የአዲስ አበባ ተቃውሞ ሰልፍ ቪዲዮ ይመልከቱ (ልዩ የEMF ቅንብር)

EMF – እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1997 ዓ.ም. ነበር “ህዝባዊ ሱናሜ” የተሰኘለት የተቃውሞ ሰልፍ የታየው። ከዚያ ሰልፍ በኋላ የኢህአዴግ አስተዳደር፤ በቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አማካኝነት በመላው አገሪቱ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ በይፋ ተከለከለ። ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም ፈቃድ ሳያገኙ ቀሩ። ሆኖም ከስምንት አመታት በኋላ ሰማያዊ ፓርቲ በአፍሪካ አንድነት ስብሰባ ሰሞን የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ፈቃድ ጠየቀ፤ መጀመሪያ ተከለከለ… በኋላ ላይ ግን ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲያደርግ ተፈቀደና በኢትዮጵያ አቆጣጠር ግንቦት 25 ቀን፣ 2005 ዓ.ም. ፍጹም ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ህዝቡ ተቃውሞውን በሰለጠነ መልክ አቅርቧል። በሚገርም ሁኔታ በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ የገባው ኢህአዴግ የሚያስተዳድረው መንግስት ሆኖ ሳለ፤ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚንስትር ደኤታ ሽመልስ ከማል በዚያኑ ምሽት ኢቲቪ ላይ ቀርቦ፤ ሰልፉን ከእስልምና አክራሪዎች ጋር በማገናኘት፤ ሰማያዊ ፓርቲን “ፖለቲካ በሃይማኖት ጉዳይ መግባት እንደሌለበት ህገ መንግስቱ ቢደነግግም፤ እነሱ ግን ይህንን በመጣስ…” በማለት ስሞታ አቅርቧል። ለማንኛውም EMF የእለቱን ሰላማዊ ሰልፍ የሚያሳዩ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን አንድ ላይ በማቀናበር ለህትመት አብቅቷል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.