የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ? (ልጅ ተክሌ ከቶሮንቶ)

ጽሁፍ ካላበሳጨ ወይ ካላስጨበጨበ አይመቸኝም። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚያበሳጭ ወይ የሚያስጨፍር ርእስ ስጠብቅ ሳልጽፍ ቆየሁ። የኢትዮጵያውያን፤ በተለይም የአማርኛ ተናጋሪዎች ከቤንሻንጉል መባረር በራሱ በቂ አናዳጅና አሳዛኝ ክስተት በመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች ስለጻፉበት እሱ ላይ ብዙ አልደክምም። ስለዚህ ሌላ አናዳጅ ርእስ ናፈቅኩ። ባለፈው ሰኞ፤ ከአድካሚው ውሎዬ እረፍት ለመውሰድ ወደኢሳት ድረ-ገጽ አመራሁ።
የኢሳት 3ኛ አመት ዝግጅት …

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 13, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

10 Responses to የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ? (ልጅ ተክሌ ከቶሮንቶ)

 1. አንዋር

  April 14, 2013 at 4:54 AM

  ሰላም ልጅ ተክሌ ጽሁፍህን አነበብኩና ምነው እንደዚህ አሰበ ብዪ ልመልስልህ ስዘጋጅ ደግሜ ሳነበው እንደዚህ በሚል ነው የጀመርከው “ጽሁፍ ካላበሳጨ ወይ ካላስጨበጨበ አይመቸኝም። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚያበሳጭ ወይ የሚያስጨፍር ርእስ ስጠብቅ ሳልጽፍ ቆየሁ። የኢትዮጵያውያን፤ በተለይም የአማርኛ ተናጋሪዎች ከቤንሻንጉል መባረር በራሱ በቂ አናዳጅና አሳዛኝ ክስተት በመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች ስለጻፉበት እሱ ላይ ብዙ አልደክምም። ስለዚህ ሌላ አናዳጅ ርእስ ናፈቅኩ።” በቃ ተናዶ ነው የጻፈው አልኩ እና ተውኩት ግን ሙስሊሙ መብቱን እየጠየቀ ባለበት ሰዓት እንደዚህ አይነት ግብዣ በዓመት አንዴ ቢመጣ ይገርማል ማለት ነው? ችግር እና በደሉን ለሌሎች ኢትዮጵያኖች ሊያሰማና መንግስት እንደሚለው እንዳልሆነ እና የሙስሊሙ አላማ መብቱን ለማስከበር ብቻ እንደሆነ ለማሳወቅ ኢሳት ዝግጅት ላይ መሳተፉ ጉዳት አለው ማለት ነወ ኔስቲ ለማንኛውም እንደገና አስበው እና ጻፍ ለጊዜ ምረንሃል ልጅ ተክሌ :

 2. አባ ጦቢያ

  April 14, 2013 at 5:48 AM

  እኔ ወያኔን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ እንደወራሪ ሳይ የቆየው ሰው ነኝ. ለዘላለሙም ባሁኑ አቋሜ እንደጸናው እኖራለው. ነገር ግን እነዚህ የሚጮኹትን እስላሞች ወያኔ ;;; ደስታውን አልችለውም.

 3. ሃዳሰ

  April 14, 2013 at 9:30 AM

  ለምን አለመስማማትሀን ከነርሱ ጋር አትጨርስም ነበር
  ነው ሁሉም ማውቅ አለበት

 4. gezahegn

  April 14, 2013 at 4:17 PM

  Mr. Tekele from Canada

  I read your comment on ESAT 3rd ceremony, participation of Muslims’ scholars in that ceremony.

  Mr. tekele as you know Ethiopian Muslims are part of or half of Ethiopian population. So how do expect getting freedom from TPLF? Some years back, I remember what you have been said that I support any kind of struggle lead to freedom. Now you do not support Muslims struggle because it is not come from Church or Christians. You are contradict yourself. Whether ESAT support Ethiopian muslins movement or not, Ethiopian muslins will declare our freedom soon at any cost. But our movement is not only for Muslims for all Ethiopians regardless of their religion. ESAT is working for this secret that is why integrating Muslims in its program.

