የተፈቀረው ቴዲ አፍሮ ብቻ አይደለም

(ግርማ ደገፋ ገዳ)
እንግዲህ ቴዲ አፍሮ የፈለገውን ቢያፈቅር ወይም በፈለገውና ባልፈለገው ቢፈቀር የኛ ጉዳይ አይደለም። ‘ቴዲ አፍሮ የኛ ነው’ ለሚሉትም ‘ተስፋቁረጡ!’ ማለት ጥሩ ምክር ሊሆን አይችልም። አንድ በሩቅ የማውቃት ወጣት ሶማሌ አለች። ከወደ ደቡብ ሶማሊያ እና… ቆንጆናት።ኢትዮጵያዊ በገጠማት ቁጥር ኃይለኛ ስልኳን ላጥ ታደርግና የቴዲ አፍሮን ዘፈን ታሰማለች። ‘ምን እንደሚል አላውቅም፤ግንዘፈኑንምእሱንምእወዳቸዋለሁ’ ትላለች። ‘ደሞ ባንቺ የተነሳ ሞቃዲሾን እና አዲስ አበባን በፌዴረሽን ወይም በኮንፌዴረሽን ስለመቀላቀል እንዳይዘፍንልንና ዳግምእስር እንዳይገባ’ እላለሁ በሆዴ። ዳህላክና ኢየሩሳሌም ከደረሳቸው ቀጣይዋ ሞቃዲሾ የምትሆን እየመሰለኝ።
Click here to read the article
‘ሞቃዲሾ ያለሽው
ልቤን የወሰድሽው
ታንኮች እንዳይግጡሽ
እንደው ምን ልሁንልሽ?
ድንበሩ የቱጋ ነው
ድንበር የሚሉት፣
ልባችን ተጣብቆ እያዩት።
ኧረ የቲኤፍጂ ያለህ
የኢሕአዴግ መጫወቻ፤
ታንኩን ውሰድና መንገድ ስጠን
ለፍቅራችን ብቻ
ጃህ! ጃህ! ሞቃዲሾሾሾሾ!!’

‘እነ ታማኝ በየነ አሥመራ መጡ’ ሲባልደስታችንንመቆጣጠርአልቻልንም።ሰፈራችንአሥመራዓይነብርሃንሆስፒታልአጠገብነበር።ከሰፈራችንወደአሥመራአብዮትአደባባይለመሄድጉዞጀመርን።ልቅምብለንነውየወጣነው።በግራበኩልሲኒማጣናን፣በቀኝበኩልየአስመራቤተመንግሥትንየግንብአጥርአሻግረንእየቃኘን፣ባይስሮይደረስን።በዚያንጊዜምርጥምርጥየአሥመራፎቶቤቶችየሚገኙትባይስሮነበር።ፎቶዙላናፎቶሐረርትዝይሉኛል።እኛምለማስታወሻይሆንዘንድከፎቶዙላገብተንቆንጆፎቶተነሳን።አሁንድረስበእጄአለ።

ወደግራወይምወደቀኝካልታጠፉየባይስሮይመንገድካቴድራል’ጋሲደርስያልቃል።ወደቀኝታጥፈን፣የትራፊክመብራቱ’ጋስንደርስእንደገናወደግራታጠፍንናበካቴድራልሥርአድርገንኮሚሽታቶንተያያዝነው።የኮሚሽታቶየዛሬውሓርነትጎዳናመጨረሻምአብዮትአደባባይይጨምራል።በዓሉግርማየተረከላቸውእነዚያዘምባባዎችያንጊዜምነበሩ።ሁሌምውብናቸው።እነሱንአንዴያያቸውሰውመቼምሊረሳቸውአይችልም።አሥመራያንጊዜምበጣምንጹህናት።እታገኝናውሾቿንምለማየትእድልገጥሞኛል።

