የአታላንታ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ።

ማኅደረ አንድነት ራዲዮ ለኢ.ኤም.ኤፍ በላከው ዘገባ መሰረት የአታላንታ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ላይ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ታውቋል።
በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ዐረመኔያዊ ድርጊት በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ በአትላንታ፣ ጆርጂያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከኦሎምፒክስ ሴንቴኒያል ፓርክ ባሻገር ከሚገኘው ሲ.ኤን.ኤን. ደጃፍ ጥቁር ልብሶችን በመልበስና ልጆቻቸውን ጭምር በማምጣት ሰላማዊ ሠልፍ አደረጉ። ሲ.ኤን.ኤን. ሳዑዲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍና መከራ ትኩረት ሰጥቶ ለዓለም ማሳወቅ የሚገባውን የመገናኛ ብዙኃን ግዴታ አለመወጣቱ ማኅበረሰቡ የተሰማውን ቅሬታ በመፈክር አስተጋብቷል። የሳዑዲን ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚያሳዩ ምስሎችንና ከ1,400 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ለሳዑዲና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ያደረገችውን የሰብዓዊ ድጋፍ የሚገልፁ መፈክሮች በአደባባይ ላይ እንዲታዩ ተደርጓል። በሳዑዲ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ ሰቆቃችን እንደሆነ መፈክሮች ከሃዘን ጩኸት ጋር እየተቀላቀለ በተደጋጋሚ ተስተጋብቷል። ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የአታላንታ ኢትዮጵያውያን  በሳዑዲ ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ

የአታላንታ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 19, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.