የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ተፈቱ

EMF – የአንድነት ፓርቲ አባላት ሲታሰሩ፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አባላቱ ወደታሰሩበት እስር ቤት ድረስ ሄደው፤ “የፓርቲው መሪ እኔ ነኝ። ጥፋት ካለ መታሰር ያለብኝ እኔ እንጂ አባላቱ አይደሉም” በማለታቸው ምክንያት አባላቱ ተፈትተው እሳቸው መታሰራቸው ይታወሳል። የተፈቱትም አባላት ሳይውሉ እና ሳያድሩ፤ መስከረም 19 ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ቀጥለው ነበር። ፖሊስ አመራሮቹን የማሰር ስራውን በመቀጠል፤ አቶ አስራት ጣሴ፣ ዳንኤል ተፈራ፣ ተክሌ በቀለን እና ብቸኛውን የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉን አስሮ ማቆየቱ ይታወሳል። አሁን ከፓርቲው ባገኘነው መረጃ መሰረት ግን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ ሌሎች 26 ያህል ታሳሪዎች መፈታታቸው ተገልጿል። ዶ/ር ነጋሶ እንደፓርቲ መሪ ያደረጉት መስዋዕትነትም በመልካም ጎኑ የሚጠቀስ የከተማው ወሬ ሆኗል።
miliondimts

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 27, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.