 5. አስራር

  April 14, 2013 at 6:37 PM

  ልጅ ተክሌ!!!
  ሙስሊም አማኝ ነኝ!!!
  ከምሬን ነው አስተሳሰብህን እወድልሃለሁኝ::
  ኢሳቶች ይህንን ለምን እንዳደረጉት ጠይቀሃቸው ቢሆንና ምክንያታቸውን ገልጸውልህ አብረህ
  በአንድነት ጽሁፍህ ውስጥ አካተኅው በሆነ ኖሮ ሙሉእ ባደረገው ነበረ:

 6. abebe

  April 15, 2013 at 7:36 AM

  Anware,gezahegn Be Hasabachu Mulu Be mulu Esemamalewugne.Tekele Ejege Yasaferale Ke ande Halaftena Ke Mesemawu Sewu Yehe Ayetebekem Be Atekalaye Ende Kelede Yeterechu Bezu Merezoche Albet Lemanegnawum Anware Endalek Degemehe Anbebena Endegena Tafe Kezame hasabeken be hassabe Enaa Be Ewunet Enemelsebetalene.

 7. ትዝታ

  April 15, 2013 at 4:36 PM

  ልጅ ተክሌ
  በጽሁፍህ ስለተበሳጨሁ ደስ ይበልህ:: ጭብጨባውን ግን የኢሳትን መጥፋት ለሚጠባበቁት ጭፍኖች ትቼዋለሁ::
  ድንገት የሚያበሳጭ ነገር ስትፈልግ የተከሰተልህን ነገር የከተብክ ኣትመስልም::መነሻ ሀሳብህን ተመልክተው የተለያዩ የመልስ ምት እንደምትቀበል ስለምገምት ለጊዜው እኔን በተለይ የከነከነኝን ላስቀምጥ
  1)”ጴንጤ” ሁሉ ለሀገሩ ያለው ተቆርቁኣሪነት ጎዶሎ ነው” የሚል እንደምታ ያላትን ሀሳብህን ኣጥብቄ እቃወማታለሁ::
  2) አንተና ታማኝ ኦርቶዶክሱን አንወክልም እንዳልከው ብዙሃኑ እንደሚያስቡትም ፓስተር ዳንኤልም ሁሉንም “ጴንጤ” አይወክልም::ገዳዮችን የማይነቅፍ ለተበደሉ የማይሞግት መጋቢ የቀበሮ ባህታዊ የሚለውን ልትለጥፍለት ትችላለህ
  3)ይህን ሃሳብ የምነግርህ አንተ ፕሮተስታንት ቀጥሎ ጴንጤ ብለህ ጎዶሎውን ከነገርከው መሃል አንዱ ነኝ::
  4)ለሃገሬ ያለኝን ፍቅር ግን ላንተ በማስረዳት አልባክንም….ኢትዮፕያ ለዘላለም ትኑር

