የበግ ለምድ ደራቢው “ጋዜጠኛ”

ከዳንኤል ገዛኽኝ አትላንታ |

“ዜና የአስተያየት ጉዳይ ሆኖዋል”በሚለው አስተያየቱ የሚታወቀው ኢራናዊው ግን በዜግነቱ እንግሊዛዊ የሆነው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ ነው።ሳልማን ሩሽዲ ዛሬም ሆነ ትላንት በ ሺአታዊው የ ኢራን አስተዳደር የሚፈለግ እንዲያውም ከ አልሆሚኒ ዘመን እስካሁንም በሃገሩ መንግስት ምህረት ያልተደረገለት የፕሬስ ሰው ነው።ሩሽዲ ታዲያ ሃገሩን እንዲተው ቀየውን እንዳያይ ተሳዶ እና ተሳቆ በሰው ሃገር በግዞት እንዲኖር ያደረገው በ እስልምና ረገድ የተቃወመው ጽሁፍ ነው።ጽሁፉ ውስጥ እንዳልገባ ምናልባትም የ አንድ ወገን ሃሳብ መስሎ ለሚንጸባረቅባቸው አጥባቂያን /conservatives/ስሜታቸው እንዳይነካ ስል ሃሳቡንም ሙሉ ለሙሉ አልነካካውም ግን ብቻ ሩሽዲ (The Satanic verses)ሰይጣናዊ ጥቅሶች ሲል የራሱ እምነት የዋለበትን የሃይማኖት አስተምህሮት ሃሳቦች በተቸባቸው ጽሁፎቹ ነው በተገኘበት በድንጋይ ተወግሮ እንዲገደል የሚያዘው የሞት ፍርድ “ፋትዋ”የተላለፈበት።ይሁን እና አገዛዝ ቢለወጥም ስር አት ቢሸጋገርም በሳልማን ሩሽዲ ላይ የተላለፈው “ፋትዋ”የሞት ፍርድ ግን እስካሁንም አልተነሳም።እናም ሩሽዲ የተለያዩ ሚዛን አልባ…ፍርደ-ገምድል ጉዳዮችን ከግራ ከቀኝ ሳያዩ የሚዘግቡ እና የ አንድ ወገንን ሃሳብ እና አስተያየት የሚያራግቡ “ጋዜጠኛ”ተብዬ ወሬ ነጋሪዎች ስለሚናገሩት ዜና ሲታዘብ ሩሽዲ “ዜና የአስተያየት ጉዳይ ሆኖዋል”ሲል የሚስተዋለው።
ለጽሁፌ መነሻ ያደረግኩት ሰው ዛሬ ከማተኩርበት ሰው ጋር ምንም ዝምድናም ቀረቤታም ግንኙነት የለውም ነገር ግን በሞያው ጋዜጠኛ ስለሆነ እንደ ሳልማን ሩሽዲ መሆን ባይችል እንኩዋን አንድ ቀን ግን ወደ ህሊናው እንዲመለስ ምኞቴ ነው አይመለስም እንጂ።የሚዲያ ኮምኒኬሽን ባለቤት የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አቶ አማረ አረጋዊን ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከትኩት መሹዋለኪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚስቱ ቤተሰቦች ንብረት በሆነው ፊሊክስ ሱፐር ማርኬት አቅራቢያ ሲሆን ለጥቆ የተመለከትኩት በጊዮን ሆቴል የማስታወቂያ ሚኒስትር ባዘጋጀው አዲስ የፕሬስ ህግ ረቂቅ ውይይት ላይ ነው አመተ ምህረቱ ተዘነጋኝ። በጊዜው ለነጻው ፕሬስ ጋዜጠኛዎች ከግማሽ በላይ ለምንሆነው መጥሪያ ደርሶን በውይይቱ ላይ ለመታደም በስፍራው ብንገኝም ነገር ግን ማህበራችንን በሚመሩት የአመራር አባላት እና በያንዳንዳችን አባላቶች ስምምነት ነጻው