የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። Read story in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 20, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.