 8. እኛዉ ነን

  April 15, 2013 at 7:21 PM

  ልጅ ተክሌ ለጽሁፍህ አንተ እንዳደረግከዉ ቁጥር በቁጥር አየሄዱ መልስ ለመስጥት ቢዳዳኝም ዓላስፈልጊ ሙግት መግጠም ተገቢ መስሎ ስላልታየኝ ትቼዉ አንድ የምታዉቀዉን እዉንት መንገር እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ይህንን አስተያየት ከዚህ ጽሁፍ ግርጌ ማኖር ፈለኩ።
  በመጀመሪይ ለኢሳት ቅርብ እንደሆን ሰዉ የኢሳት የድጋፍ ማህበር በየ አገሩ ሲቋቋም ያለው ነጻነት የምታዉቅ አልመሰለኝም። አያንዳዳንዱ ማህበር በአካባቢው ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ ነዉ እንግዶችን የሚጋብዝው። ሌላዉ የኢሳት የድጋፍ ማህበር ለኢሳት ብር ከማሰባሰብ ባለፍ በተልያየ ጎራ አጥር ሰርተዉ የተቀመጡ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ባለ አጋጣሚ አበሮ ለመነጋገርና አብሮ ለመስራት ይችሉ ዘንድ አጋጣሚዎችን መፍጠር መሆኑ የዘነጋኸዉ መሰለኝ። የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴዎች በየከተማዉ ከሚሰፘቸዉ ስራዎች ዉስጥ ሁለቱን ከጠቀስኩልህ ዘንዳ እኔ ባለሁበተ አካባባኢ ለተዘጋጁ አራት ዝግጅቶች እኔዴት እንግዳ እንደመረጥን ልንገረህ።እኔ ባለሁበት ከተማ ይህንን ዝግጅት ስናዘጋጅ በድጋፍ ማህበሩ ዉስጥ ሁለት ሙስሊም ወንድሞቻችን አሉ አነሱ ጃዋር እንዲመጣና አሁን ያለዉ የሙስሊም ወንድሞቻችንን ጥያቄ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖረዉ የሚችለዉን የፖለቲካ እንድምታ እንዲያስረዳልን ፈለጉ፥ የተቀረነዉ ሁለቴም ሳናስብ የጀዋር መምጣት በደስታ ተቀበልነዉ። አጋጣሚ ሁኖ ጀዋር ባለመቻሉ ሃጂ ነጅብን እንዲጠሩ ሆነ። የሃጂ ነጅብ ስልክ በመካከላችን የነበረዉ ሰዉ ስላልነበር አርግጥ ነዉ እሳቸዉን መቻላቸዉን ሊያረጋግጥ የሚችልሰዉ ፍለጋ የኢሳት ማኔጅመንት ጋር መደወል ነበረብንና ያን አድርገናል። ሎሳንጀለሶች ደግሞ ይህን ዘጋጣሚ መጠቀም ፈልገዉ ሶስቱም እኛ የጋበዝናቸዉን እንግዶች መጠቀም ፈለጉ(ሲያትል፣ ሳኖዜ፤ ሎስ አንጀለስና ሳንዲያጎ) ወጪ ለመቆተብ ሲባል እንዲህ አይነት ቅንጅት የተለመደ ነዉ። ምናልባት ከዚህ በፊት የተደረገዉን አንተም ተካፋይ የነበርክበት ዝግጅትና ከዛም በፊት የነበሩት ማየቱ በቂ ይመስለኛል። ነገሩ ይህ ሆኖሳል ለመን ያን ሁሉ ዝባዝንኬ መሞነጫጨር እንዳስፈለገህ አልገባኝም። እነዳዊት እንዲህ ያሉ አወዛጋቢ ጽሁፎችን ማዉጣታቸው የሳይታቸዉ ሂት(traffic) ለመጨመር ሊሆን ይችላል(ነዉ አለልኩም) አንተ ግን እንዲህ ካሉ ረብ ከሌላቸዉ አሉባልታዎች ልትርቅ ይገባሃል። ፈጽሞ በአንተ አያምርም።

 9. serbedin

  April 16, 2013 at 3:33 AM

  – ወዳጄ ታማኝ፤ ከዚህ ቀደም በስህተት ሙስሊሞቹን የካሰ መስሎት በልጅነቱ የክርስቲያኑ በኣል ሲከበር
  ስለሙስሊሞች በአል አለመከበር የተናገረው ንግግር በየዋህነት ቢታለፍም፤ በምንም መልኩ ግን ታማኝ እንደ
  ኢትዮጵያዊ እንጂ የክርስትና እምነት ተከታዮችን ወክሎ የሰነዘረው የይቅርታ ንግግር አይመስለኝም። እኔና ታማኝ
  ኦርቶዶክሶች ብንሆንም ኦርቶዶክሶችን አንወክልም። እኔ እስከማውቀው ድረስ፤ እነ ነጂብ ትናንትም ዛሬም
  ከኢሳትም ጋር ያገናኛቸው የሀይማኖት መሪዎች መሆናቸው ነው። የሀይማኖት መሪዎች ከጋበዝን ደግሞ ቢመጡም
  ባይመጡም የኦርቶዶክሱንም የፕሮቴስታንቱንም፤ የይሁዲውንም፤ የካቶሊኩንም ነው እንጂ፤ በምን መስፈርት ነው
  የሙስሊሞቹን ብቻ የምንጋብዘው? ይሄ አደገኛና መታረም ያለበት አካሄድ ነው። አሳማሚ ቃል ነው እውነት አልነበረም? እስኪ አንደገና ያንብበው አቶ ተከሊ???

