“የአውራምባ ታይምስ ቀጣይነት አጠያያቂ ሆኗል”

ውድ የአውራምባ አንባቢያን

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ በአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይሰፍን ለማድረግ ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችን በተደጋጋሚ ማሰር፣ ማስፈራራትና ማዋከብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካታ ወጣትና አንጋፋ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ በተለይ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ወዲህ ኢህአዴግ መንበረ ስልጣኑን በሀይልና በፍጹማዊ የበላይነት ለመቆጣጠር ያስችለው ዘንድ ጣቱን ከቀሰረባቸው ሴክተሮች አንዱ ነጻው ፕሬስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም በርካታ አፋኝ ህጎችን ከማውጣት ባሻገር የንግድ ተቋማት ማስታወቂያ እንዳይሰጡ ጣልቃ ገብቶ በማስፈራራት፣ ይተቹኛል ያላቸውን ጋዜጦች በኢኮኖሚ ተዳክመው አቅም እንዲያጡ የማሽመድመድ አማራጭ በዋናነት ሲጠቀምበት ቆይቷል፡፡ ተስፋ ባለመቁረጥ ይህን ሁሉ ጫናና ፈተና ተቋቁመው ጥቂት ጋዜጦች ለመቀጠል ቢሞክሩም፡፡ ሰሞኑን ከሁሉ የከፋ አስደንጋጭ አደጋ ተቃርጦባቿል፡፡ አገዛዙ በጋዜጦች የማተሚያ ዋጋ ላይ ከ45% እስከ 50 % ጭማሪ አድርጎ ጋዜጦች የማይኖሩባት ኢትዮጵያ ለመፍጠር የቆረጠ ይመስላል፡፡ በጣም አስገራሚው ደግሞ ‹‹መንግስትን ለሚተቹ ጋዜጦች ማስታወቂያ እንዳትሰጡ›› ብለው ነጋዴውን በማስፈራራት የሚታወቁ ባለስልጣናት የህትመት ጭማሪውን በተመለከተ ሲጠየቁ ‹‹ማስታወቂያ ያላቸው ጋዜጦች በዚህ ጭማሪ አይጎዱም›› በማለት ማንን ለመጉዳት ታስቦ ጭማሪ እንደተደረገ በይፋ አስታውቀዋል፡፡

ውድ አንባቢያን

ከዚህ የህትመት ጭማሪ በኋላ የአውራምባ ታይምስ እጣ ፈንታና ቀጣይነት አጠያያቂ ሆኗል፡፡ እናም ህትመቷን ለማስቀጠል ከነደፍናቸው በርካታ ስትራተጂዎች አንዱ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን በሳምንት አንድ ዶላር ብቻ በመክፈል ማንበብ የምትችሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ከዚህ በምናገኘው መጠነኛ ገቢ ደግሞ ህትመቷን ማስቀጠል ነው፡፡ እናም በዚህ አሰራር መሰረት ዘወትር ቅዳሜ ሶፍት ኮፒው በኢ.ሜይል እንዲደርሳችሁ የምትፈልጉ ውድ አንባቢያን በሳምንት አንድ ዶላር ብቻ (ለአሰራር እንዲመች የሦስት ወሩን 12 ዶላር ቅድሚያ)  በመክፈል በኢ.ሜይል አድራሻ awrambasubscription@gmail.com አማካኝነት ስማችሁንና የኢ.ሜይል አድራሻችሁን እንድታስመዘግቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል

መጋቢት 17 ቀን 2003 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ክፍያውን በፔይፓል ለመፈጸም ይህንን ሊንክ ይጫኑ PayPal

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 26, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.