ፕሬስ እንደጉዳዩ ባለቤትነት መድረክ ላይ ከሚያወያዩት መሃከል ስፍራ ሳይሰጠው የጥናት ወረቀት ከሚያቀርቡት መካከል አንዱ ሳይሆን በውይይቱ ለመቀጠል እንደሚቸገር በመስማማት የ እለቱን አጀንዳ የወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር በረከት ስም ኦን በ አኤርትራዊ ስማቸው አቶ መብራቱ ማስተዋወቅ ሲጀምሩ አቶ ክፍሌ ሙላት አንጋፋው ጋዜጠኛ የማህበራችን ሊቀመንበር አቶ መብራቱን በመነሳት እድል እንዲሰጡት ይጠይቃቸዋል እሳቸውም “ከፋለው …ከፋለው ቆይ እድል እሰጥሃለው እድል እሰጥሃለው”በማለት ደጋግመው ቢናገሩም ክፍሌ ግን ሊያሳልፋቸው ባለመቻል እንዲናገር እንዲፈቅዱለት ጎተጎተ እናም አቶ መብራቱ …አቶ በረከት ፈቀዱለት እናም ክፍሌ ኢነጋማን በመወከል ተናገረ”የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ነጻው ፕሬስ ባልተወከለበት አንድም ቦታ ባልተሰጠበት ሁኔታ ይህንን ውይይት ለመካፈል ይቸግረናል ስለተደረገልን ጥሪ እናመሰግናለን ስለዚህ ያሰናብቱን “በማለት ሲናገር አቶ በረከት በዋናው ስማቸው አቶ መብራቱ ለማምታታት እና ለማሳመን ቢሞክሩም አቶ ክፍሌ አዳራሹን ለቆ መውጣት ሲጀመር በጉዳዩ ላይ ከሰምምነት የደረሱ የፕሬሱ አባላት ተግተልትለው አዳራሹን ለቀው ሲወጡ…አቶ አማረ አረጋዊ የቀድሞው ኢትዮጲያ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ የበግለምድ በመደረብ ፕሬስ አቁዋቁመው የቀበሮ ባህታዊነታቸውን የሚያውቀው እያወቀው በፕሬሱ ስም ተወክለው ከመድረክ ጉብ ብለው ነበር።ከሳቸውም ጋር ዛሬ ድረስ በፕሬሱ ስም ከወያኔ ጋር ተደራድረው የህዝብ ገንዘብ በጀት ተበጅቶላቸው አገም ጠቀም የፕሬስ ሰዎች ሆነው ሲሞዳሞዱ የቆዩት እነ አንተነህ አብርሃም …እነ መኮንን ተፈሪ ውይይቱን ተቀላቀሉ በሁዋላም ብሄራዊ የጋዜጠኛዎች ማህበር እና የ አሳታሚዎች ፎረም የሚል እነ አቶ አማረ አቁዋቁመው ስብሰባ ጥሎ የወጣው ፕሬስ እንደ ጋጠ-ወጥ በ ኢቲቪ ሲዘፈንበት እና ሲቅራራበት ቆየ እንዲያውም ያንን ቅጥ ያጣ ከጋዜጠኝነት መርህ የዘለል ፕሮግራም በመስራት ፕሬሱን የሰደቡ መስሎዋቸው የራሳቸውን ሞያ ያቀለሉት ጋዜጠኛዎች እነ ሃይለ ኢየሱስ ወርቁ ጋዜጠኛ በ ኢቲቪ በውስጥ የብ አዴን አባል በሁዋላም በበረከት ስም ኦን ልዩ ትዛዝ ከባልደረባው ከታታሪው ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሃመድ ጋር እስርቤት የገባ።አሳዛኙ ነገር በምርጫ 97(2005)ዋዜማ ወያኔ እንደሚፈልገው በርካታ ፕሮግራሞችን በተቃዋሚው ጎራ ያሉትን ህዝቦች ሁሉ አንገት ያስደፋ ስራ የሰራው ሃይለ ኢየሱስ ወርቁ …በባድመ ጦርነት ወቅት ኢትዮጲ ሬድዮን ወክሎ ከቡሬ ግንባር ሲዘግብ የቆየው አብዱልሰመድ መሃመድ በጦርነቱ ወቅት አንገቱ አካባቢ ቆስሎ የነበረ ለወያኔ ሁሉን የሆነ ግን ግን አብዮት ልጆችዋን ትበላለች በሚለው ስሌት በወያኔ ተተፍተው እስር ቤት ለ እስር ቤት የተንከራተቱ አድርባዮች ናቸው።

