የአማራውን ህዝብ በሰደበው አለምነው መኮንን ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳው ቀጥሏል (Photos and video)

በዛሬው እለት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ ጠንካራ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ በተለይ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ነው፤ የከተማው ነዋሪም አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል፡፡

 ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል

ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል


በባህር ዳር የአንድነትና የመኢአድ አባላት ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል

በባህር ዳር የአንድነትና የመኢአድ አባላት ጫማ በማውለቅ በብአዴን ላይ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል


በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ ቅስቀሳ እናዳይደረግ ማይክራፎን መበስበር ጭምር ሙከራ ቢያደርግም የከተማዋ ነዋሪዎች የፖሊሶቹንና የትራፊኮቹን ህገወጥ ድርጊት አስቁመዋል፡፡ አካባቢው “ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” በሚለው ዜማ ደምቋል፡፡

ፖሊሶቹ ከህጉ ይልቅ ለአለቆቻቸው ታማኝነታቸውን እያረጋገጡ መሆናቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል፡፡ ህዝቡ ቀስቃሾቹ ሊነኩ አይገባም በማለት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል ረዳት ኢንስፔክተሩ ተጨማሪ ሀይል እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም በህዝቡ ጫና የቅስቀሳ ቡድኑ ስራውን ቀጥሏል፡፡

Source: Fenote Netsanet

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 21, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የአማራውን ህዝብ በሰደበው አለምነው መኮንን ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳው ቀጥሏል (Photos and video)

 1. Mieraf Ahadu

  February 25, 2014 at 3:02 AM

  የካቲት 16/2006 ዓ.ም አንድነትና መኢአድ የጠሩት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ በድል ተጠናቀቀ፡፡ የህዝብ ጠላቶች ሲሸሸጉና ሲደበቁ መስተዋሉን ከቦታው የሚመጡ መረጃዎች በመጠቆም ላይ ይገኛሉ፡፡ ብአዴን ሰርጎገብ ደጋፊዎቹን አሰማርቶ ሰልፉን ለማወክ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በመጠበቅ ፖሊሶች ያሳዩት ቅንነት ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ድምጼን ተቀማሁ ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ በነበረው ህዝብ ላይ የጥይት እሩምታ ያዘነበው ፖሊስ ዛሬ ተለውጦና የህዝብ አለኝታነቱን አስመስክሮ በመታየቱ የሰላማዊው ሰልፍ እድምተኛ ፖሊስ የኛነው የሚል የባለቤትነት ማዕረግ ሰጥቶታል፡፡ ለነገሩ አቶ አለምነው መኮንን የተሳደቡት መላወን አማራ ነው፡፡ ከመላው አማራ ህዝብ ደግሞ የፖሊስ ሰራዊት አባላቶች ይገኙበታል፡፡ ሰልፉ ድምቀት እንዲኖረውና በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ያስቻለው የሰውየው ስድብ በግለሰብ ዙሪያ ያጠነጠነ ባለመሆኑነው፡፡ እንደ ባህርዳር የፖሊስ ሰራዊት አባላት ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል የህዝብ አጋርነቱን እንዲያሳይ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ ከተነሱ መፈክሮች ውስጥ
  • መተማ የኛ ነው
  • ቋራ ይኛ ነው
  • ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ
  • አቶ አለምነው መኮነነ ለፍርድ ይቅረብ
  • የጎንደርን ግዛት ለሱዳኖች ለመስጠት የሚደረገው እንቅስቃሴ ይቁም
  • በሃገራችን በነጻነት እንኑር
  • ስደት ይብቃ
  • ብአዴን የአማራን ህዝብ አይወክልም የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

 2. ግፋየሁ

  March 6, 2014 at 6:31 AM

  አለምነው የ አገር ሻጭኦች ተላላኪ ነው
  ሞት ይፈረድበት
  ወገን ተባበር አንድ ሁን