። መታ። አገባው። ተገቢ ባልሆነ ፍጹም ቅጣት ምት ናይጄርያ የመጀመሪያውን ግብ አግብቶበታል። እንደከዚህ ቀደሙ ሌላ የፍጹም ቅጣት ምት አግኝተው እየመሩ ናቸው። 10፡24 ላይ ናይጄርያ ሌላ ሙከራ ሊያደርጉ ሲሉ፤ አስራት መገርሳ አክሽፎበታል።

ናይጄርያ ያገኘው አንድ ጎል የኢትዮጵያን ቡድን የረበሸው ይመስላል።

አሁን ጨዋታው ከተጀመረ 30 ደቂቃ ሆኗል። 30ኛው ደቂቃ ላይ ናይጄርያዎች አጥቅተው ሌላ ሙከራ አደረጉ፤ በጭንቅላት ተመትቶ የኢትዮጵያ ቡድን ላይ ሞክሯል። አልፎ አልፎ የኢትዮጵያ ቡድን እየተቀባበሉ ወደፊት ለማለፍ እየሞከሩ ነው። ሆኖም ይሄ ነው የሚባል ሙከራ ለማድረግ አልቻሉም። 33ኛው ደቂቃ ላይ የማዕዘን ምት አድርጓል። ሆኖም አልተሳካም። አሁን የናይጄርያ ቡድን ብዙም ወደፊት እየሄደ ሲጫወት አይታይም። መሃል ላይ መጫወት አብዝተዋል። መከላከል ላይም ያተኮሩ ይመስላል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃ ቀርቷል። ሁኔታው በዚህ አይነት ከተፈጸመ፤ የናይጄርያው ቡድ በቀጥታ ለብራዚሉ የአለም ዋንጫ አለፈ ማለት ነው።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃ ሲቀረው… የናይጄርያ ቡድን የሚገርም ሹት አደረገ። መግባት የሚችል ኳስ ነበር። ሆኖም የኢትዮጵያ በረኛ ሲሳይ ባንጫ በሚገርም ሁኔታ አዳናት። ያለቀለት ግብ በማዳኑ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል። ግማሽ ጨዋታው 1 – 0 ተጠናቋል።
ከ እረፍት ተመልሰው ጨዋታው ከተጀመረ 20 ደቂቃዎች አልፈዋል። በኢትዮጵያ ቡድን በኩል ደህና እንቅስቃሴ ይታያል።63ኛው ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያ የፍጹም ቅጣት ልትሆን የምትችል ኳስ ብታገኝም፤ ዳኛው አላጸደቃትም። ጨዋታው በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 25 ደቂቃዎች ብቻ ቀርቷል። በሚቀጥሉት ቀናት የኢትዮጵያ ቡድን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ማስቆጠር አለበት። ይህ ግን አጠራጣሪ ይመስላል። ሳላዲን እንደገና ፔናልቲ ውስጥ ተጠልፎ ቢወድቅም፤ ፍጹም ቅጣት ምት ሳይሰጥ ቀርቷል።
አሁን ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃዎች ሲቀሩ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በጥሩ ሁኔታ መጫወት ጀምረዋል። ከመጀመሪያው ጀምሮ በዚህ አይነት ቢጫወቱ የማሸነፍ እድላቸው ከፍ ሊል እንደሚችል ይገመታል። አሁን ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ ሲቀር የሚያደርጉት ጥሩ ጨዋታ፤ “ከመጀመሪያው ቢደረግ ኖሮ…” ብለን እንድንቆጭ እያደረጉን ነው። አዲስ ህንጻ ተቀይሮ ገብቷል። የናይጄርያው በረኛ ብዙም ስራ የበዛበት አይመስልም። ጨዋታው ሊጠናቀቅ 7 ደቂቃ ሲቀረው የናይጄርያ ቡድን ሁለተኛውን ግብ፤ በቅጣት ምት አስቆጥሯል። የናይጄርያ ቡድን ለብራዚሉ የአለም ዋንጫ ያለፈ ይመስላል። ናይጄርያ 2 – ኢትዮጵያ ዜሮ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ናይጄርያዎቹ በጨዋታ በልጠውናል። የሆነውን ነገር በጸጋ መቀበል ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡድን እዚህ ደረጃ ድረስ መምጣቱ በራሱ ያኮራል። በዚህ እየተጽናኑ ቀጣዩን የቻን አፍሪካ ውጤት መጠባበቅ ነው። ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረገው የቻን አፍሪካ ጨዋታ ማጣሪያውን ማለፏ ይታወሳል።

አሁን ዳኛው ከሚጨምሩት የባከነ ሰአት ውጭ ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም። ዘጠና ደቂቃው በናይጄርያ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ናይጄርያ ለአምስተኛ ጊዜ ለአለም ዋንጫ አልፏል። ተጫዋቾቹን ጨምሮ 250 ሰዎችን በቻርተር አውሮፕላን ይዞ የሄደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ያዘኑ እና የተከዙ ተጫዋች እና ደጋፊዎችን ይዞ ይመለሳል። እኛ ግን እንላለን – “አይዟችሁ፤ ነገም ሌላ ቀን ነው!” የጽሁፍ ቀጥታ ስርጭታችንም እዚህ ላይ ተጠናቋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የኢትዮጵያ እና ናይጄርያ ጨዋታ ቀጥታ ስርጭት ናይጄርያ 2 – ኢትዮጵያ 0

 1. Ashenafi

  November 16, 2013 at 1:25 PM

  To the editor

  The Nigerian team did not play more than our team,it is not true. our players ridiculed the Nigerian team. The Ethiopian team played a wonderful game , Our team has played like Barcelona. The Ethiopian team was awesome!!!
  For that matter, the Arbiter was in favor of them.He gave them penalty with out any foul from the Ethiopian tam.

 2. Girma Moges

  November 17, 2013 at 6:53 PM

  ጥሩ ሪፖርት ነው:: የኢትዮጵያ ዳግማዊ መነሳት አድርጋለች በሙያው:: ሪፖርት አድራጊውም በርታ! ሑላችንም እንበርታ!