የአባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ) መገለባበጥና ኢሳት – እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)

አባ መላ ማን ነው?
በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል። Read story in PDF: አባ መላ ማን ነው?

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 11, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to የአባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ) መገለባበጥና ኢሳት – እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)

 1. በለው!

  March 11, 2014 at 3:26 PM

  “ባዶ ቀፎ ከፊት ሲም ካርድ ከኋላ
  ከፊት ያፋሽካል ከኋላ እየበላ
  ተጣርቶ አይመልስ መልሶም አይጠራ
  “Who is in Charge?”አለ ሰሚ አጥቶ ቢጣራ።
  በለው!
  “በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትቅም ላይ ጠንካራ አቋም አለኝ” አባ መላስ…. በኢትዮጵያ አየር መንገድ እረዳት አብራሪ ኀይለመድክን አበራ የጠለፈን አውሮፕላን ሳይ አስተሳሰቤ ተናወጠ…የኢትዮጵያ ጥቅም ሉዓላዊነት ተነካ ዘራፍ አለ። በለው!ግለሰቡ አቋሜን ለወጥኩ ሲል በድረ-ገፁ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራን ሶስቱን ቀለማት ወደ ጎን ስሎ ኮከቡን ውጭ አስቀምጦት ነበር፣ አንዳንዴ ልማታዊ ካድሬ ወደብ፣ አውሮፕን፣ዳርድንበር፣ ፻፶ሺህ ስደተኛ በአረብ ሀገር መደፈር፣ መደብድብ፣ መዋረድና አንገታቸው በሜንጫ ሲቀላ ለቁጥር መሙሊያና ለዝና አለቀሱ እንጂ ሀገርና ፓርቲ ይምታታባቸዋል ልማትና ጥፋት አይገለጥላቸውም…ሳይናገሩ የሚጨበጨብላቸው የራሳቸው አማኝ የዋህ ተከታዮችና ሆዳቸውን አቀብድደው ቱልቱላ የሚነፉበት መድረክ ስላላቸውና ስለሚመቻችላቸው እራሳቸውን በማግዘፍ ነው።

  ***”የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳን ጋር በድንበሩ ጉዳይ እየተዳደረና ተግባራዊ እያደረገ ያለው የቀድሞወች የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት እና የደርግ መንግስት ተፈራርመውት የነበረውን ነው ብሎ ተናግሮት የነበረውን አስመልክቶ የደርግ መንግስት ከሱዳን ጋር ምን የተፈራረመው ነገር አለ ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ መንግስቱ ኃይለማርያም መስል ሲሰጡ ምንም የተፈራረምነው ነገር የለም። ኃይለማርያም እና ወያኔ ውሸታሞች ናቸው። ደርግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመው ሰንድ ካለ ለምንድን ነው ወያኔወች ሰነዱን ለህዝብ ይፋ የማያደርጉት? …” የቀድሞው የኢ/ፕ/ ኮ/መንግስቱ ኃይለማርያም

