የታሰሩት የሰማያዊ አመራሮችና አባላት በደል እየደረሰባቸው ነው

(EMF) ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ ፓርቲ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅሥቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ አመራሮችና አባላት በእስር ቤት ውስጥ መሆናቸው ይታወቃል። እነዚህ በቅስቀሳው ወቅት ፖሊስ በህገ ወጥ መንገድ ያሰራቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እስር ቤት ውስጥ በደል እየደረሰባቸው መሆኑንም ተናግረዋል። ዮናታን ተስፋዬ ይህን በተመለከተ እንዲህ ብሏል።

የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች

የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች


በየካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት አባላትና አመራሮች ትናንት ምግብ እንዳይገባላቸው በመከልከሉ ጾማቸውን አድረዋል፡፡ በተመሳሳይ በቤተሰብና በአባላት እንዳይጠየቁም እየተከለከሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከሌሎች እስረኞች በተለየ በር በጊዜ እንደሚዘጋባቸው፣ እንዳይጠየቁ እንደተከለከሉና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸውመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ እየተበደሉ መሆኑን ለፖሊሶች በሚናገሩበት ወቅትም ‹‹እኛ ምን እናድርጋችሁ! ታዘን ነው! እናንተን ያሰራችሁ ሌላ አካል ነው፡፡ እኛ አይደለንም!›› የሚል መልስ እደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 29, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የታሰሩት የሰማያዊ አመራሮችና አባላት በደል እየደረሰባቸው ነው

 1. andnet berhane

  April 29, 2014 at 12:13 PM

  ይህን ጽንፈኛ ወንበዴ ወጣቱን ለማንኮላሸት የሚያደርገው ጥረት በብዙ መንገድ ጥሯር እንዲሁም በሆድ የተጋዙ ጥቂት የወጣቱን ስም የሚያጎድፈ ሕሊናቸውን የሸጡ እንድነብር ተናዳፊ ወጣት ሴቶችን ያባቶችን ጀብዱነት አንግበው የተነሱ የጊዚያችን ወጣት ጀግኖች ለምግብ ሳይሆን ትግላቸው ለመብት ለነጻነት በመሆኑ የወያነን(ኢሓዴግ)የራሱን መቃብር እየቆፈረ ለመሆኑ እሚታይ ምልክት ነው ጠላትነታቸውን አስመስክረዋል ለዚህም በቁም እያለን አንሞትም ለነጻነትና ለሃገራችን ክብርና ልእልና በጽናት መቆማቸውን የጀመሩትን ትግል ከግብ እንደሚያደርሱት የሚያሳይ ትንቢት ሳይሆን እውንነቱን በተደጋጋሚ አሳይተዋል በዚህም በሰረት ይህን አገዛዝ ማስወገድ የሁሉም ዜጎች በመሆኑ በእስር ያሉትን ወጣት ታጋዮቻችንን በነቂስ በመውጣት ማስፈታት ይጠበቅብናል
  እየጠፋን ልንኖር
  ሀገር አለን እያልን ታሪክ ያከበራት
  ህዝብ አለን እያልን በደም የገነቧት
  ለዘመናት የኖርን ብሄሮች ከበዋት
  በጭቁን መስዋእት ሃገር የሚሸጧት
  ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር
  መናገር ተነፍገን መኖር ተበታትነን
  በስራት በስደት መብታችን አጥተን
  ወገኔ ተባበር በጽናት ባንድነት
  ይወገድ ይህን ስራዓት ተቀዳጅ ነጻነት
  ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር
  ላለፈው ሁለት ዘመን ያየኸው መከራ
  ቤትክን ሲያፈርስ እርሻህን ሲቀማ
  ድበርክን ሲያስደፍር አያት አባት ሲያደማ
  ዝምታው ምንይሆን ምነው ስታቅማማ
  ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር
  በመንደር ተደራጅ ፍራቻው ይወገድ
  በትር ምሳር አንግት ጠላትህ ይታረድ
  ሞት ለማይቀር ታፍነህ ከምትወድቅ
  አንገቱን ቀንጥሰው ጠላትነ ይወቅ
  ታድያ እስከመቼ እየጠፋን ልንኖር
  ዓለም የሚሰማው ጥቃት ስትሰነዝር
  አንተም እንድነሱ ጡንቻህን ስትገትር
  በሰላም ለመጣል ተባብረህ ሰልፍ ውጣ
  እደ ዩክሬን ትግል እንደ ታይላድ ቅጣ
  ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
  ፈራ ተባ አትበል ቆርጠህ ተነሳ
  ዛሬውን አታስብ ነገንም አታውሳ
  ባገርህ ባንተላይ የተነሳ ጠላት
  ማንነትክን ክዶ ሲሰነዘ ጥቃት
  ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
  ቀደምት አባቶችህ የተውልህ ብቃት
  ጋሻው ጦሩ ጎራዴ ከሰገባው አውጣት
  እንዲማር ወያኔ ለዘመናት ቅጣት
  አባረህ አውጣው ይህን ያገር ጥፋት
  ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
  ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወጣት አዛውንቱ
  ያባት የናት ሃገር ድንበሯን ሲገፏት
  ሃገርና ክብር አንተነት በድፍረት
  አዋርደው ሲሸጡህ ለአረብ ባርነት
  ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር
  ወያኔ ጥጋቡ ቦንድ ገዢ ሲያጣ
  ሳአኡዲን ተስማማ ኢትዮጵያዊ ይውጣ
  አዋርደው አራክሰው እንደንሰሳ ገለው
  ሰቶችን በወሲብ እንድውሻ ሰረው
  ታድያ እስከመቼ ነው እየጠፋን ልንኖር
  አባት የሌለው ቤት ገቢው የበዛበት
  ሙስና ገነን ዘራፊው ምንገዶት
  ለህዝብ ያልቆመ ለግሉ ተጠምዶ
  መንግስት ባይ ለማኝ የሚኖር ተዋርዶ
  ታድያ እስከመቼነው እየጠፋን ልንኖር