የብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ምስክርነት

ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ 33ኛውን ጉባኤ በዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ባካሄደበት ውቅት የቦርድ ሊቀመንበሩ አባ ወልደትንሳኤን ያለ አግባብ በሀሰት ወንጀል ከስው እንደነበረ የሚታወቅ ነው። አባ ወልደትንሳኤም ለስድስት ወራት ከሎስ አንጀለስ ዋሽንግተን ዲሲ ድረስ በመላለስ ጉዱዩን ከተከታተሉ በኋላ እውነት በሆነው በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደጋፊነት ኦክቶበር 18 ቀን ፍርድ ቤቱ የሀስቱን ክስ ደምስሶ አባ ወልደትንሳኤን በነጻ አሰናብቷል። ስለሆነም በመላው ዓለም የሚያደርጉት ሐዋርያዊ የወንጌል አገልግሎት ስለሚቀጥል የቤተክርሲቲያን ልጆችን አስደስቷል። መንፈሳዊ አገልግሎት የፈተና ጉዞ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም እውነት ታፍና እንዳትቀር በጸሎት የተጋችሁ ምእመናን፣ ሀሰትን በማጋለጥ የተጋችሁ ጋዜጠኞች፣ የህግ ባለሙያዎች እንዲሁም ገንዘባችሁንና ጉልበታችሁን መስዋዕት ያደረጋችሁ በሙሉ ድካማችሁን አይቶ እግዚአብሑር እውነተኛ ፍርድ ሰለሰጠ ክብርና ምስጋና ይገባዋል። በዚህ አጋጣሚ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አባ ወልደትንሳኤን አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ በጽሑፍ የሰጡትን ምስክርነት ከዚህ ጽሁፍ ጋር አያይዤ በሚቀጥለው ገጽ አቅርቤዋለሁ።

የእግዚአብሔር ቃል የዋኖቻችሁን ቃል አስቡ ብሎ እንዳስተማረን እኛ የቤተክርስቲያን ልጆች የቅዱስ አባታችን መልእክት በስደተኛዋ ቤተክርሲቲያን የአገልግሎት ጉዞ ላይ የተከሰተውን ጠባሳ የታሪክ ምእራፍ ይዝጋል ብለን እናምናለን። ለቅዱስ አባታችንም ረጅም እድሜና ጤና እንዲሰጥልን እንመኛለን። READ FULL AMHARIC MESSAGE IN PDF>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 28, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.