ግን እነሱም ሆኑ ሌሎች በሞያቸው ጋዜጠኛ የተባሉ የመንግስት ካድሬዎች አደጋ እና እስራት ሲደርስባቸው የደረሰባቸውን ውስጥ ለውስጥ ለፕሬስ ተቁዋማት መረጃ በማቀበል የኔ የሞያ ባልደረባዎች ነጻውን ፕሬስ ከመመስረት አንስቶ እስካሁንም በስደት የሚመሩት ንስር ጋዜጠኛዎች የነዚህን የመንግስት ጉሮሮ የሆኑ በቀቀን ጋዜጠኛዎች ችግር ለፕሬስ ተቁዋማት የደረሰባቸውን በማስታወቁ ረገድ የሚቀድማቸው የለም ። የፕሬስ ተቁዋማትም የሚጠቅሱት የመጀመሪያ የመረጃ ምንጭ(monitor)ንስሮቹን ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ ወቀሳ ሲደርስባቸው እንኩዋን ኢነጋማ እንደ መ ንግስት አሰራር ሳይሆን እንደነጻ ተቁዋም ጋዜጠኛዎቹን ነደሚመለከት ነው ምላሹ።ይሄ ብቻ አይደለም የመንግስት የሚዲያ ተቁዋም ውስጥ መሽገው በርካታ አሳፋሪ መረጃዎችን ለህዝብ በመርጨት ስራ ላይ ተሰማርተው በሁዋላም ባመቻቸው ወቅት ወደስደት ሲያቀኑ እነዚሁ ጋዜጠኛዎች የ አለም መንግስታት ጥገኝነት እንዲሰጡዋቸው አይነተኛ ሚና ከሚወጡት የፕሬስ ተቁዋማት ውስጥ ኢነጋማ አንዱ ነው።በአማረ አረጋዊ የሚመራው ሪፖርተር አንድም ቀን ስለጋዜጠኛዎች እስራት እና ወከባ አንድም ቀን ዘግቦ አያውቅም ነገር ግን መንግስት በወረቀት ዋጋ ላይ ጭማሪ ሲያደርግ ብቻ አማረ ደርሶ የፕሬስ ተሙዋጋች ሆኖ ብቅ ይላል እንጂ።ባለስልሳ ገጹ የማስታወቂያ ጋዜጣው ጉዳይ ስለሚያሳስበው።

ወደዋናው ጉዳዬ ስመለስ ታዲያ አቶ አማረን ለሶስተኛ ጊዜ ያየሁት ማ ዕከላዊ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በፕሬስ ክስ ፖሊስ ጠርቶ ሊያነጋግረው ሲል ሲሆን እንደ አጋጣሚ እኔም ከኢትዮጲያ ሞያሌ አንስቶ እስከ ዲላ ከዚያም ናዝሬት እና አሰላ በሁዋላም አዲስ አበባ ወንጀል ምርመራ በ አደራ እስረኝነት ተመላልሼ በሁዋላም ወንጀል ምርመራ ታስሬ መርማሪዬ አስር አለቃ መሰረት(ሴት)ናት ጠርታ ስታነጋግረኝ አቶ አማረ አንኩዋኩቶ ሊገባ ሲል እንዲጠብቃት ከነገረችው በሁዋላ ከበሩ ወደ ሁዋላ መለስ እንዳለ እንደማይሰማት ስታረጋግጥ ጉዳያችንን ገታ አድርጋ “ይሄን ታውቀዋለህ ?” ስትለኝ አዎ ጋሽ አማረ ነው የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ አልኩዋት “ታዲያ ይሄ ጋሼ የሚባል ሰው ነው እንዴ ?” ስትለኝ አባባልዋ እንዳልገባኝ እና ምን ለማለት እንደፈለገች በገረሜታ አነጋገር ስመልስላት ነገሩን በመተው ወደጉዳያችን ገባች።