የአማራ ህዝብ በመሰደቡ… አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ ነው!

(EMF) የአማራውን ህዝብ የተሳደቡትን የብአዴን ከፍተኛ አመራር; አቶ አለምነህ መኮንንን በመቃወም አንድነት ፓርቲ በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ:: ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ መዘጋጀቱንና ለዚህም ጥበቃ እንዲደረግ የፖሊስ ሃይል እንዲመደብ የከተማውን ከንቲባ በደብዳቤ ጠይቋል:: ሙሉውን ደብዳቤ ከዚህ በታች ለህትመት አብቅተነዋል::

ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ መዘጋጀቱንና ለዚህም ጥበቃ እንዲደረግ የፖሊስ ሃይል እንዲመደብ የከተማውን ከንቲባ በደብዳቤ ጠይቋል::

ፓርቲው ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ መዘጋጀቱንና ለዚህም ጥበቃ እንዲደረግ የፖሊስ ሃይል እንዲመደብ የከተማውን ከንቲባ በደብዳቤ ጠይቋል::


ይህ በእንዲህ እንዳለ… በትናንትናው ዕለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው “….አቶ አለምነው መኮንን፣ ለአማራ ህዝብ ለውጥ ደከመኝና ሰለቸኝ ሳይል ያለመታከት ሲሰራ የኖረና እየሰራ ያለ ነው::” በማለት ተናግረዋል:: ይህ ደግሞ በጥፋት ላይ ሌላ ጥፋት ሆኖ የአማራውን ህብረተሰብ ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ አሳዝኗል::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 14, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to የአማራ ህዝብ በመሰደቡ… አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ ነው!

 1. AleQa Biru

  February 14, 2014 at 9:24 AM

  ወይ ስራ ማጣት…መቼ ነው የአማራ ህዝብ የተሰደበ?
  ሌላ ክልል ውስጥ ሄደው የሚኖሩት አማሮች ሁሉንም የአማራ ህዝብ ይወክላሉ ተባለ እንዴ?

 2. andnet berhane

  February 14, 2014 at 5:33 PM

  አለቃ ብሩ ምንለማለት ፈለግህ በመጀመርያ የትም ይሁን የት ሕዝብን ማንቋሸሽ ትክለኛ አለመሆኑን ካመንክበት መልካም ነው: ነገርግን ሕዝብ የትም የትም ይሁን ባጠቃላ ተነክቷል ስለዚህ እንዲህ ያሉ ያልታረም አንድበት ያላቸው ሰዎች በስልጣን ተጠቅመው ሕብን ማዋረድ አግባብና የህገመንግስቱ የሰጣቸው መመርያ ስለ ሚጻረር ከእርካናቸው መወገድና በህግ የመጠየቅ ኃላፊነት አለባቸው:ስለዚህም ያስቀመጥከው አስተያየት መሰረት የለእለው በመሆኑ ጉዳዩን በጎጠኝነት ያስመስላል: ሁለተኝ ክልል ማለት ትርጉሙን ማወቅ ጠቃሚ ነው ልዩነት በስፍራ መለካት የለበትም እንድሕዝብ ቅን ማሰብና በቅንመመልከት መልካም ነው: ጉዳዮ ባያምህ ብዙዎች ያማቸዋል አስብበት

 3. AleQa Biru

  February 16, 2014 at 7:07 AM

  አንድነት ብርሀኔ/ብርሀነ,

  በመጀመሪያ “የአማራ ምክትል ምናምን” የተባለው ሰውየ የተናገረው የጅል/ሞኝ ንግግር መሆኑ አልጠፋኝም:: ነገር ግን ጉዳዩን ከዚህ የዘለለ አድርው የፖለቲካ ትርፍ አገኛለሁ ብለው እንዲያውም ጭራሽ በፓርቲዎች ደረጃ ተቀናጅተው ጊዚያቸውንና ገንዘባቸውን እያጠፉ ያሉትን ስመለከት ደግሞ የበለጠ ገርሞኛል:: እንዴት በአንድ ጅል/ሞኝ ሰው ቂል ንግግር (የምላስ-ወለምታም ሊሆን ይችላል)አንድ ለራሱ ክብር ያለው ፓርቲ ውድ ጊዜውን ያባክናል?

  ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሌላ ትልቅ አጀንዳ ጠፍቶ ነው ሁሌ በአሉባልታ እና በተልካሻ ነገሮች ላይ በተመሰረቱ “ችግሮች” ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩት? ከምር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስቡ ከሆነ ለምን ህዝቡን ቀን ከቀን የሚሰቃይባቸውን ጉዳዮች እያነሱ አማራጭ መፍትሄ አያቀርቡም? ወይም መንግስትን መፍትሄ እንዲያቀርብ አይወተውቱም?

  – የትራንስፖርት ችግር (በተለይ በአዲስ አበባ)
  – በየጊዜው የሚጠፋ የመብራት, የስልክ እና ውሀ አገልግሎት
  – የኑሮ ውድነት እና ሌሎች እኔ (ውጭ በመኖሬ ምክንያት)የማላውቃቸው ችግሮች

  እና ወንድም መጀመሪያ የሰጠሁት አስተያየት ከዚህ መንፈስ የተነሳ እንጂ “ህዝብን ማንቋሸሽ” ነውር መሆኑ ጠፍቶች አይምሰልህ::