የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በአትላንታ።

Esat Atlanta

Esat Atlanta

የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ለማድረግ በአትላንታ በተዘጋጀው ታላቅ ምሽት ላይ ቁጥሩ በብዙ መቶ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ተገኝቶ ነበር። ገና ከጅምሩ በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስት ታማኝ በየነ፣ አርቲስት ሻምበል በላይነህ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ልጅ ተክሌ በክብር እንግድነት ተገኘተዋል።

ይህንን ዝግጅት በተለይ ልዩ የሚያደርገው በዚህ የአትላንታ ዝግጅት ላይ ኢትዮጵያዊያን እንዳይገኙ አስቂኝ ማስፈራሪያ ሲካሄድ ነበር። ይህ ማስፈራሪያ የተደረገው በሰለሞን ከዳልኝ እና በግብረ አበሮቹ ሲሆን፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ… “ኢሳት በአሸባሪነት የተፈረጀ ድርጅት በመሆኑ፤ ይህ ድርጅት በሚያደርገው ማናቸውም ዝግጅት ላይ የሚገኙ ሁሉ አሸባሪዎችን በመደገፍ ወንጀል የሚጠየቁ ይሆናሉ።” ሲሉ ነበር። ነገሩን ይበልጥ አስቂኝ ያደረገው ደግሞ፤ “በስፍራው ተገኝተን ፎቶ እና ቪዲዮ በማንሳት ማንነታችሁን እናጋልጣለን” ሲሉ ቆይተው፤ ዝግጅቱ በተደረገበት የስብሰባ አዳራሽ አካባቢ ግን ደብዛቸው መጥፋቱ ነው።

የኢ.ኤም.ኤፍ. ዘጋቢ ከአዳራሹ ውጪ አግኝቶ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን እንዳሉት፤ “እነዚህ በአሸባሪነት ሊያስከሱን ፎቶ የሚያነሱትን ሰዎች እየጠበቅን ነው።” ሲሉ ሳቅ የተቀላቀለበት ምላሽ ሰጥተዋል። ለዚህም ይመስላል። ዝግጅቱ ሲጀመር ንግግር እንዲያደርጉ ከተጋበዙት ሰዎች መካከል፤ አቶ ምትኩ ተሾመ የማህደረ አንድነት ሬዲዮን ወክለው ሲናገሩ፤ “በቅድሚያ በማህደረ አንድነት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ብዙ የተሻሉ ተናጋሪዎች ስላሉ ጊዜ አልወስድባችሁም። ነገር ግን አንድ ነገር ለማለት እወዳለሁ። ዛሬ ሁላችሁም በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ተከሳችኋል። እንኳን ለዚህ አበቃችሁ።” ሲሉ ህዝቡ በሳቅ እና በጭብጨባ ደስታውን ገልጿል።

በዝግጅቱ መጀመሪያ ላይ የክብር እንግዶች ሆነው የተገኙት አርቲስት ታማኝ በየነ፣ አርቲስት ሻምበል በላይነህ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና ልጅ ተክሌ ወደ አዳራሹ ሲገቡ… ህዝቡ ከመቀመጫው ተነስቶ በከፍተኛ ጭብጨባ ነበር አቀባበል ያደረገላቸው።

Artist Tamagn Beyene - Atlanta

Dawit Kebede of Awramba Times

ልጅ ተክሌ “አገር ማለት” በሚለው የበቀለ ዋቅጅራ ግጥም ዝግጅቱን ጀምሯል። አቶ ጌታቸው በበኩላቸው፤ “በአትላንታ የኢሳት ድጋፍ ሰጪዎች ስም የአገራችን የኢትዮጵያን ጉዳይ የራሳችሁ አድርጋችሁ እዚህ በመገኘታችሁ አመሰግናለሁ። ለረዥም አመታት እውነትና ኢትዮጵያዊነትን አጣምራችሁ የያዛችሁ የክብር እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ… እንላለን።” ካሉ በኋላ፤ “ኢሳትን ተንከባክበን ማሳደግ አለብን፤ ይህም የዜግነት ግዴታችን ነው።” ብለዋል።

በመቀጠል የክርስትና እና የእስልምና አባቶች ንግግር አድርገዋል። አባ ገብረስላሴ ባደረጉት ንግግር፤ “ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ነገር ስትሰሩ በእግዚአብሄር ስም እንድናገር ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ። በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት አገልጋዮች መካከል፤ የህዝብ መገናኛዎች ወሳኞች ናቸው። መሪዎች ባይወዱት፣ አማኞች ባይቀበሉት እነዚህ ጋዜጠኞች ግን ይናገራሉ። እውነትን ይመሰክራሉ። እግዚአብሄር እነዚህን ሰራተኞች ያለ ምንም ሳንሱር ለህዝብ የሚገባውን መልዕክት እንዲያስተላልፉ ነበር መደባቸው።

Aba GebreSeilassie

እግዚአብሄር ለተገፉት ይጮሃል። እግዚአብሄር በመንፈሱ ካቋቋማቸው ውስጥ በነቢያት አማካኝነት ይናገራል። እንዳሁኑ የህዝብ መገናኛ ዘዴዎች ባልነበሩበት ወቅት በነቢያት አማካኝነት ይነገር ነበር። ካህናቱና ነገስታቱ ህዝቡን ሲቀጡ ሲያስሩ… ህዝቡን ሲበድሉ፤ ወታደሮች ህዝቡን ሲገድሉ እግዚአብሄር በነቢያቱ በኩል ይናገራል።” አባ ገብረስላሴ ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 40 እና 58ትን ጠቅሰው ትምህርት ሰጥተዋል።

(ይቀጥላል)
የሃጂ ሳፊ ንግግር፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና የአርቲስት ታማኝ በየነ ንግግሮች ቀጣዮቹ ናቸው። ዝርዝር ዘገባው ይቀጥላል።
Ethiopians in support of ESAT - Atlanta

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 4, 2012. Filed under ESAT. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.