የናዝሬት ህዝብ ለመለስ ዜናዊ ስላላለቀሰ… ውሃ ተከለከለ

(EMF) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ፤ የየከተማ ህዝብ በውድም ሆነ በግድ ለቅሶ እንዲወጣ መደረጉ የሚታወስ ነው። ሆኖም አንዳንድ ከተሞች ለቅሶውን በኢቲቪ ከማየት ውጪ በአደባባይ ወጥተው ደረት ሲመቱ አልታዩም። ከነዚያ ከተሞች አንዱ ናዝሬት (አዳማ) ከተማ ነው። የኢህ አዴግ ደጋፊዎች ባሉባቸው ከተሞች ህዝቡ (ከላይ እንደገለጽነው) በግድም ይሁን በውድ ወጥቷል።

አዳማ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ፤ የኦህዴድ ባለስልጣናት መቀመጫ ናት። ይህም ሆኖ ግን የናዝሬት ህዝብ ሙሾ ለማውረድ አደባባይ አልወጣም። በዚህም ምክንያት በባለፈው ምርጫ አሸንፏል ተሎ አዲስ የተሾመው የከተማው ከንቲባ አቶ አለማየሁ ከስልጣኑ እንዲነሳ ተደርጓል። በምትኩም ሌሎች አዲስ ተሿሚዎች ከተማውን እያስተዳደሩ መሆኑን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ. የደረሰው ዘገባ ያረዳል። ኢ.ኤም.ኤፍ. ወደ ከንቲባው ቢሮ ስልክ ደውሎ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ አቶ አለማየሁ የህክምና ፈቃድ ተሰጥቷቸው እረፍት ላይ ናቸው ተብሏል።

የህወሃት ሰዎች የበቀል እርምጃ የወሰዱት በናዝሬት/አዳማ ከተማ ከንቲባ ላይ ብቻ አይደለም። ህዝቡም ላይ ሌላ የበቀል እርምጃ እየወሰዱበት ይገኛሉ። ካለፈው የመለስ ዜናዊ ቀብር በኋላ፤ የናዝሬት ነዋሪዎች ውሃ እንዲያጡ ነው የተደረገው። አሁን አስራ አምስት ቀናትን አስቆጥረዋል። በመጀመሪያ የተሰጣቸው ምክንያት “መስመሩ ስለተበላሸ ነው፤ ይጠገናል።” የሚል ነበር። አሁን ግን አስራ አምስት ቀናት አለፉ። ህዝቡ በዝናብ ውሃ ነው እየተጠቀመ ያለው። ለመጠጥም ሆነ ለማንኛውም ጉዳይ ከዝናብ ውሃ በስተቀር ምንም አማራጭ አልተገኘም። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ፤ “በርግጥ ሌላ የበቀል ነገር ካልሆነ በስተቀር፤ የተበላሸን የውሃ መስመር መጠገን 15 ቀናት ይፈጃል ወይ?” እያሉ ነው።

የከተማው ከንቲባ ጭምር የተነሳበት፤ በኦህዴድ/ኢህአዴግ የሚተዳደረው የናዝሬት ህዝብ የመረረ ችግር ላይ ይገኛል። በአዲሱም አመት ምንም የተገኘ ለውጥ የለም። የዝናቡ ወቅት ሲያበቃ፤ ሁኔታው በምን አይነት መንገድ ይቀጥላል? ደግሞስ የከተማው ከንቲባ በቢሮው ከሌለ ናዝሬትን ማን እያተዳደራት ነው? ከሁሉም በላይ ግን ውሃ መች ይመጣል?” የሚሉት ጉዳዮች የናዝሬት ህዝብ  ጥያቄዎች ሆነው ይቆያሉ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 14, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.