የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ

——————————–
በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ስም ለተሰየመውና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል በዚህ ወር መጨረሻ በአዳማ ለሚደረገው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የርዕዮት ምስል ያለበት የፖስተር ንድፍ በእጁ ይዞ በመገኘቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው፡፡
——————————-
በአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ምርቱ ጉታ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ገደማ በተለምዶ ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ መታሰሩን የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡

Mertu Guta

Mertu Guta

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፀው ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች የገበያ ስፍራው እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲያሰሙ የነበረውን ብሶት እንደዜጋ ለማዳመጥ ከሞከሩ የአንድነት አባላት መካከል ወጣት ምርቱ ጉታን አስረውታል፡፡

ወጣት ምርቱ ጉታ በአሁኑ ሰዓት በአዳማከተማ ፖሊስ መንሪያ የወረዳ4 ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን በአዳማ ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ለማሰራጨት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀትና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪቃል በአዳማ የአንድነት ጽ/ቤት በወሩ መጨረሻ ለሚዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የፖስተር ንድፍ በእጁ ይዞ በመገኘቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል፡፡

የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል በጽ/ቤቱ በወሩ መጨረሻ የሚያደርገውን የኪነጥበብ ምሽት የከተማው ተወላጅ ለሆነችውና በህገወጥ እስር ለምትገኘው ለርዕዮት አለሙ መታሰቢያ እንደተሰየመ የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ጨምሮ ገልጧል፡፡
Source:-  Fenote Netsanet

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 19, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ

 1. ትዝብት

  March 20, 2014 at 3:58 AM

  ወጣት ምርቱ ጉታ ሰላሙን እመኝልሃለሁ!!
  የነጻነት ታጋዩ ወጣት ምርቱ ጉታ:- “ታጋይ ይሞታል ዓላማውና ትግሉ አይሞትም”!!
  ወጣት ምርቱ አንተ ለጊዘው በእነዚህ የበርሃ ሰው በላ እጅ በአካል ስትሰቃይ : ያ! ለነጻነት የቆምክለት ሰሚ ያጣ 90ሚሊዮን ወገንህ የቁም እሥረኛ መሆኑን አስበህ እንደ-ጥዋፍ እየነደድድክና እየትቃጠልክ ብርሃን እየሰጠህ ለነጻነት የምትታገል የጀግና ጀግና ወንድማችንና ልጃችን በርታ!! እግዚአብሄር እሥራአልን ከግብጽ ባርነት ያወጣ አምላክ ከአንተ ጋር ይሁን!!አሜን!!!!
  ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!!!

 2. babb

  March 20, 2014 at 1:04 PM

  Free Mirtu Guta
  free Eskinder Nega
  Free Reeyot Alemu
  Free Bekele Gerba
  Free wubset Taye
  Free Andualem aragie
  …..

  .
  .
  .
  .
  Free Alemu Jerra
  Free Birhan Taye
  Free Jemaneh Bitew
  Freedom freedom freedom