የባህር ዳር ህዝብ ሆ ብሎ ወጣ!! ህዝቡ “ከባዶ ጭንቅላት… ባዶ እግር ይሻላል፡፡” አለ! (Video added)

(ዜና ጥንቅር ዳዊት ከበደ ወየሳ)
የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ የብአዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በመናቅ እና በመሳደብ የተናገሩት ቃል ነው:: አማራውን… “በባዶ እግሩ እየሄደ ሌላውን ይንቃል” ካሉ በኋላ ለአማራው የሚቆረቆሩትን ደግሞ “ለሃጫቸውን…” እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ ለመጻፍ የምንጸየፋቸውን ቃላቶች ጭምር በመጠቀም አሽሙር አይሉት ስድብ ሰንዝረዋል:: ነገሩ ከአንድ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ወይም እመራለሁ ከሚል ሰው የሚጠበቅ ባለመሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፣ አናዷልም::

በመሆኑም የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲዎች በጥምረት ሆነው በባህር ዳር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ:: ምክትሉ ሊቀመንበሩ ከሰልፉ በፊት እንደበፊቱ በትእቢት ተወጥረው ሳይሆን ረጋ ብለው ምን ለማለት እንደፈለጉ ቢያስረዱም ህዝቡ ግን ተቃውሞውን ቀጠለበት:: ለነገሩ በዚህ አጋጣሚ ሌሎች የሚነሱ የህዝብ ብሶቶች እንዳይነሱ በመስጋት የክልሉ አስተዳዳሪዎች አንዳንድ እንቅፋቶችን ለመፍጠር መሞከራቸው አልቀረም:: እርግጥ ነው… ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ሲዘጋጁ ብዙ እክል ገጥሟቸው ነበር:: ከተማ ውስጥ በራሪ ወረቀት መስጠት እና ቅስቀሳ ማድረግ ጭምር ተክልክለዋል:: ሆኖም ህዝቡ ራሱ ከልካዮቹን በመቃወሙ የፖሊሶቹ እገታ እና ጫና በረድ አለ:: ተቃዋሚዎቹ በባዶ እግር መሄድ ማለት ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት ቅስቀሳ ሲያደርጉም ሆነ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ… ጫማቸውን አውልቀው በባዶ እግራቸው ነበር የታዩት::

bahrdar demo13 2232014

ዛሬ እሁድ… እ.ኢ.አ የካቲት 16, 2006 ባህር ዳር ቀበሌ 12፣ ግሽ አባይ በሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ሰልፉ ሲጀመር የተለያዩ መፈክሮች እየተደመጡ ነው፡፡ በሰልፉ የፊት ረድፍ ላይ የፓርቲው ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግዛቸው፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እና ሌሎችም አመራሮች ከህዝቡ ጋር ሆነው ታይተዋል:: ከግሽ አባይ የተነሳው ሰልፈኛ ጉዞውን በባህር ዳር ጎዳናዎች ላይ ማድረግ ሲጀምር ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች ሰልፈኛውን ተቀላቅለዋል:: የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የያዙ ወጣቶች ከፊት ሆነው መፈክር በማሰማት ከተማዋን ከጠዋት እንቅልፏ አባነኗት:: የባህር ዳሩን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ፣ የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፊት በመምራት ላይ ይገኙ ነበር::
bahrdar demo7 2232014

ከባህር ዳር በደረሰን ዘገባ መሰረት… ህጻናት ልጆቻቸውን በጀርባቸው ያዘሉ፣ በዊልቼይር የሚሄዱ፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶች በአንድነት ሆነው በባህርዳር ከተማ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡
bahrdar demo9 2232014
ሰልፉ ከመጠናቀቁ በፊት ቁጥራቸው 15 ሺህ ያህል ሰዎች እንደነበሩ ነው ከስፍራው የተዘገበው:: በወቅቱ ከተያዙት መፈክሮች የተወሰኑት…
“የመሬት ቅርምቱ ያብቃ!”
“ህዝብን ከርስቱ ማፈናቀል ይቁም”
“ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም”
“የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነው ለፍርድ ይቅረቡ”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”
“ህዝብን እየሰደቡ መግዛት አይቻልም”
“ድል የህዝብ ነው”
“አቶ አለምነው የሰደቡት የአማራን ህዝብ ብቻ አይደለም”
“ብአዴን /ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልእልና የለውም”

