የተቃውሞ ሰልፉ በድምቀት ተከናወነ (በርካታ ፎቶዎች ይዘናል)

EMF – ዛሬ ግንቦት 25፣ 2013 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ ብዙ ሺህ ህዝብ ተገኝቶ ነበር። በአሁኑ ጊዜም ለስድስት ሰአታት የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም ተጀምሮ፤ በድምቀት ተከናውኖ… በሰላም ተጠናቋል። ቁጥሩ እጅግ የበዛ ህዝብ በወጣበት በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “አንለያይም! አንለያይም” የሚሉ እና “መማር ያስከብራል፣ አገርን ያኮራል” የሚለውን መዝሙር ህዝቡ በጋር ሲዘምር ነበር። ከዚህም በተጨማሪ “የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ ይመለስ” የሚሉትና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

ከነዚህ መፈክሮች መካከል…
መንግስት ህገመንግስቱን እና ዜጎችን ያክብር!
የህሊና እስረኞች ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ይፈታ!
ነፃነት እና ፍትህ እንፈልጋለን!
ሁሉም የመንግስት ሌቦች ለፍርድ ይቅረቡ!
የመንግስትን በሀይማኖት ጣልቃ ገብነት እናወግዛለን!

የሚሉት በጉልህ ይታዩ የነበሩት ናቸው። የተቃውሞ ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ የነበረ ሲሆን፤ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ፤ ህጋዊ ፍቃድ እየተከለከለ ላለፉት አመታት በራሱ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ነበር። አሁን ግን ከአመታት በኋላ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የታየበት ሰልፍ ነበር። ብዙዎች፤ “ተነፈስን! ወጣልን!” ሲሉ ተሰምቷል። ሌሎች ደግሞ “በህዝባችን ኮራን!” የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

የነበረውን እንቅስቃሴ በቃላት ከመግለጽ ይልቅ በፎቶ አስደግፈን ማሳየቱ ስለሚሻል፤ የተቃውሞ ሰልፉን የሚያሳዩ ከ35 ፎቶዎች በላይ ለህትመት አብቅተናል።

Also view flickr picture.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.