የአውራምባ ታይምስ ዋና አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ታስሮ ተፈታ! ም/አዘጋጁ አልተፈታም!!

የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ ባለፈው እሁድ ከመኖሪያ ቤቱ በታጣቂዎች ተይዞ የተወሰደ መሆኑ ይታወቃል። በተያያዘ ዜና የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ዳዊት ከበደም ከትላንት በስቲያ በማዕከላዊ እስር ቤት ለአራት ሰአታት ከታሰረ በኋላ መለቀቁን ከዚያው ከማዕከላዊ እስር ቤት ያገኝነው መረጃ አረጋግጧል። በወቅቱ የማዕከላዊ እስር ቤቱ ሃላፊ ዳዊት ከበደን፤ “ምክትል አዘጋጁ የታሰረው ከናንተ ጋር በተያያዘ መንገድ አይደለም” በማለት ከጋዜጠኝነት ጋር ተያይዞ የሚሰጥ መግለጫ ትክክል አይደለም ብለውታል።

ዳዊት ከበደ ከማዕከላዊ ከተፈታ በኋላ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ወደ አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ያደረግነው የስልክ ጥሪ ተሳክቶ ለጥቂት ደቂቃዎች ምላሽ ሰጥተውናል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት እኚሁ ባለስልጣን ወንድወሰን የታሰረው ከጋዜጠኝነት ጋር በተያያዘ አለመሆኑን ጠንከር አድርገው ገልጸዋል። በኢ.ኤም.ኤፍ በኩል “የኛም አደዋወል በጋዜጠኝነት ጋር ካልተያያዘ በምን ምክንያት ታሰረ?” የሚለውን ሙግት አዘል ጥያቄ ደጋግመን ካቀረብንላቸው በኋላ… “ውብሸት የታሰረው ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ነው” ብለዋል።

ኢ.ኤም.ኤፍ – “አንድን ሰው ወይም ጋዜጠኛ ሽብርተኛ ለማለት መስፈርቱ ምንድነው?” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “እሱ በአዲሱ ህግ ላይ የተካተተ ስለሆነ እዚያ ላይ ማንበብ ትችላላችሁ” ብለውናል።

ኢ.ኤም.ኤፍ – “እሁድ ቀን ያሰራችሁበትስ ምክንያት?”
ባለስልጣኑ – “በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ያሰርነው በፍርድ ቤት ማዘዣ ነው።”
ኢ.ኤም.ኤፍ – “በማዘዣው ላይ የተጻፈው ቀን አንድ ሳምንት አስቀድሞ መሆኑን ነው የሚያሳየው”
“ማዘዣው ከወጣ በኋላ ክትትል ስናደርግበት ነበር”
ኢ.ኤም.ኤፍ – “በፍርድ ቤት ማዘዣው ላይ በአሸባሪነት ተጠርጥሮ ይላል። ይህ ጋዜጠኛ አሸባሪ ለመሆኑ ምንድነው መረጃችሁ?”
ባለስልጣኑ – “በአዲሱ ህግ መሰረት አሸባሪ የሆነ ብቻ ሳይሆን ለአሸባሪዎች ድጋፍ የሰጠም ይታሰራል፤ ይቀጣል።”
ኢ.ኤም.ኤፍ – “ኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪ የተባሉትን ድርጅቶች ስም ዝርዝር ሊገልጹልኝ ይችላሉ?”
ባለስልጣኑ – “ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት ሰባት ናቸው”
ኢ.ኤም.ኤፍ – “ታዲያ ይህ ጋዜጠኛ ከየትኛው ድርጅት ጋር ነው ሽብር የፈጸመው?”
ባለስልጣኑ – “እሱን ወደፊት በፍርድ ቤት የምናየው ነገር ይሆናል። አመሰግናለሁ።” በማለት ከዚህ በላይ ሊያወሩን እንደማይፈልጉ ገልጸው ስልክ ምልልሳችን አበቃ።
ሌሎች ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፤ ውብሸትን ከግንቦት ሰባት ጋር አያይዘው ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለውናል። በአዲሱ ህግ መሰረት ኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በተመለከተ አስተያየት የሰጠ ወይም ዜና ያቀረበ ጋዜጠኛ በአስራ አምስት አመት ጽኑ እስራት ይቀጣል። አሁን በአውራምባ ታይምስ ም/አዘጋጅ በወንድወሰን ላይ እየተደረገ ያለውን ይኸው ነው። በመሆኑም በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በቅርብ በሚያውቁት ድርጅት አማካኝነት ወይም በግላቸው ይህን አይነቱን የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ ለሰብአዊ መብት ተቋማት በመግለፅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እንዲፈታ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጉ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 23, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.