አሥመራአደባባይተሰርቶአላለቀም፤ግንጢምብሎነበር።ሰልፋችንንይዘንእየተፈተሽንገባን።ታማኝእየተውረገረገግልብጥብሎለወጣውየሙዚቃአፍቃሪአሥመራላይታይቶየማይታወቀውንየማስተዋወቅእናየማዝናናትስልቱንሲነሰንሰውአደባባዩሙሉአፉንከፍቶቀረ።በብሔራዊደረጃተዋቅሮ፣ቁሳቁሱንናባለሙያዎቹንሰብስቦሕዝብንበነጻለማዝናናትከአዲስአበባየመጣሁሉአቀፍየሙዚቃቡድንአሥመራላይትርዒትሲያደረግ፣የመጀመሪያላይሆንይችላል፤እነታማኝታዋቂመሆንከጀመሩበኋላግንያየመጀመሪያነበር።የአሥመራወጣቶችጥሎባቸውየመሃልሃገርዘፈንናዘፋኞችንይወዳሉ።የሺመቤትዱባለ (ትመስለኛለች)

ባሕላዊዘፈኗንስታቀልጠውአደባባዩበደስታተናወጠ።የአስመራወጣቶችጥሎባቸውየመሃልሃገርዘፈንናዘፋኞችንይወዳሉ።ንዋይደበበወደማይክራፎኑብቅሲል፤ሁሉምአበደ።የአስመራወጣቶችጥሎባቸውየመሃልሃገርዘፈንናዘፋኞችንይወዳሉ።በተለይአንዲትአከለስንኩልየነበረችወጣትንዋይንአለቀውምአለች።እያስደገመችውናአብራውእየደነሰችተመልካቹንአንጫጩት።የአሥመራወጣትለመጨረሻጊዜከመሃልኢትዮጵያየመጣንአገርአቀፍየሙዚቃባንድለመመልከትእድልየገጠመውበዚያንጊዜነበር።ከዚያበኋላያለውንባላውቀውአይፈረደብኝም።
የአውሮፓውዘፋኝMauroየሚጫወተውየ1987ቱ፣
“ቦኖሴራ
ቦኖሴራሲኞሪና
ቦኖሴራ
ሲኞሪናቻዎ! ቻዎ!”ከወደአሥመራዘግየትብሎገብቶነውመሰለኝእንደጉድይደመጥነበር።

በMauroዘፈንበየዳንስናመጠጥቤቱየሚውረገረግሞልቷል።ከMauroእኩልእጁንወሰሰማይሰቅሎ “In the moonlight after midnight….” የሚለውተቆጥሮአያልቅም።አሥመራውስጥ፣የኪሮስአለማየሁ “አንጉአይፍስስ” ታዋቂነበር።የጸሐዬዮሃንስ “ተባለእንዴ” ተወዳጅነበር።አድማጩሌላትርጉምሰጥቶትየነበረውየታረቀተስፋሂወትዘፈንበስፋትይኮሞኮምነበር።ሰውነተ─ቀጭንናጸጉረረጅምየሆኑትየአሥመራቆነጃጅቶችየመሃልሃገርወጣትላይዓይናቸውከተከሉ፤ አያነሱም።ከልብአፍቃሪናቆንጆዎችናቸው።ሌላውፋሽንልብስቀርቶየትምህርትቤትየደንብልብስእንኳያምርባቸዋል።የቀይባሕርሁለተኛደረጃተማሪዎችከላይቀይሹራብነበርየሚለብሱት።ያውምእዚያውአሥመራየተሰራ።የመሃልሃገርወጣትወንድንእያፈቀሩስለሚያደርጉትልዩልዩነገርበየጊዜውይወራል። ‘ተያይዘውወደሱዳንጠፉ’ምየዚያምድብአባልነበር።ግንየሚያፈቅሩትወንድ ‘ሰው’ ስለሆነእንጂ ‘ዘፋኝ’ ስለሆነአልነበረም።ዛሬምያየተለወጠአይመስለኝም።
በአንድየወረዳአስተዳደርጽ/ቤትውስጥየሚሰራአንድጓደኛነበረን።የአዲስአበባልጅነው።አሥመራዋናውፖስታቤትአጠገብከሚገኙሕንጻዎችከአንዱላይተከራይቶይኖርነበር።አልፎ፣አልፎእዚያውአካባቢካለውከታዋቂው‘አልባባር’ ሻይእንጠጣለን።አንድቀንቤቱስንሄድበጣምተከፍቶአገኘነው።እናምለምንእንደተከፋሳናውቅማዘንጀመርን።ብዙደቂቃቆይተንነበርስላስከፋውጉዳይየጠየቅነው።መልሱአሳዛኝነበር።ተዳብሎትይኖርየነበረውወጣት፣የባሕርኃይልአባልነበር።ምጽዋስትያዝካለቁትየባሕርኃይልአባላትአንዱሆኗል።የባሕርኃይሉአባልከጓደኛችንጋርየአፓርታማቸውንየወርክፍያእየተጋሩመኖርከጀመሩቅርብጊዜያቸውነበር።ለአጭርቀናትየሥራጉዳይነበርወደምጽዋያቀናው።ባማሩፍሬሞችየተዋቡትፎቶዎቹአሁንድረስትውስይሉኛል።እነዚያንፎቶዎችእያየንአዘንን።ባናውቀውምየምናውቀውያህልተሰማን።ጓደኛችንምየሟቹንንብረቶችለማእንደሚሰጥግራገብቶትነበር።የአዲስአበባልጅመሆኑንእንጂሌላጠለቅያለመረጃስለሌለውየወላጆቹንአድራሻከወዴትአግኝቶመርዶውንእንዴትእንደሚነግራቸው አስጨንቆታል።በዚያንጊዜየወላጆቹንሆነየዘመዶቹንአድራሻየሚያውቅሰውብቻነበርከጭንቅሊገላግለውየሚችለውእንጂእኛአልነበርንም።አንድሰውወጥቶለዘላለምስለመቅረቱወላጆችሊያውቁአለመቻላቸውሲታሰበን፣በጣምአስከፋን።ምንምማድረግስላልቻልልናማድረግምስለማንችል፣የአሥመራምሽትምበጊዜጭርየማለትሁኔታአስፈሪበመሆኑ፣የማጽናኛቃላትን አስረክበነውፎቶዎቹከፊታችንአልጠፋእያሉወደሰፈራችንአቀናን።

