የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሩዋንዳ አቻውን በፍጹም ቅጣት ምት ረታ

EMF – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ለሚደረገው የአፍሪካ ሻምፒዮና አልፏል። ትላንታ ኪጋሊ ሩዋንዳ ላይ በተደረገው የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ጨዋታ፤ ከ እረፍት በፊት ዜሮ ለዜሮ ቆይተው፤ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሩዋንዳ አንድ ግብ አስቆጥሯል። ሆኖም ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ውስጥ ተደርጎ በነበረው ጨዋታ ኢትዮጵያ 1 – 0 አሸንፋ ስለነበር፤ ጨዋታው እንደ እኩል ተቆጥሮ በፍጹም ቅጣት ምት እንዲለዩ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ቡድን 6 – 5 አሸንፏል። በእለቱ በረኛ የነበረው ሲሳይ ባንጫ ሁለቱን ጎል በማዳኑ ለኢትዮጵያ ቡድን ባለውለታ ሆኗል። Read more on PDF

እርማት፡ በ PDF በተጻፈው ዜናችን ላይ ቀጣዩ ጨዋታ በናይሮቢ ኬንያ እንደሚደረግ ገልጸን ነበር። ሆኖም ሴንትራል አፍሪካ ጨዋታው በኮንጎ ብራዛቪል እንዲደረግ በጠየቀችው መሰረት፤ የሴፕቴምበሩ ጨዋታ በኮንጎ እንደሚሆን ፊፋ ይፋ አድርጓል።
sisay bancha

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 28, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.