የኃየሎም አርአያ አሟሟት… እና በጀሚል ያሲን ላይ የተሰጠ የሞት ብይን [ክፍል ሁለት]

(በዳዊት ከበደ ወየሳ – አትላንታ)

አንዳንድ ወዳጆቻችን ባለፈው ሰሞን ባወጣሁት የኃየሎም ግድያ ዙሪያ ቅሬታቸውን ገልጸውልኛል። ሆኖም በኔ ውስጥ ያለውና እነሱ የሚሉት እውነት አይገናኝም። ለነገሩ ብዙዎቹ ዘገባዎች አገር ቤት እያለሁ ያወጣኋቸው ናቸው። ይሄንን ጽሁፍ ለየት የሚያደርገው ዝርዝር ትንታኔ ውስጥ በመግባቴ ነው። አሁንም ቢሆን በኔ እምነት ነገሮችን በመሸፋፈን የምንሄድበት መንገድ ሌሎች እውነቶችን እንዳንመለክት ያደርገናል።

ምንም እንኳን ጀሚል ያሲን ግድያውን ቢፈጽምም፤ የተደረገበትን ኢሰብአዊ ተግባር አልደግፍም። ለምሳሌ ንብረቶቹ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በወያኔ ባለስልጣናት ተመዝብሯል። እና የፈለግነውን ያህል ኃየሎምን ብንወደውና ጀሚልን ብንጠላው ቢያንስ ወያኔ ያደረገውን ግፍ በመደበቅ የምንሄድበት መንገድ ማንን እንደሚጠቅም አይገባኝም። እኔም ብሆን ይህንን ጉዳይ እንደገና ለማንሳት የተገደድኩት… ይህ የጀሚል እና የኃየሎም  ጉዳይ ነፍስ ተሰጥቶት የህዝቡ መነጋገሪያ በመሆኑ ነው እንጂ፤ ጉዳዩ ከጀሚል ጋር እንደሞተ ከኔም ጋር ሊሞት ይችል ነበር። ሆኖም የኃየሎም አሟሟት ሲነሳ፤ ሻዕቢያን እያገዘፉ… የወያኔንም ግፍ እየደበቁ መሄዱ በኔ እምነት የትም የሚያደርስ አይደለም።

ስለሆነም በዚህ እኔ በምጽፈው ታሪክ ምክንያት ልዩነት ሊኖረን ይችላል። ይህ ግን በመካከላችን እንደመሰረታዊ  ችግርና ልዩነት መቆጠር የለበትም። የማውቀውን እውነት በመናገር የወያኔን የተደበቀ ግፍ በመጻፌ የሚቀየሙኝ ካሉ ግን ከአቅሜ በላይ በመሆኑ፤ እኔ እየወደድኩ እነሱ ሊጠሉኝ ይችላሉ። እዚያ ላይ ምንም ቁጥጥር የለኝም።

ቀሪውን ታሪክ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኃየሎም አርአያ አሟሟት… እና በጀሚል ያሲን ላይ የተሰጠ የሞት ብይን [ክፍል ሁለት]

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 14, 2011. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.