የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ ታሰረ

Ethiopian Journalist arrested

Ethiopian Journalist arrested

የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ትናንት (ዕሁድ) ከቀኑ 9፡00 ሰዓት አካባቢ በርካታ ቁጥር ባላቸው የጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ከመኖሪያ ቤቱ መታሰሩን አውራምባ ታይምስ ከቤተሰቦቹ አረጋግጧል፡፡
ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር ሲውል መኖሪያ ቤቱ ተበርብሮ የተለያዩ ሰነዶች፣ ሲዲዎች፣ ካሜራዎች፣ የአውራምባ ታይምስ የተለያዩ ዕትሞች መወሰዳቸውንም ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋዜጠኛ ውብሸት የታሰረበትን ምክንያት እንዲገለጽለት ለሚመለከታቸው የመንግስት የጸጥታ ተቋማት ጥያቄ አቅርቦ በዛሬው ዕለት ባገኘው ምላሽ ‹‹ጉዳዩ ከጋዜጣዋ ጋርም ሆነ ከሙያው ጋር ተያያዥነት የለውም›› የሚል ምላሽ አግኝቷል፡፡ ሆኖም የታሰረበት ምክንያት በተጨባጭ ይህ ነው ተብሎ አለመገለጹ እጅግ አሳስቦናል፡፡
የም/ዋና አዘጋጁ መታሰር በተቀሩት የጋዜጣዋ ባልደረቦች ስነልቦና ላይ መረበሽን ፈጥሯል፡፡ ስለሆነም በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከግምት በማስገባት ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገበት ምክንያት እንዲሁም የሚገኝበትን ሁኔታ መንግስት እንዲያሳውቀን የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይጠይቃል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 20, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.