የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ገንዘቡን እንዲመልስ ተጠየቀ

28ኛውን የስፖርት ዝግጅት በአትላንታ ላይ ለማድረግ ዝግጅቱን ያጠናቀቀው፤ በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን በሚድሮክ በኩል የተሰጠው ገንዘብ እንዲመለስለት መጠየቁ ታወቀ። ይህንኑ እውነታ በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ያረጋገጡልን የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ሃላፊ፤ “አዎ እስካሁን ምንም የደረሰን ነገር አልነበረም። አሁን ግን በህጋዊ ጠበቃቸው በኩል ገንዘባቸው እንዲመለስ ጠይቀዋል።” ብለዋል።

Save it or blaze it!

እንደፌዴሬሽኑ ምንጮቻችን ከሆነ፤ ገንዘቡ እስከ ጁን 13፣ 2011 ድረስ እንዲመለስ በጠበቃቸው አማካኝነት ተጠይቆ ነበር። ይህም ቀነ ገደብ በትላንቱ እለት ያለፈ በመሆኑ ከዚህ ቀጥሎ በህጋዊ መንገድ ጉዳዩ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው፤ ባለፈው ሳምንት አቶ አብነት አትላንታ ላይ ቆይታ አድርገው የጆርጂያ ዶም ስራ አስኪያጅን አነጋግረውና ጉዳዩን የሚከታተል ጠበቃ ቀጥረው መሄዳቸውን አረጋግጠውልናል።

የዚህ ሁሉ መነሻም አንድ የፌዴሬሽኑ የቦርድ አባል፤ የተለገሰውን ብር “የደም ገንዘብ ነው” በማለቱ መሆኑ ታውቋል። በሌላ በኩል በግል ግለሰቦች የሚናገሩት ወይም የሚጽፉት መልዕክት በቀጥታ ፌዴሬሽኑን እንደማይወክል የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ሃላፊ ለድረ ገጻችን ገልጸዋል። ሆኖም ይህን አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ እንደ ድርጅት አቋሙ አለመሆኑን ቢገልጽም በሚድሮክ ስራ አስኪያጅ በኩል የፌዴሬሽኑን ማስተባበያ አልተቀበሉትም።

ይህ ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ካልተመለሰ በነአቶ አብነት በኩል ያሉ ወገኖች ጨዋታው በጆርጂያ ዶም እንዳይካሄድ የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው። ይህ ደግሞ ለአትላንታ አዘጋጆች፤ ወደ አትላንታ ለሚመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ማሳሳዘኑ አይቀርም።

አሁን አሜሪካ ላለችበት የኢኮኖሚ ድቀት፤ በመጪው ጁላይ በአትላንታ የሚደረገው የስፖርት ፌስቲቫል፤ ከአትላንታ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች ጀምሮ የአትላንታንም ኢኮኖሚ በወሰነ ደረጃ መጥቀሙ የማይቀር ነው። ሆኖም አሁን እንደተባለው ገንዘቡን በማስመለስ ዝግጅቱ እንዳይደረግ ከሆነ፤ የፌዴሬሽኑን ህልውና ብቻ ሳይሆን በአትላንታ ብዙ ገንዘብ እያወጡ የንግድ ቤቶቻቸውን በማደስ ኢንቨስት የሚያደርጉትን የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያሳዝን መሆኑ ይታመናል።

ይህን አስመልክቶ በፌዴሬሽኑ በኩል የተሰጠ መግለጫ እስካሁን የለም። በቅርቡ ግን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፌዴሬሽኑ ምላሽ እንደሚሰጥ እየተጠበቀ ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 14, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.