ከስፍራው ሁኔታውን እየተከታተለ በቀጥታ ሲዘግብ የነበረው ነብዩ ሃይሉ እንደገለጸው ከሆነ… በሰልፉ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር ለሰልፈኛው ተለቆ ህዝቡ ንግግሩን በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ነው፡፡
“ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ”
“ነፃነታችን በእጃችን ነው”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፡፡”
“ብአዴን የአማራን ህዝብ ለመምራት የሞራል ልዕልና የለውም”
“መተማ የኛ ነው፣ ቋራ የኛ ነው” በሰልፉ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መሀከል ይገኝበታል፡፡ ሰልፉ በህዝብ እንደታጀበ ቀጥሏል፡፡

በመጨረሻም የየፓርቲዎቹ ተጠሪዎች ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል:: አቶ አበባው መሃሪ 1-አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ
2- ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆም
3-አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስበዋል፡፡
የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በንግግራቸው… አቶ አለምነው እንዲህ እንዲናገሩ ያደረገውን አምባገነን የኢህአዴግ ስርአት ለመቀየር እንስራ ብለዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ናቸው፡፡ ኢንጂነሩ የመግቢያ ንግግራቸውን የከፈቱት በዛሬው እለት ደስ ካሰኙን መፈክሮች “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” የሚለውን በማለት ነበር፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በንግግራቸው መጨረሻ ላይ አቶ አለምነው ይቅርታ ካልጠየቀና በህግ ፊት ካልቀረበ አንድነት በድጋሚ በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ አሳውቀዋል፡፡

አሁን ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም እንደወጣ፣ በሰላም ወደ ቤቱ እየተመለሰ ነው:: የሰላማዊ ሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ የህዝቡን ጨዋነትና የአመራሩን ብስለት ያሳያል:: እርግጥ ነው… ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም ወደቤቱ ቢያመራም… ባህር ዳር ላይ የተለኮሰው የመነቃቃት ስሜት ግን በቀላሉ የሚበርድ አይመስልም:: እኛም መልካሙን ሁሉ እየተመኘን ዘገባችንን እዚህ ላይ አጠናቀናል::


ምስጋና: ሙሉውን ዘገባ ለማድረግ የቻልነው በተለይ ነብዩ ሃይሉ፣ ዳዊት ሰለሞን እና እስከዳር አለሙ ሁኔታውን እየተከታተሉ ከሚያቀርቡት የፎቶ እና የጽሁፍ መረጃ ተነስተን ነው:: በመሆኑም በኢ.ኤም.ኤፍ እና በአንባቢዎቻችን ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 23, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

14 Responses to የባህር ዳር ህዝብ ሆ ብሎ ወጣ!! ህዝቡ “ከባዶ ጭንቅላት… ባዶ እግር ይሻላል፡፡” አለ! (Video added)

 1. teddy

  February 23, 2014 at 7:12 AM

  Just saw your Bahirdar report ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም ወደቤቱ ቢያመራም… ባህር ዳር ላይ የተለኮሰው የመነቃቃት ስሜት ግን በቀላሉ የሚበርድ አይመስልም::hahah keep on dreaming. I hate guys like you-dooms day callers.

