የኢትዮጵያ ሙስሊምች የጁምዓ ተቃውሞ ቀጥሏል (VIDEO UPDATE)

365qen“365 ቀን ተጠይቆ ያልተመለሰ ጥያቄ!” በሚል መፈክር የተጀመረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ በዛሬው እለትም በደመቀ ሁኔታ ቀጥሎ መዋሉን ባልደረባችን ከአዲስ አበባ በስልክ ገልጾልናል።

የጁምዓ ተቃውሞ በዛሬው እለት ከተካሄደባቸው ስፍራዎች መካከል፡ የአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ፡ በወሎ ደሴና ወልዲያ፡ በጂማ፡ በናዝሬት እና በሃረር ከተሞች ያሉ መስጊዶቸ ይገኙበታል።

ሰላማዊ ተቃውሞ በተደረገባቸው በነዚህ ስፈራዎች ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል እና የክልል ፖሊሶች እንዲሁም ሲቪል ለባሸ የደህንነት አባላት እነደተገኙና በረካታ ሰዎችን ማሰራቸውን ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ገልጸዋል።

 

ጀርመን ሬዲዩ ሰለ ዛሬው የአንዋር የተቃውሞ ውሎ – ዶይቸ ቬለን ያድምጡ


በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ሙስሊም ምዕመናን የሚያሰሙት የተቃዉሞ ድምፅ ቀጥሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ ሀረር ዉስጥ መስጊድ በፖሊስና በሙስሊም ምዕመናን መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዉ ህይወት ማለፉና የተጎዳ መኖሩንም ወኪላችን ጠቅሶልናል። የፖሊስ ጥበቃ መጠናከሩም ተሰምቷል።

በሌላ በኩል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙን የይግባኝ አቤቱታ ዛሬ ተመልክቷል። ለዉሳኔም ቀጠሮ ሰጥቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎዉ ግቢ በተማሪዎች መካከል የተነሳዉ ግጭት ዛሬ የሰከነ ቢመስልም የመማር ማስተማሩ ሂደት አልተጀመረም። የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ አስራ አምስት ሰዎች በክትትል መያዛቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። በነዚህ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን በስልክ አነጋሬዋለሁ።

Al Jazeera report:

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.