የአዲስ አበባ ደህንነቶችና ፖሊሶች የአንድነት አባል ላይ ድብደባ ፈፀሙ

Beaten by EPRDF

Beaten by EPRDF

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ አመራር አባል የሆነው ወጣት ብርሃኑ ገረፋ ሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. ሳሪስ አካባቢ የፓርቲውን በራሪ ወረቀት ሲበትን በ1 ደህንነትና በ6 ፖሊሶች በህገወጥ መንገድ መታሰሩን ፓርቲው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡

ወጣት ብርሃኑ በደህንነት አባሉ በመሳሪያ ሰደፍ ጀርባውንና ጭንቅላቱን ከመመታቱ በተጨማሪ ፖሊሶችም እጁን ጠምዝዘው በቦክስ ግራ ጉንጩን መመታቱ ተጠቁሟል፡፡ በእስር ቤት ውስጥ አንድ ቀን አሳድረው ካንገላቱ በኋላ ሐምሌ 23 ቀን 2005 ዓ.ም. በመታወቂያ ዋስ መለቀቁ ታውቋል፡፡

ወጣት ብርሃኑ የፀጥታ ኃይሎች ሲይዙት እጁን በካቴና እንደወንጀለኛ አስረው ሳሪስ አቦ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በእግር ከወሰዱት በኋላ ወደ አቃ ቃሊቲ ፖሊስ መመሪያ ወስደው ማሳደራቸው ታውቋል፡፡

Beaten by EPRDF

Beaten by EPRDF


Source: Fenote Netsanet

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 31, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.