በወቅቱ እኔ እንኩዋን የታሰርኩት ኢትዮጲያ ሞያሌ አካባቢ ለጉዳይ ሄጄ ሳለ አካባቢው ላይ በተነሳ ረብሻ ወታደሮች ሰዎችን እያስቆሙ መታወቂያ ሲጠይቁ ጉዳዩ በ ኦሮሞዎች እና በመንግስት ደጋፊዎች መካከል የተነሳ ረብሻ ነበር እና መታወቂያ ስጠየቅ የሞያ ማህበሬ የሰጠኝን ቢጫ መታወቁያ አሳየሁኝ መታወቂያው ጋዜጠኛነቴን ከመጠቆሙም በላይ በድጋሚ እሱን በመተው የቀበሌ መታወቂያ ስጠየቅ እሱንም አሳያለሁ ነገር ግን ብሄር በሚለው ስፍራ ላይ የተጻፈው ለነሱ ስላላስደሰታቸው ተይዤ ወደ ሚግሬሽን እስር ቤት በመግባት ነው ጉዳዩ የፌደራል ነው የደቡብ ክልል…የኦሮሚያ ክልል ነው የዞን በሚል የተለያዩ ቦታ እና ሃገሮች ስታሰር ቆይቼ በሁዋላም ወንጀል ምርመራ በዚያ አኩሁዋን ነበረ አማረን የተመለከትኩት።ከዚያ በሁዋላ ታዲያ አማረን ለብዙ ጊዜ ሳላየው ቆይቼ ለ አራተኛ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት በ አንድ የፕሬስ ጉዳዮች ላይ በተደረገ ውይይት የተለመደውን የበግ ለምዱን ደርቦ ደርሶ የነጻ ፕሬስ ተሙዋጋች ሆኖ አየሁት።

በምርጫ 97 ወቅት ተቃዋሚዎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ደርሶ ለሃገር እና ለህዝብ ተቆርቁዋሪ በመምሰል የሚጽፋቸው ር ዕሰ አንቀጾች በ እውነት በማር የተለወሱ መርዞች ነበሩ።እንዲያውም አንዱን ር ዕሰ አንቀጽ እንደማስታውሰው “መርካቶ ተቀምጦ ድንጋይ በመወርወር ስልጣን መጨበጥ አይቻልም” የሚል ነበረ ከዚህ በሁዋላ ነበረ አንዱን ሪፖርተር ላይ የሚሰራ ወዳጄን በግርግሩ ሰሞን አግንቼው ሁኔታዎችን ስጠይቀው ስራ መልቀቁን እና ስራም የለቀቀው የሪፖርተር ሰራተኛዎች አብዛኛዎቹ ጋዜጠኛዎች “ሚናችንን መለየት አለብን”በሚል ዙሪያ አነጋግረውት እሱ ግን”መስራት የሚፈልግ ይስራ የማይሰራ ይልቀቅ”ማለቱን ነገረኝ።እናም አማረ ተቃዋሚዎችን መምከር ጀመረ ፓርላማ ግቡ እያለ።ይህንኑ ጉዳይ ታዲያ የ ኢሳት ዜና አንባቢ ባለፈው አመት የ አማረ አረጋዊ ንብረት የፕሬስ ስራዎች የሚሰራበት ቢሮ በመንግስት ሃይሎች ከተነጠቀ በሁዋላ በቃለምልልሱ ወቅት ጋዜጠኛ ፋሲል ለ አማረ ይህንን የፓርላማ ግቡ ዘገባውን አስታውሶ ሲጠይቀው አማረ በለመደው ቀጣፊ አንደበቱ”እንደዚህ አይነት ነገር አልጻፍኩም ማስረጃ ማቅረብ ትችላለህ ? “ በማለት ስልኩንም ዘግቶዋል።የ አማረ ንብረት በመንግስት ሃይሎች ከመወረሱ በፊት በ አማረ ላይ የመታገት እና ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበትም ነበረ ይህ ግን በመንግስት ሃይሎች የሆነ ሳይሆን በ አላሙዲን ደጋፊዎች እና በዳሽን ባንክ የወያኔ ንብረት አንቀሳቃሾች በሆኑ ግለሰቦች የተፈጸመበት ድርጊት ነበረ።