ከተወሰኑቀናትበኋላጽ/ቤቱገብተንአናገርነው።ንብረቱንሁሉፍቅረኛውወደአዲስአበባወስዳለች።ቤተሰቡመርዶውንምበዚያውእንደሚሰሙነገረን። ‘የአሥመራአፍቃሪዎችእንዲያናቸው’ አለን።ደስአለን።በደንብየምታውቀውአንዲትወጣትነበረችውለካ! …..ስታፈቅረውም “ዘፋኝነው፤ወይምበሚቀጥለውዓመትነጠላክሊፕይለቃል፤
‘እምባይሶራሆቴል፣ጉርጉሱምየባሕርዳርቻ’
ለማንምክፍትናችሁምነውለኔብቻ’ እያለያቀነቅናል” ብላአልነበረም።

ከዚያችውብከተማብዙውብየፍቅርታሪኮችአሉ።
ከቀይመስቀልዋናውጽ/ቤትአጠገብሼልነዳጅማደያአለ።ከሼልፊትለፊትበጣሊያንጊዜሲኒማሮማ፤ከጣሊያንበኋላሲኒማአዲስአበባነበር።ሥሩየትራፊክመብራትአለ።ከሲኒማቤቱጀርባካሉየሚያማምሩቤቶችመካከልአንድየሙዚቃት/ቤትነበር።አንድየሐረርጌልጅየሆነጓደኛዬበትርፍጊዜውጊታርመምታትይማርነበር።አንድቀንተያይዘንሄድን።ለነገሩጊታርምባይሆንአንድየሙዚቃመሳሪያመሰልጠንእንዳለብኝሁሌምአስብነበር።የሙዚቃማሰልጠኛውንከማየትናጓደኛዬንከማበረታታትባሻገርያለኝየጊዜሁኔታሥልጠናውንእንድጀምርአላደረገኝምናቅርእያለኝሳልጀምረውበዚያውተውኩት።