 10. andnet berhane

  April 16, 2013 at 10:41 AM

  ተክሌ ኢሳትን ለመንቀፍና እስላም ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ለምን እንዳስቆጨኽ በግልጽ ብታስቀምጠው መልካም ነው ለመሆኑ በዚህ የተነደፈው የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የወንድሞቻችን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በጋራ ለሃገራችን ከውድቀትና ጥፋት ተባብረው ያደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ የተገነባውን የመላው ኢትዮጵያውያን ሕልም ለማጨለም ካልሆነ በስተቀር አሁንም ኢሳት የመላው ኢትዮጵያውያን ማንንም ሳለይ የሚንቀሳቀስ ታላቅ የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ ከመሆን አልፎ ተሟጋች በመሆን ከቢንሻንጉል የተፈናቀሉትን ወደ ስፍራቸው ሊመልስ የቻለው በዳረገው ሁሉን የሚያሳትፍ ዲሞክራሲና ፍትሕ ያለው አመራር በመሆኑ መረዳትና አቋምህን ማሳወቅ ያስፈልጋል:
  እሳትን የሚመሩና እሳትን እዚህ ያደረሱት ዜጎች ባንተ አስተያየት አፍራሽ ግንዛቤ ያዘኑ ብዙዎች ናቸው ይህንን ለማለት የገፋፋህ ምንይሆን ለሚለው በቂና ቅን የሆነ መልስ ካልሰጠህ አንተነት ያጠራጥራል በውስጡ የነበርክ ዛሬ ተለውጠህ የምትሰጠው አሉታዊ ትችት የመጀመርያ ሳይሆን ተደጋጋሚ የሆኑ ቃል ምልልሶችንም ታዝቢያላሁ:
  ላማንኛውም ትግል ስንገባ አምነንና ተረድተን ውጤት ለማምጣት በትጋትና በቆራጥነት መሰለፍ እንጂ እንድ አየር ጠባይ በመቀያየር ሊሆን የማይችል በመሆኑ: አንተም ከኢሳት አስተዳደር ወስጥ ቅራኔ ካለህ ራስህን ከማጋለትህ በፊት መወያየትና ፍላጎትክን ማሳወቅ አንተነትክን ታማሳክር ነበር ያ አልሆነም አሁንም ለዚህ የጻፍከው አሉታዊና የከሰረ ትችት የነጸረ ማብራርያና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ከምን ተነስተህ ድርጊቱን ለማጥላላትና በሕዝቡ በጥርጣሬ መከፋፈል ለመፍጠር ያነሳሳህ ጉዳዩን ማብራት ይጠበቅብሃል:
  ይህን ያልኩበት ምክንያት ካስቀመጥከው አርእስትና ከጽሑፍ ይዞትህ በትሞና በማንበብ የተረዳሁት በውስጥህ እሚከነክንህ ወግንተኛና አሉታዊ አስተሳሰብ ያዘለ በመሆኑ: በለእላው መንገድ ወያነ ሲጫወትበት የነበረው ካርታ ተመዞ ያለቀ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊ ተረድቶትና ተገንዝቦት ከንግዲህ በቃ ብሎ የተነሳበት የትግል ጎዳና ማንም አይቀለብሰውም: ወደአንድነት መስመሩን ቀይሮ የዘር የጎሳን ነቀርሳ ሽሮ ተላቆ