  ***”የኢሕአዴግ መንግሥት ለሱዳን መሬት ቆርሶ የሚሰጥበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር አንድ ነው፡፡ በ1996 ዓ.ም. ከሱዳን ያለፉ አሸባሪዎች በአዲስ አበባ የግብፅ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ላይ የግድያ ሙከራ በመደረጉ ምክንያት በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ግጭቶች ነበሩ፡፡ በዚህ ግጭት ወቅት በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር አካባቢ ያሉ የሱዳን አርሶ አደሮችና ኢንቨስተሮች ተፈናቅለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ድንበሩ አካባቢ በተጨማሪ መሬት ክፍት ሆኗል፡፡ ይህ ተጨማሪ መሬት ክፍት በሚሆንበት ጊዜ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ይህንን መሬት ማረስ ጀምረዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀደም ሲል ከነበሩ ስምምነቶች ተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር በዚህ መሬት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ባንነካቸው፣ አጠቃላይ የድንበር ማካለሉ ሥራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ማንኛውም አርሶ አደር እንዳይፈናቀል የሚል ስምምነት እንዲፈረም አድርገናል፡፡ ይህንን ስምምነት የሱዳን መንግሥት ተቀብሎ ተጨማሪ ነገር ነው ያደረገልን፡፡ ስለዚህ እኛ የምናጣው የሰጠነው ወይም የምንሰጠው መሬት የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ጉዳይ የሚነሳበት ትክክለኛ መነሻ የለም፡፡ አሁን የተከለለ መሬት የለም፡፡ የተከለለ መሬት በሌለበት ይህ ለዚህ ተሰጥቷል የሚባል ነገር የለውም፡፡ እንዴት እንደሚካለል ግን ከአፄ ምንሊክ ጀምሮ የተደረጉ ስምምነቶች መሬት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ አለ፡፡ ነገር ግን ኮሚቴው ሥራውን ጨርሶ ያስረከበበት ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ ይህ ስምምነት ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ከሕዝብ ጋር ተወያይተን እንዴት ተግባራዊ እናድርገው የሚል ሥራ ወደፊት ይጠብቀናል፡፡ በቅርቡ በተካሄደው የሁለቱ አገሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የማካለልና የሕዝብ ማስፈር ጉዳይን ምን እናድርግ የሚል ተነስቷል፡፡ ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን አልጨረሰም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሥራውን አጓትቶታል፡፡ ስለዚህ ሥራውን እንዲሠራ ማድረግ ይገባል ከሚል ስምምነት በስተቀር ወደማካለል የሚያደርሰን ደረጃ ላይ አልደረስንም፡፡”ኃይለማርያም ደስአለኝ ከልማታዊ ጋዜጠኞች ጋር..

  ***”ይገርማል!።አንዳንዱ መሬቱ አሳልፎ ላለመስጠት ይሰዋል። ሌላ ደግሞ የሀገር መሬት በአሮጌ አውሮፕላን ይለውጣል፣ ይሸጣል። ወይ ህወሓቶች! የኢትዮጵያን መሬት እየቆረሱ ለመቸብቸብ ነው እንዴ ስልጣን የያዙ?
  በቃ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን መሰጠቱ ተረጋግጧል። ዉሳኔው ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው። መሬታችንን እናስመልሳለን።” ..አብርሃ ደስታ ከመቀ(ቐ)ሌ(ለ)

  ***”የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው:: በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል::” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ…

  ***“ኢህሃዴግ አለቅጥ ሰብቷል በስብሷልም፤ በዚሁ ሁኔታው በቀጣዩ ምርጫ እንደ ዘጠና ሰባቱ በዝረራ መሸነፉ አይቀሬ ነው” ይለናል። እኛም ይሄንን ነገር ራሱ ቤን ከበደ (ከኢትዮጵያ ፈረስት!)ነው የሚናገረው ወይስ በላዩ ላይ ያደረው መንፈስ እየለፈለፈ ነው የሚለውን እያጣራን ነው። ቁምነገሩ ግን ቤንም እንደ ሌሎቹ ኢህሃዴግዬን “ላጥ በይ” ብሎ ሌላ ሊወሽምባት ከጅሏል ወይ ደግሞ ተለይቷት ፈት ሆኖ መኖሩን መርጧል። ዘንድሮ እንደሁ ክኢህሃዴግ የማይፋታ ባል እና ባላባት የለም… (እዘች ጋ ሳቅ አለ…) አቤ ቶክቻው እንደዘገበው።
  አባ መላ ኢህአዴጎችን እየሰደበ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ሲቀላቀል “አገኛለሁ” ብሎ ያሰላው ጥቅም ነበር። ሆኖም ሀሳብን በነፃነት ለመግለጽ ከሚያስችል ነፃ መድረክ ውጪ ሌላ ነገር ሊያገኝ አልቻለም። ባገኘው ነፃ መድረክም ማንም ሳይቆነጥጠው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቀድሞ አለቆቹን እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ነግሯቸዋል። እኛንም አስቆናል። ስንስቅለት ጨምሮ ጨማምሮ አቅምሷቸዋል። እኛም፦“የአገሩን ሰርዶ ባ’ገሩ በሬ” እያልን ተዝናንተናል። ሆይ መላ ነሽ.. ሆይ መላ… ድንቄም አባ መላ? በለው! በቸር ይግጠመን

 2. tilahun

  March 11, 2014 at 6:07 PM

  Enndelbu best comment and appeal for all Democratic
  and civic organization .You get more and more matured .we hope you and your friends lead us to the promise land of freedom!!

