የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ዳኛ ብርቱካን የአመቱ የክብር እንግዳ እንድትሆን በሙሉ ድምፅ ወሰነ

EMF – 28ኛው የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ እንደሚደረግ ይታወቃል። በዚህ ዝግጅት ላይም የክብር እንግዳ አመራረጥን አስመለክቶ ረዥም ግዜ የወሰደ ውዝግብ ተነስቶ ነበር። በተለይም ኦክቶበር 28 ቀን 2010 አትላንታ ላይ በተደረገው የቦርዱ ስብሰባ ላይ ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ከተመረጡ በኋላ፤በአንድ ወገን ስራ አስፈጻሚው የተሰጠውን ምርጫ ሽሮታል የሚል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ስራ አስፈጻሚው “ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎችን መጋበዝ ከጀመርን፤ ወደፊትም ተመሳሳይ ጥያቄ እየተነሳ ይከፋፍለናል።” በሚል ስጋት የተሰጠውን ውሳኔ አንስቶት ነበር። Birtukan

ሆኖም በህጉ መሰረት አብላጫው የቦርድ አባል ተሰብስቦ ጉዳዩን በድጋሚ ተመልክቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ ለ ኤፕሪል 16 2011 ቀጠሮ ተያዘ። የቦርድ አባላትና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ወደ አትላንታ በመምጣታቸው፤ ልዩ ልዩ ስብሰባዎች አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነበር የተደረጉት። ቅዳሜ ከሰአት ሊደረግ የነበረውም ስብሰባ፤ ከጠዋት ጀምሮ ምሽት ድረስ ነው የዘለቀው። የወቅቱ አንደኛው አጀንዳ የዳኛ ብርቱካን ጉዳይ ቢሆንም፤ በፌዴሬሽኑ የውስጥ ጉዳዮችም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም የዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ ጉዳይ ለድምፅ ቀረበ። የፌዴሬሽኑ የቦርድ አባላት እና ስራ አስፈጻሚዎች በሙሉ ድምፅ የዳኛ ብርቱካንን የ2011 ዓ.ም. የክብር እንግድነት ተቀበሉት። በስብሰባውም መጨረሻም ለፌዴሬሽኑ አንድነትና ለህዝቡ ፍላጎት ሲባል፤ በስራ ሂደት የተቀያየሙ አባላት ይቅር ተባብለው እጅ ለ እጅ ተጨባብጠው የስብሰባው ፍጻሜ ሆነ። እስከ እኩለ ለሊት ድረስ የአትላንታ ነዋሪ እርስ በርሱ የ እንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በእጅ ስልክ ሲለዋወጥ ቆየ። ዜናውን ዘግይተው የሰሙት የሌላ ክፍለ ግዛት ነዋሪዎችም በአትላንታ ለሚገኙ የቦርድ አባላትና ስራ አስፈጻሚዎች፤ በተመሳሳይ የ“እንኳን ደስ ያላችሁ” መልዕክት ሲጎርፍ ነበር ያመሸው። እሁድ አብዛኛው አባላት በተረጋጋ መንፈስ ስለቀጣዩ የ28ኛው በአል እየተነጋገሩ ነው። በተለይም ፌዴሬሽኑ ጠንክሮ እንዲሄድ የሚፈልገው የህዝብ ወገን የእፎይታ መንፈስ እየታየበት ይገኛል። ፌዴሬሽኑም ልዩነትን በመነጋገር ፈትቶ በአንድነት ለአንድ አላማ መቆሙ… ለሌላው መልካም ትምህርት የሚሰጥ፤ ወደፊትም በፌዴሬሽኑ ታሪክ ውስጥ የሚጠቀስ ይሆናል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 17, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.