የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለአንድነት ፓርቲ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ሰጠ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አንድነት ፓርቲ ለላከለት ማስጠንቀቂያ ምላሽ መስጠቱን የአንድነት ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

አቶ ስዩም መንገሻ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት በቅርቡ አንድነትን በ“አሸባሪነት” የሚፈርጅ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡን ተከትሎ አንድነት ፓርቲ ድርጅቱ ምላሽ እንዲሰጥ ጥር 1 ቀን 2006 ዓ.ም ደብዳቤ ጽፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለደብዳቤው ምላሽ ባለመስጠቱም አንድነት በድጋሚ የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በጻፈው ደብዳቤ በ15 ቀን ውስጥ ምላሽ ካላገኘ ወደ ክስ እንደሚሄድ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

ማስጠንቀቂያው የደረሰው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም የካቲት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ለአንድነት ማስጠንቀቂያ ሁለት ገፅ ያለው ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምላሽ ላይ ከተወያየ በኋላ ምላሹ ትክክለኛ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ በመድረሱ ጉዳዩን ለፓርቲው የህግ ክፍል እንዲመራ መወሰኑን የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ ስዩም መንገሻ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት “አኬልዳማ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ዘጋቢ ፊልም አንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ በፓርቲው መከሰሱ አይዘነጋም፡፡

UDJ's letter to ETV

UDJ’s letter to ETV

ETV letter to UDJ - Page 1

ETV letter to UDJ – Page 1


ETV's letter (2nd page) to UDJ

ETV’s letter (2nd page) to UDJ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 25, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.