 3. Satenaw

  March 11, 2014 at 6:59 PM

  ይሄ ሰው አባ መላ ሳይሆን አባ አተላ ነው ስሙ መሆን ያለበት:: የሰው አተላ ነው:: እግዚአብሔር ሰውን በማሕጸን እንዲረገዝ ሲፈቅድ እርሱ ሲረገዝ ግን ምናልባት ቢዚ ሆኖ ረስቶት ተረግዞ እንደሆነ አላውቅም:: የአይምሮ በሽተኛ ይመስለኛል:: ህይወቱን በሙሉ በማኩረፍና በመገለባበጥ የፈጀ የሥነ ልቡና ችግር ያለበት ድኩም ፍጡር ነው::

  በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገለባብጦ የተናገራቸው ፍጹም ተጸራሪ ነገሮች ለማመን የሚያስቸግሩ ናቸው:: ጤነኛ አይምሮ ከቶ እንደዚህ መገለባበጥ አይቻለውም የታመመ ካልሆነ በቀር::

  ለወደፊቱ ወያኔዎች ሲመጡ እየተቀበሉ በሃላፊነት ቦታ ላይ ማንጠላጠል ተገቢ እይደለም:: ወያኔም መታገል ከፈለጉ እዚያው ባሉበት ማድረግ ይችላሉ:: ወደዚህ ወደ እኛ ለምን እንደሚመጡ አላውቅም:: የተቃዋሚው ክፍል ሃይል አነሰው ያላቸው ማነው? እዚያው ወያኔ ውስጥ ሆነው ይታገሉ:: አንዴ በወያኔ የተለከፈ ሰው ምን ግዜም ወያኔ ነው ከአቶ ገብረ መድህን አርኣያና ከጥቂቶቹ በስተቀር::

 4. TERUBE

  March 14, 2014 at 10:33 AM

  ER ABA MELA YELOTEM MELA,,BE 60 AMETO YEGLBABETUWA KKKKKKKKK

 5. ትዝብት

  March 15, 2014 at 3:08 AM

  ከሁሉ በፊት የከበረ ሰላምታየን ላስቀድም!
  ከረጅም ቆይታ በሁዋላ መመለሴ ነው;
  በቅድሚያ መታወቅ ያለበት ማንኛውም “ሚዲያ” ከምንምና ከማንም የፖለቲካ ድርጅት ወገናዊነት መወገን በአለም አቀፉ የጋዘጠኞች ሕግ መሰረት ክልክል ከመሆኑም ባሻገር በሕጉ መሰረትም ያስቀጣል; አንድ “ሚዲያ”ሁሉንም ወገን በማቅረብ ጋዘጣዊ ስራውን የማከናወን ግዴታ አለበት; ጋዘጠኛው ቅድመ መረጃዎችን በማሰባሰብ ጭብጡን በመረጃ በማስደገፍ ሁሉንም ወገን ያለምንም ፍራቻና ይሉኝታ የራሱን የግል አመለካከት ሳይጨምር ጥያቄውን በአግባቡ ማቅረብ ይጠበቅበታል;
  ታዲያ አድማጩ ወይም ተመልካቹ የሁሉንም ወገን ሰምተው የራሳቸውን አቁዋም መያዝና መክራከርና መወያየት ይችላሉ:
  ማለት የፈለኩት “ኢሳት” ሚዲያ በመሆኑ ተቃዋሚንም ሆነ ደጋፊንም ወይም መሃል ሰፋሪም ሁሉንም
  በእኩልነት ማስተናገድ የሙያ ግዴታ አለበት::
  ስለዚህ አባ መላንም ሆነ ሌላውን በእኩልነት ማስተናገድ ሃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ስለሆነ ሊወቀሱ አይገባቸውም::

  ኢትዮጵያ በክብር ለዘልዓለም ትኑር!!!