 2. Robele Ababya

  February 23, 2014 at 7:30 AM

  It was with great Ethiopian pride and tears in my eyes that I watched the mammoth demonstration by the heroic residents of Bahr Dar. This massive demonstration marks the beginning of the end of the TPLF/EPRDF regime.
  Thank you my fellow Ethiopians residing in Bahr Dar. Thank you the distinguished patriotic leaders of the UDJP and AEUP for your exemplary collaboration in this noble undertaking to organize the inspiring demonstration jointly.

 3. Kibrom Alexive

  February 23, 2014 at 8:28 AM

  Waw..Oo….I am really tremendously happy. I have no words to express my feelings. As senior professional which I am now is acquired from my Amhara people who are walking on barefoot and let me to be educated to higher level. I am proud of being from a barefooted people of Ethiopia and Amhara. Empty skull is nothing while Barefooted walk forward is every thing. Thank you my hero people and EMF. I Could have been good if I were to participate barefooted with my people but not in homeland ;but, today,I am walking in my village barefooted to get involved from a distance.

 4. ሶሎሞን

  February 23, 2014 at 2:57 PM

  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!!ከአንድ ሽ ቃላት በላይ እውነቱን የሚናገር አባባል

 5. ጎንደሬው

  February 23, 2014 at 3:12 PM

  ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገውን የባህርዳርና አካባቢው ህዝብ ከልብ አመሰግናለሁ:: ህዝቡ የአማራው ም/ገዥ በተናገሩት ስድብ ተናዶ ተቃውሞውን ለማሰማት ወጣ እንጅ መኢአድንም ሆነ አንድነትን ለመደገፍ አይደለም:: እነዚህ ሁለት ድርጅቶች የሰሜን ሸዋ ድርጅቶች ናቸው:: እየታገሉ ያሉት ዴሞክራሲ ለማስፈን ሳይሆን የተነጠቁትን ስልጣን ለማስመለስ ነው:: አቶ አበባው ለምን እዚያ ድርጅት ውስጥ እንደተቀመጡ ሳስብ ይገርመኛል:: ያልተገነዘቡት ነገር ከርሳቸው ይልቅ በየትናንሽ ቦታ የተሸጎጡት ሰሜን ሸዋወች ተቀባይነት እንዳላቸው ነው:: ከርሳቸው ጀርባ የሚደረጉ ስብሰባወች አሉ:: ከሰሜን ሸዋ ውጪ የሆነ ሰው በምንም አይነት ሁኔታ ተአማኒነትና ተቀባይነት የለውም:: ጥበቃ ላይ የተሰማሩ ወይም ሂሳብ ክፍል የሚሰሩ ወይም ተላላኪና ረዳት ተብለው የተቀመጡት የሰሜን ሸዋ ሰዎች ዋናው ተግባራቸው ስለላ ነው:: እኒህን ሰዎች አቶ አበባው እንዲህ አድርጉ ብለው ሊያዝዟቸው አይችሉም:: ሰዎቹ አመራር የሚቀበሉት ከእስክሪኑ ጀርባ ከተቀመጠው ምርጥ ሰው ነው:: አጋጣሚውን እየተጠቀሙ የህዝብ ተቆርቋሪ መስለው የሚሰለፉት ለህዝብ ክብርና ፍቅር ስላላቸው አይደለም:: ፈሪ ስለሆኑ እራሳቸውን ችለው ብቻቸውን አይታገሉም:: ሌላው መስዋእት ሆኖ ለስልጣን እንዲያበቃቸው የአዞ እምባ ያነባሉ:: የነዚህን ሰዎች ምንነት ለማወቅ ጠጋ ብሎ ማየት ነው:: ያኔ እውነቱን ይረዳና ከነርሱ በእጅጉ ይርቃል:: እንደሽንፍላ ቢያጥቡት የማይጠራ ድርጅት መኢአድ ነው:: ለረጅም ጊዜ መጠቀሚያቸው ሆነናል:: ልንነቃ ይገባል:: ትግሬወችና ሸዋወች እየተፈራረቁ እንደመሳሪያ እንዲጠቀሙብን አንፍቀድ:: ለእውነተኛ ዴሞክራሲና ለለውጥ የሚታገል ሰው መደገፍ ያለበት ሰማያዊ ፓርቲንና ኢዴፓን ሊሆን ይገባል:: የራሳቸውን የስልጣን ኮርቻ በእኛ ላይ ለመጫን እኛኑ በመሳሪያነት ለመጠቀም እየሞከሩ እንደሆነ እንረዳ:: ከሰሜን ሸዋ የበቀሉ ሰዎችን በንጉስነት ተቀምጠው አይተናቸዋል:: በዋናነት ሲያሰቃዩና ሲገድሉ የነበረው ከሰሜን ሸዋ ውጭ የሆነውን አማራ ነበር:: በዚህ መሰረት ብዙ ግፍ አሳልፈናል:: አሁን ደግሞ ወያኔ በተራው በአማራነት ስም ከገዥወቻችን ጋር አዳብሎ መከራችንን እያበላን ነው:: መላው ኢትዮጵያዊ እኒህን የሰሜን ሸዋና የትግራይ ተቀናቃኝ ድርጅቶች እኩል መታገል ይኖርበታል:: አንዳቸው ከሌላቸው አያንሱም:: ሁሉም የህዝብ ጸር ናቸው:: ይህን መልእክት የማስተላልፈው ሰው ሁለቱንም በቅርብ ያየሁ ሰው ነኝ:: እኛ ከማንም የማናንስ ራሳችን ሀሳብ ማፍለቅም ሆነ መምራት እንደምንችል ማሳየት አለብን:: ሸዋወች በገዥነታቸው ጊዜ ወያኔም አሁን ስልጣን ላይ ሆኖ በሰበሰበው ሀብት ተደግፈው በአካላችንም ሆነ በህሊናችን እንዲያዝዙ መፍቀድ የለብንም:: እነዚህ ሁለት የተንኮል መናሀሪያወች ለማንም የማይሆኑ ስለሆነ እናርቃቸው::