ያጓደኛዬአንዲትልጅተዋወቀ።ደሞሰፈሯእኛየምንኖርበትአጠገብነው።የሃገርፍቅርማኅበርኃላፊዎችከነበሩትመካከል፣አሁንስማቸውንየዘነጋዋቸውአንድሰውይኖሩበትከነበረውሕንጻላይነበርቤተሰቦቿየሚኖሩት።በጣምቀይናአፍላወጣትናት።ቅላቷወደክልስነትያደላል።የሁለተኛደረጃትምህርቷንገና አልጨረሰችም።በፍቅርለማበድጊዜአልፈጀባትም።ብንአለች።በጣምራሷንትጠብቅየነበረችአፍላ፣ራሷንረሳች።ልብሷንእንደነገሩለብሳያልጠበተረጸጉራንእንደእብድከወዲያወዲህእየነሰነችው ‘እከሌንፈልጌነው’ ስትለንሮጠንከሽንትቤትምቢሆንጎትተንእናመጣዋለን።እንዲያካላደረግንከደጅአትሄድም።እንዲያውምትሰድበናለች።መጀመሪያሰሞንእሷታፍረንነበር።ከትንሽጊዜበኋላእኛማፈርጀመርን። “እኔባፈቀርኩትእናንተምንአገባችሁ” ትለናለች።ተደናግጠንጊዜሳንፈጅጓደኛችንንፍለጋእንራወጣለን።በጊታሩቦታእሷንእንዲያቅፍአደረግችውናበትርፍጊዜውየሚሰለጥነውንጊታርትቶእሷንማቀፍጀመረ።ጓደኞዬንእስክለየውድረስእንደዚያነበር።

በአንድወቅትሐረርጌይህንጓደኛዬንፍለጋሄድኩኝ።በወላጆቹየድሮአድራሻውፈልጌውአገኘሁት።ሚስትአግብቷል።የአንድልጅአባትምሆኗል።የሰርጉንአልበምአውጥቶአሳየኝ።በሐረርጌኦሮሞየአለባበስባሕልሽርብሎያከናወነውንሰርግአየሁት።ሙሉነጭልብስለብሷል።በሆዱአቅጣጫጩቤሻጥአድርጓል።አፍሮጸጉሩላይቀይአበባሰክቷል።አልበሙንአድንቄስሰጠው “የመጨረሻፎቶሥርያለውንፎቶአየኸው?” አለኝ።በእውነትአላየውም።መልሴንምሳይጠብቅእራሱአውጥቶአሳየኝ።ያቺየሰፈራችንቆንጅዬ ነበረች።

“አሁንምትገናኛላችሁ?” ጠየኩት።
“ከሞተሰውጋርመገናኘትቢቻልእንዴትጥሩነበር” አለኝ።
በጣምአዘንኩኝ።
“ቪዛባገኝ…..” ብሎ ሲጀምር፣
“ምን ልትሆን?” አልኩት። መቸኮል አልነበረብኝም።
“አሥመራሄጄከመቃብሯላይየጽጌረዳአበባአስቀምጥነበር”
‘እሷ’ጋ ሄዳለሁ’ የሚል መስሎኝ ነበር የተቻኮልኩት።
አሥመራካሉትመቃብሮችሶስቱንአውቃለሁ።የካቶሊክ፣ምጽዋመውጫአጠገብያሉትንየብሪትሽሴሜተሪእናቤትገርጊሽያለውን።አሥመራዙ፣ከብሪትሽሴሜተሪአጠገብነውያለ። ቤትገርጊሽማለትጎርጊስቤተክርስቲያንማለትነው።የጎርጊስቤተክርስትያንመቃብርከቤተክርስትያኑብዙምሳይርቅከፍያለቦታላይያለው።ከፍካለውየመቃብርሥፍራመጀመሪያየሚታየውየራስተስፋዬበራኺመቃብርነው።በጥሩሁኔበእምነበረድየተሠራነው።አጠገቡተቀምጫለሁ።አሁንረሳውትእንጂመችተወልደውመችእንዳረፍፉከመቃብራቸውላይያነበበኩትእስከቅርብጊዜድረስአልተረሳኝምነበር።ፎቷቸውምጭምር።ከዚያመቃብርላይሆኖወደምጽዋአቅጣጫያለውንተያያዥተራራናሸለቆማየትያስደስታል።የብሪትሽሴሜተሪ፣የቤትገርጊሽናየአሥመራዙአካባቢዎችለፍቅርየሚመቹናቸው።ረጃጅምየባሕርዛፎችየሚታዩባቸውናንጹህናቸው።

መቃብሯከብሪትሽ ሴሜተሪ እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ። ከዚያ ለመቀበር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች መሞት ያስፈልጋል።
ጸሐፊውን በዚህ ኢሜይል ሊያገኙት ይችላሉ። girmariver@gmail.com

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 24, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.