“የኢትዮጵያና የሕዝቧ ደመኛ…” ይሰቀል! በሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)

በ1900ዓ.ም በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግሥታት ስምምነት፣ “በልዩ የቆመ ፍርድ ቤት” የሚል ስያሜ የተቋቋመ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ሥራውን በ1914ዓ.ም ሲጀምር፣ የመጀመሪያው የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደ ሥላሴ ነበሩ፡፡ ከርሳቸውም ቀጥለው የተሾሙትም ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ ናቸው፡፡ የዚህ ፍርድ ቤት ዋነኛው ተግባር የውጭ ዜጎች እርስ-በራሳቸው ሲጋጩና/ወይም  የውጭ አገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን በተጋጩ ወይም በተካሰሱ ጊዜ ፍርድ መስጠት ነበር፡፡ በፍርዱም ላይ የከሳሹ/የተከሳሹ የውጭ አገር ዜጋን የሚወክል ቆንስል/ኤምባሲ ወኪል እንደአንድ ዳኛ ሆኖ ይቀመጥ ነበር፡፡ ይህ ፍርድ ቤት ከ1928ዓ.ም በኋላ፣ “በልዩ የቆመ ፍርድ ቤት” መባሉ ቀርቶ፣ “ከፍተኛው ፍርድ ቤት” ተባለ፡፡ ይህም ፍርድ ቤት፣ ከ1928ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ታሪካዊ ስሕተቶችን ፈፅሟል፡፡ በዚህ ወቅትም፣ ከ52 ዓመታት በፊት የፈፀመውን ግዙፍ የሕግ ስሕተት እናወሳለን፡፡ አንዴ “በልዩ የቆመው”፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ የ“ከፍተኛው” ፍርድ ቤት እየተባለ ቢጠራም፣ ፍርድ ቤቱ ፍትሐዊነት የጎደለውና በገዢዎች ጥቅሻ የሚሰራ መሆኑን አንድ አብነት ጠቅሰን እንነጋገራለን፡፡

Read story in PDF

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 26, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.