 6. AleQa Biru

  February 23, 2014 at 4:25 PM

  ወይ ጉድ !!!

  በሕዝቡ ስሜት ይጫወቱበታል:: ፈጣሪ ይይላችሁ!!!

  ምስኪን ሕዝብ ጠንካራ መሪዎች ያገኘ መስሎት አብሮ ይነጉዳል:: ሙቀቱ ሲግል ሕዝቡን ሜዳ ላይ ትተው በአሉባልታና እና በእንካስላንቲያ እንደሚተበተቡ ማን በነገረው (በአስታወሰው)!!!

 7. ባሳምን መቸም

  February 23, 2014 at 7:18 PM

  አቶ ዓለምነህ መኮንን, ከጌቶችህ የታማኝነት የጉርሻ እንጎቻ አገኛለሁ ብለህ የራስህን እናትና አባት ወንደምና እህቶችንም ለሃጫም ማለትህ ,ወያኔንም ሳታሳዝን አልቀረህም::
  ለከተቢስ ውሻ መሆንህን ከማስመስከር ሌላ ,ምንም ያተረፍከው ነገር የለም ::ወያኔ መንጋጋው ውስጥ ለጊዜው አስቀምጦሃል አሁን ግን እነሱንም ስላገማሃቸው አንቅረው ይተፉሃል: ከዛ የማን ብሄር ሊያስጠጋህ ነው?

 8. ባሳምን መቸም

  February 23, 2014 at 7:34 PM

  የukraine ጀግና ልጆች ተስፋ ሳይቆርጡ የነበረውን የሩሲያ ተላላኪ አሸንጉሊት መሪ ደማቸውን ከፍለው አስወግደውታል, እናንተም የጎንደር ልጆች ይህንን ተባይ አስተዳደር ፈንቅላችሁ ማስወገድ የናንተ ፋንታ ነው; የወደፊት እድላችሁን የምትወስኑት እናንተ ስለሆናችሁ ,እነዚህን የትል መንጋ ባዶ ራስ ባለሥልጣን ነን ባዮች ጊዜያቸውን ማሳጠር አሁንም የማንም ሳይሆን የናንተ ጀግና ወጣቶች እጣ ነው::
  እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን

 9. በለው!