ይህ ሲሆንም ሆነ የንብረት ነጠቃ ሲፈጸምበት የፕሬስ ተቁዋማት ጋዜጦች በርብርብ ዘግበዋል።ታላላቅ የ አለም አቀፍ የፕሬስ መብት ተከራካሪዎችም በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ ዘገባ እንዲያወጡ ኢነጋማ ትልቁን ሚና ተጫውቶዋል።ከነዚህ ሁሉ ነገሮችም በሁዋላ አማረ አረጋዊ በ እውነተኛ ኢትዮጲያውያን የፕሬስ ታጋይ የሆኑ ጋዜጠኛዎች ላይ ወያኔ አደጋ ሲደቅን የወያኔን ዜና መልሶ ከማስተጋባት በቀር አለም አቀፍ የፕሬስ ተቁዋማት ያወጡትን ዘገባ አላስተናገደም።ለነገሩ ድመት መንኩሳ አመልዋን አትረሳ አይደል የሚባለው።ህዝብ ባወቀው ጸሃይ በሞቀው የ ጋዜጠኛ ውብ እሸት ታዬ እና የመምህርት እንደዚሁም ጋዜጠኛ ር ዕዮት አለሙ የሽብር ወንጀል ክስ ሃገር ቤት የሚገኘውን ሪፖርተር ጋዜጣ ባያሳስበውም እንኩዋን ጉዳዩን ቦታ ሰጥተው የዘገቡትን የነ ብሉም በርግ እና የነ ሲፒጄ ዘገባ እንዴት በሪፖርተር ላይ ሳይካተት ቀረ ? ይሄ ያነጋግራል ያጠያይቃል እናም አማረ አረጋዊ የበግ ለምድ የደረበ የቀበሮ ባህታዊ እንጂ እርሱ በ እርግጥም ጋዜጠኛ ነው ለማለት ከዚህ በላይ መሄድ አስቸጋሪ ነው እላለሁ እኔ በበኩሌ ምክንያቱም አለም በ አማረ ላይ የሚፈጸመው በ ፕሬስ ላይ የሚቃጣ አደጋ ነው እያለ ሲጮህ በሁዋላም በሌሎቹ ጋዜጠኛዎች ላይ ሲደርስ የድርጊቱ ፈጻሚ ያለውን መልሶ ማስተጋባት ምንያህል በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ተሰማርቻለሁ ለሚል ሰው አሳፋሪ እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል… ሳልማን ሩሽዲ ለ እውነት እና ለሞያው ሲል እምነቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ጉዳዮችን ተችቶዋል እውነትን ወዶ ሃቅን ሽቶ ሃገሩንም ትቶዋል።አማረ አረጋዊ ደግሞ ገንዘብ…ሆዱን ብሎ ሃገሩን እና ህዝቡን እንደዚሁም እቆምለታለሁ የሚለውን ሞያውን እና እውነትን ክዶዋል ስለዚህ ሲመትሩለት ይነጭ ማለት ይሄ አይደለ ? ለሚደግፈው የገዢ መደብ መቆሙን አለም እያወቀ ለመብቱ ለ አመታት ሲጮህለት በቀጭን የ እውነት ክር እና ስለት ላይ በመረማመድ እውነታን ያቁዋደሱ ጋዜጠኛዎች ላይ የደረሰው ፍርደ-ገምድልነት የማያሳስበው ይህ ምን ይባላል ? ሰላም።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 4, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.