የአዲስ አመት ዋዜማ የዋጋ ዝርዝር

Happy Ethiopia new year, 2011. Awra doro

ኢ.ኤም.ኤፍ. ፡ አዲስ አመትን ተከትሎ የመጣው፤ የሰሞኑ የዋጋ ንረት የከተማውን ህዝብ ሲያነጋግር ቆይቷል። እንደ ኢ.ኤም.ኤፍ. ዘጋቢ ከሆነ፤ “ዋጋው ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው ሰማይ ነክቷል” ብሎናል።

የኢ.ኤም.ኤፍ. ዘጋቢ ተዘዋውሮ የተመለከተው የሾላ ገበያን ሲሆን፤ በሌሎች ቦታዎች ዋጋው ሊጨምር እንደሚችል ነው የገለጸው። ከዚሁ ጋር አያይዞ፤ “እንደ ድሮው በመደብ አይሸጥም። የመደብ ገበያ ቀርቷል። የምግብ ሸቀጦች በኪሎ ነው የሚሸጡት። በዚህ አመት በተለይ የነጭ ሽንኩርት ዋጋ ጨምሮአል። ” በማለት ገልጾልናል።

ሪፖርተራችን ከአዲስ አበባ የዘገበልን የዋጋ ዝርዝር ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

ተራ ቁ. አይነት ሾላ ገበያ(በብር) ሌሎች ቦታዎች(በብር)
1 በሬ 10 ሺህ 12 ሺ
2 በግ 800.00 2ሺህ
3 ዶሮ 100.00 150
4 ጤፍ 1ሺ 300 1ሺ 500
5 ፉርኖ ዱቄት (በኪሎ) 12.00 15.00
6 ቀይ ሽንኩርት (በኪሎ) 6.00 8.00
7 ነጭ ሽንኩርት (በኪሎ) 90.00 100.00
8 ዝንጅብል (በኪሎ) 25.00 30.00
9 ቲማቲም (በኪሎ) 12.00 15.00
10 ካሮት (በኪሎ) 8.00 10.00
11 ቅቤ (በኪሎ) 125.00 150.00
12 በርበሬ (በኪሎ) 57.00 70.00
13 ስኳር (በኪሎ) 14.00 15.00
14 ጨው (በኪሎ) 3.00 5.00
15 ችቦ 5.00 8.00
16 ሳሙና (ፒኮክ/ቢ29) 8.00 10.00

ተያይዞ በደረሰን ዘገባ መሰረት…

በአገሪቱ ካሉ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ክፍያ በማስከፈል የመጀመሪያ የሆነው ICS ኢንተርናሽናል ኮሚዩኒቲ ት/ቤት፤ ዘንድሮ ለጀማሪ ተማሪዎች (ለነርሰሪ) በዓመት 118ሺ ብር ወይም 6,900 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን ክፍያው በትምህርት ደረጃው እያደገ ይሄዳል፡፡ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚከፈለው በዓመት 380ሺህ ብር ገደማ ወይም 22,310 ዶላር ያስከፍላል፡፡ ትምህርት ቤቱ ለመጪው የትምህርት ዘመን የ10% ጭማሪም አድርጓል፡፡

ሳንፎርድ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ለጀማሪ ወይንም ለነርሰሪ ተማሪዎቹ፣ ለኢትዮጵያውያን በዓመት 18,420 ሲሆን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዓመታዊ ክፍያው በዓመት 42,669 ደርሷል፡፡ ት/ቤቱ ለውጪ አገር ዜጐች የኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ዓመታዊ የክፍያ መጠን በ5 እጥፍ የሚያስከፍል ሲሆን፣ ለጀማሪ የውጭ ዜጋ ተማሪዎች በዓመት 92,445፣ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በዓመት 205,122 ብር ያስከፍላል፡፡ ት/ቤቱ በዘንድሮው ዓመት የ15% ጭማሪ ማድረጉም ታውቋል፡፡ ይኸው ትምህርት ቤት ለኢትዮጵያዊ ተማሪዎች የመመዝገቢያ 24,344 ብር ሲያስከፍል ለውጭ አገር ዜጐች ደግሞ ብር 48,144 ብር የመመዝገቢያ ያስከፍላል፡፡ የግሪክ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት በበኩሉ፤ ለመጪው የትምህርት  ዘመን የ40% የክፍያ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን ለነርሰሪ/ለጀማሪ ተማሪዎቹ 16470፣ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ 41,280 ብር ያስከፍላል፡፡ የመመዝገቢያ ክፍያውም 2,500 ብር ደርሷል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 9, 2011. Filed under FEATURED. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.