  February 23, 2014 at 11:16 PM

  “በሽግግር ወቅት የአማራ ብሄር የሚወክለው ስላልነበር የግድ ከዚያ ብሔርም ባይሆን “በአመለካከት” ከትጥቅ ትግል ጀምሮ አማራውን ያደራጀው ኢህአዴግ ስለነበር ብአዴን የተባለ ቡድን እንዲወክለው አድርገናል፡” አቶ መለስ ዜናዊ ከሊቀጠበብት መስፍን ወልደማርያም ጋር በነበራቸው ውይይት ከተናገሩት በቅርቡ በአውራአምባ ታይመስ ድረገፅ ላይ ወጥቶ ከነበረ ቪዲዮ የተወሰደ። ነገር አለ በለው! ***ብአዴን የሻቢያህወአት ጉዳይ አስፈፃሚ አማራ ያልሆነ አማራ መሰል የድምጽና የትግል አፋኝ ቅጥረኛ ነው ማለታቸው ነው። አሁን አማሮቹ ኢህአዴግ ብአዴን የጠላውን ኢትዮጵያዊነትን ይዘው በአደባባይ ” ከባዶ ጭንቅላት በባዶ እግር ተራመዱ…አሁን ብአዴን የየትኛው አማራ ወካይ ነው? አንድነት፣ መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲን ለማፍረስ መድረክ ጦሩን ያሰማራው ለምንድነው? ቡልቻ ደመቅሳ፣ነጋሶ ጊዳዳ፣ሊ/ጠ በየነ ጰጥሮስ፣ በእነዚህ ፓርቲዎች ላይ የሚሰነዝሩት ተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫና ፉከራ ከምን የመነጨ ፍራቻ ነው። ሶስተኛ አማራጭ ሆነን ሀገር እንመጣለን የሚሉት የውጭ ሀገር ነዋሪዎችና ውጭ ሀገር ተምረን መጣን የሚሉት ያልተኬደበትን መንገድ ቀለበትና አሳላጭ ሊሰሩ ይሆን? ኢዴፓና ብአዴን ሊጋቡ ይሆን?”ኢህአዴግ ተቃዋሚ ፓርቲ ይፍጠር የተቃዋሚን ሥራ እየሰራ ደክሞታል የሚሏትን ቧልት ሊተገብሩ ይሆን? ኢህአዴግ ሌንጮ ለታን የመከላከያ ሚኒስትር ሊሾም ይሆን? ደረሲያንና ፖለቲካ ተንታኞች የሥራ ድረሻቸው ምን ይሆን? አማራው እራሱን ወክሎ “ደገኛ” አማራ ብቻ ሳይሆን ደጋ፣ ቆላና ወይናደጋ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው። አማራን ቆላና ወይና ደጋ እንዳይኖር የሚከለክል፣ ትግሬን ደጋ ላይ እንዳይኖር ደገኛ እንዳይባል የሚከለክል…ደቡብ ክልል ደጋ የአየር ጠባይና ደገኛ እንዳይሆን የሚከለክል ሕገመንግሰት ኢህአዴግ ከየት አመጣ?”

