የቶሮንቶና የነቀምት ግንባር (ተክለሚካኤል አበበ)

የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤

1-      “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡ አንደኛው መስመር በአራት ኪሎና በፒያሳ አድርጎ፤ ወደ አዲስ አበባ መስተዳድር ጽ/ቤት ያመራል፡፡ ሁለተኛው አማራጭ በአራት ኪሎ ተጉዞ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አልፎ መስቀል አደባባይ ያበቃል፡፡ ሶስተኛው አማራጭ፤ በአራት ኪሎ ፒያሳ፤ ቸርችልን ይዞ ድል ሀውልት ጋር ያበቃል ነበር የሚለው፡፡ ከላይ እንደተመለከታችሁት፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር፤ ሶስቱም አማራጮች አልተመቹትም፡፡ የተመረጡት መስመሮች በርካታ ትምህርት ቤቶች የትምህርትና የመንግስት ተቋማት ስለሚገኙበት፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ግንባታ ያለባቸው መንገዶች ስለሆኑ፤ እንዲሁም በእለቱ የህዳሴው ግድብ ግንባታን የተመለከቱ ዝግጅቶች ስላሉ፤ መስተዳድሩ ሰልፉን ሳይፈቀድ ቀረ፡፡  Continue Reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 10, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የቶሮንቶና የነቀምት ግንባር (ተክለሚካኤል አበበ)

  1. Samson

    April 10, 2014 at 2:32 AM

    The only option that weyane has is leaving the country and escape to either hell or Mars. God bless Unity Party for dumping weyane