የአቧሬ ጉልት ገበያ ተቃጠለ

እሳቱን ለማጥፋት በሞከሩ ዜጎች ላይም የወያኔ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው ቢያንሰ ሁለት ሰዎች ሞቱ ።
ትናንት ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ (9 ፣30 ) ላይ አዲሰ አበባ ወስጥ አቧሬ አካባቢ “ጉልት ገበያ”እየተባለ የሚጠራው ቦታ በእሳት መጋየቱ ታውቋል። በእሳቱ ምክንያት በርካታ ንብረት ወድሟል። የእሳት አደጋ መኪኖች እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አለማድረጋቸውና እንዲያዉም እሳቱን ለማጥፋት የሚሞክሩትን ዜጎች የጸጥታ ኃይሎች ጥይት እየተኮሱ ሊያግዱ መሞከራቸው ወያኔ ሆን ብሎ ያቃጠለው ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተያየት ብዙዎች አየሰጡ ነው። ቢያንሰ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መሞታቸው ታዉቁአል። ቦታዉን ለከበርቴዎች ለመሸጥ የዜጎችን ንብረት ሙሉ በሙሉ ማውደም በጣም አሳዛኘ ድርጊት ከመሆኑም በላይ ይህ የጥፋት መልክተኛ የሆነው ወያኔ በህዝብ ላይ ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ በህዝብ ላይ የሚያደርሰው ግፍ ማለቂያ የሌለው መሆኑ ብዙዎች በቁጭት ተናግረዋል።

ምንጭ፡ የፌስ ቡክ ዘገባ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 24, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.