  “በአመለካካት”ሌላውን መወከል ማለት ምን ማለት ነው? ጥንት አባቶች በባዶ አግራቸው በጠርሙስ አጋምና ቀጋ ላይ አልፈው ዳርድንበርን ሰንደቅን ካስከበሩ በተጠረገ መንገድ በባዶ እግሩ ተሰልፎ ማንነቱን የማያስከብር ትውልድ አይኖርም!። ያልሆኑትን ነን ብለው ባንዳና ሹምባሽ ሎሌዎች ተጠረቃቅመው አማራ መሰሎች ሁሉ ማንነታቸውን ይፈትሹ፣ ድሮም ቤትህን አጥራ ብያለሁ..ለማያድሩበትም ቤት አያምሹ!ወይ ውረድ ወይ ሂድ ! እንቢኝ በል በመብትህ እንቢኝ በል በአገርህ!እንተ የራስህ ወካይ ሰው! ሙሉ ሰው ኢትዮጵያዊ ነህ!።ወጣቱ ንቃ ውሻ በቀደደው ጅብ ታስገባለህ!!…..ሠላም!

 10. ወሎየው

  February 24, 2014 at 4:22 PM

  አቤት ጎንደሬው እንዲህ እንጠራራ እንዲህ እንመካከር ንገረው ለጎጃም ኦሮሞውም ይስማ ደቡብ ቤንሻንጉሉ ሶማሌው ሀረሬው ጋምቤላ ቤንሻንጉል ሁሉም ባንድ ይምከር:: መች ኢትዮጵያን ጠላን ጭቆናን እንጅ
  በርግጥ ሸዋ ለሌላ ቀርቶ ለራሱ ሰዎችም አይሆንም:: እርስ በርሳቸው የተላለቁት በመርዝ ነው:: አጼ ሚኒሊክ የተሻሉ ሰው ነበሩ:: የተሻሉ የሆኑት ግማሽ ጎናቸው ከሌላ ብሄር በመሆኑ ነው:: ያም በመሆኑ በመርዝ ገደሏቸው:: ሚስታቸውን ጣይቱን በገዳም አስቀምጠው በመጨረሻ ገደሏቸው:: ልጅ እያሱን ገደሉ: ንግስት ጣይቱን በመርዝ ባላቸውን ራስ ጉግሳን ደግሞ በሀሰት ወንጅለው ጦር አዝምተው ገደሏቸው:: የየጠቅላይ ግዛቱን ታዋቂ ሰዎች በመርዝ ጨረሱ:: አንዳንዶችን ደግሞ በሀሰት ወንጅለው ጦር እያዘመቱ አጠፏቸው:: እንደዚያ ነበር ያደረጉት:: ይህን ሲያደርጉ እንደተባለው በመሳሪያ ይጠቀሙት የነበረው እኛኑ ነበር:: አንዳችንን በአንዳችን እያስመቱ ጊዜያቸው እስኪደርስ ድረስ ቀለዱብን:: ስዩመ እግዚአብሔር እያልን ሰገድንላቸው:: መኢአድ የሰሜን ሸዋወች ስብስብ መሆኑን ማንም ያውቃል:: እነርሱም እንዳባቶቻቸው በብልጠት እየተራመዱ ነው:: ከእኛው መዋጮ ሰብስበው እየተከፋፈሉ አንዳችን በሌላችን እንድንጠረጠር እያደረጉ ዛሬም እንደትናንቱ ታናሽ አድርገው ይቀልዱብናል:: እንደእውነቱ ከሆነ ከሸዋወች ወያኔ ይሻላል:: ወያኔ ቢያንስ ከአብራኩ ወጥቻለሁ ላለው ህዝብ ሰርቷል:: ትናንት በድህነት ይኖሩ የነበሩ ይበሉት ለሆዳቸው ይለብሱት ለገላቸው ያልነበራቸው ትግሬዎች ዛሬ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውታል:: እንደሸዋወች በስልጣን ላይ ከተሰባሰቡት ውጭ ያለው ህዝባቸው እንዲበላ እንዲጠጣ እንዲያጌጥ እንዲያምርበት የማይፈልጉ አይደሉም:: እነርሱ በልተው ወርቅ የሚሉትን ህዝባቸውንም ያበላሉ:: ሸዋወች እርስ በርሳቸው እንኳ አይተማመኑም:: ሁሉም በግለኝነት ላይ የተመሰረቱ ስግብግቦችና ምቀኞች ናቸው:: ከነርሱ ውጭ የሆነ የወዛ ሰው ካዩ በቅናት ይደብኑና እርሱን ለማጥፋት ሴራ ይጎነጉናሉ:: የንጉስ ሚካኤል ዘር የጠፋው በሸዋወች ነው:: ዛሬም ቢሆን ለወሎ አልተኙም:: ወሎየ የሆነ ሰው እንደጠላት እየተዘመተበት ነው ያለው:: ልደቱ ወሎየ ስለሆነ ሀቅ ይዞም የሚሰማው ጠፋ:: ሸዋወች በሚያውቁበት ስልት ማለት በሀሰት ውንጀላና በአሉባልታ እወጣ እወጣ ያለውን የአገር አይን ደነቆሉት::
  ከትግሬና ከሸዋ በተለይ ደግሞ ከሸዋ ጣሊያን ተመልሶ ቢገዛኝ እመርጣለሁ::
  እንታገል ከተባለ ወያኔን ብቻ ሳይሆን የሸዋ ድርጅቶችንም አንድ ላይ መሆን አለበት:: ይህን ያነበባችሁ ሰዎች በኔ ላይ ከመጮሀችሁ በፊት የተናገርኩትን ነገር በደንብ አብሰልስሉት:: ከተናገርኩት ውስጥ አንድም ሀሰት የለውም:: ስለዚህ ትግላችን ከነዚህ ከሁለቱ አካባቢወች የጸዳ መሆን አለበት:: እነርሱ የገቡበት ድርጅት መፍረሱ አይቀርም:: በተንኮል አንቱ የተባሉ ናቸው:: ለነገሩ ትግሬ ይሻላል:: ቢያንስ እንደጠላህ ታውቃለህ:: ሸዋ ማለት ጥርሱን እያሳየ ቀኝ ሲገጥመው ድራሽ የሚያጠፋ ነው:: እንዲያው ሳስበው ከሰሜን ሸዋ የተገኙት አቡነተክለሀይማኖትና ክርስቶሥሰምራ ብቻ ሳይሆኑ ዲያብሎስም ጭምር ነው::

