የኢትዮጵያዊያን ሰልፍ ውጤት አመጣ! [አዳዲስ የኢ.ኤም.ኤፍ. ፎቶዎችን ይመልከቱ]

ጁላይ 25 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በዋሺንግተን ዲሲ ተደርጎ የነበረው፤ የዋሺንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ውጤት ማምጣቱ ተገለፀ። በመለስ ዜናዊ እና በበረከት ስምኦን አማካኝነት የአሜሪካ ድምፅ በልማት ላይ እንዲያተኩርና የተወሰኑ ግለሰቦችን በሬዲዮኑ ላይ እንዳያቀርቡ ጥያቄ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፤ የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪቃ ዴስክ ሃላፊዋ ይህንኑ ደግፈው ለጋዜጠኞች መመሪያ አሳልፈው እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ኢትዮጵያዊያን ይህንን በመቃወም እና የአሜሪካ ድምፅ እንደድሮው በነጻነት እንዲሰራ ለመጠየቅ ጁላይ 25 ቀን ሰላምዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ውጤት አግኝቷል።

የአሜሪካ ድምፅ ተጠባባቂ ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ሬዲሽ፤ ጋዜጠኞቹን በትላንቱ እለት ሰብስበው፤ “ከዚህ በፊት የሰራችሁትን ስራ እናደንቃለን። አሁንም ያለምንም ገደብ በነጻነት ስራችሁን ቀጥሉ።” በማለት ከእንግዲህ በኋላ የሳንሱር ማነቆ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ውስጥ እንደማይኖር ነው የገለጹት።

ኢ.ኤም.ኤፍ. በዚህ ጉዳይ ላይ የተላለፈው የድምፅ መልዕክት እንደደረሰው ለህትመት ያበቃዋል። ከዚህ በታች ያቀረብነው ፎቶ ኢትዮጵያዊያን ከቪ.ኦ.ኤ. ቅፅር ግቢ ውጭ ያደረጉት ሰልፍ ነው።

ታማኝ በየነ

“ተስፋ መቁረጥ አይገባንም። አለም በጥቂት ሰዎች ነው የተቀየረችው። ኢትዮጵያም በጥቂት ሰዎች ትቀየራለች። የምናደርገው ነገር ለውጥ እያመጣ ነው። ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ትግል በስፖንሰርሺፕ አይሆንም።” ታማኝ በየነ

 አበበ በለው

“12 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ፤ አባይን በልመና ገንዘብ መገደብ ይቻላል? እንዲህ አይነቱን ነገር በሚዲያ ላይ መነጋገር ከጀመርን ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ስለፈሩ ነው ቪ.ኦ.ኤን ። ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ እቃ በእቃ በቀያየር ነው የቀረው። ችግር ላይ ነው… ይህንን መነጋገር እንዳይቻል ነው ቪ.ኦ.ኤን ማፈን የፈለጉት።” አበበ በለው

“ከቦርዱ ጋር ወደፊት ለመነጋገር ቃል ተገብቶልናል” ነአምን ዘለቀ

“ከቦርዱ ጋር ወደፊት ለመነጋገር ቃል ተገብቶልናል” ነአምን ዘለቀ

ጥያቄያችንን የሚቀበል አካል እንፈልጋለን።

ጥያቄያችንን የሚቀበል አካል እንፈልጋለን።

ጥያቄያችሁን ለመቀበል መጥተናል።

ጥያቄያችሁን ለመቀበል መጥተናል።

ጥያቄያችን ለቦርዱ አባላት እንዲሰጥልን እንፈልጋለን።

ጥያቄያችን ለቦርዱ አባላት እንዲሰቀርብልን እንፈልጋለን።

ሰላም ነው!

ጥያቄያቸውን ተቀብለናል።

ፖሊስ እና የሴኩሪቲ ሃላፊው የኢትዮጵያዊያኑን ጥያቄ ተቀብለው ሲሄዱ።

ፖሊስ እና የሴኩሪቲ ሃላፊው የኢትዮጵያዊያኑ በወረቀት ያዘጋጁትን ጥያቄ ተቀብለው ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ገቡ።

ፖሊስ እና የሴኩሪቲ ሃላፊው የኢትዮጵያዊያኑ በወረቀት ያዘጋጁትን ጥያቄ ተቀብለው ወደ ዋናው መስሪያ ቤት ገቡ።

ኢትዮጵያዊያኑ ጥያቄያቸውን ማሰማት ቀጠሉ

ኢትዮጵያዊያኑ ጥያቄያቸውን ማሰማት ቀጠሉ (ፎቶ ኢ.ኤም.ኤፍ.)

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

"ከኒው ዮርክ ድረስ ከጓደኞቼ ጋር የመጣነው በቪ.ኦ.ኤ. ላይ የሚደረገውን አፈና ለመቃወም ነው" ተድላ አስፋው

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

”]July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC. [Photo EMF]
July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC. [Photo EMF]July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC. [Photo EMF]July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC. [Photo EMF]

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC. [Photo EMF]

ምላሽ እስከምናገኝ ጥያቄያችን ይቀጥላል።

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

July 25, 2011. Ethiopians rally in Washington DC.

በመጨረሻም

በመጨረሻም የቪ.ኦ.ኤ. ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሚስተር ሬዲሽ... የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኞች ያለ አንዳች ገደብ እና ሳንሱር ስራቸውን እንደድሮው እንዲቀጥሉ ትዕዛዝ ሰጡ። ይህም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ለነበሩ ኢትዮጵያዊያን ታላቅ ድል ነው። አሁንም ግን በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ነጻ ጋዜጠኞች በእስር ላይ መሆናቸውን ለአንድ አፍታም መዘንጋት የለብንም። ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ በማዞር የተጀመረው ጥረትና ትግል እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 26, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.