 11. ከበደ ድሪባ

  February 24, 2014 at 5:59 PM

  በጣም የሚገርመውና በህዝብ ገንዘብ የሚቀልደው የኢትዮጵያ ዘና አገልግሎት ድርጅት ወብ ሳይት ላይ የወጣ አራምባና ቖቦ ጨዋታ. ጥሩነቱ ግን አገራችን ሳንሱር ማድረግ ተከልክሎአል. ካላመናችሂሁ የሚቀትለውን ተመልከቱ

  http://www.ena.gov.et/index.php?option=com_k2&view=item&id=2072%3A%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A_%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%A2%E1%8A%A0%E1%8B%B5-%E1_%93%E1%88_%E1%89%B2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%89%A3%E1%88%85%E1%88_%E1%8B%B3%E1%88_-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%89%83%E1%8B%89%E1%88%9E-%E1%88%B0%E1%88_%E1__-%E1%8A%A0%E1%8A%AB%E1%88%84%E1%8B%B1&Itemid=249&lang=am

 12. TERUBE

  February 25, 2014 at 7:25 AM

  KKKKKKKKKK KEBADO CHNQELAT BAdo eger yeshalale dege belhale yehe new meles esu

 13. TERUBE

  February 25, 2014 at 7:28 AM

  ke bado chnqelat KKKKKKKKK BADO EGER YESHALALE:: TERU BELHALE YAGER SEW

 14. tsehay

  February 25, 2014 at 8:10 AM

  ምንም ይሁን ምን ባ/ዳር ላደረጉት ነገር ክብር አለን