የቂርቆስ መካነ መቃብር ስፍራ እየፈረሰ ነው

(ዳግም አሁንም—ከአዲስ አበባ) በኣዲስ ኣበባ ቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃበር እየታረሰ ነው። ከፒያሳ የጎፋ ካምፕን መንገድ ኣያይዞ ለመስራት መሚል ሰበብ፥ የቅዱስ ቂርቆስ መካነ መቃብር ስፍራ ከሙታን ቤተሰብ አውቅና ውጭ፥ ኣጽማቸው ከኣፈር ጋር አየታረሰ ከከተማይቱ ውጭ፥ አንደሚጣል የኣይን አማኞች ኣስታወቁ። ስራው በመንገዶች ባለስልጣን የሚካሄደው ይኸው ዘግናኝ ድርጊት የተጀመረው ከሁለት ቀናት በፊት ሲሆን፥በስፍራው ወዳጅ ዘመዶቸቸውን ለኣመታት ያሳረፉ የሙታን ቤተሰቦች ሁኔታውን ከሰሙበት ሰዓት ጀምሮ፤ አየተጠራሩ የቻለ መቃብሩን በማንሳት ወደ ደብረ ሊባኖስ…ቅሪተ ኣካሉን ይዞ ዳግም አየተላቀሰ የወሰደ ሲሆን….ያልቻሉት ደግሞ ቤተክርስቲያንዋ እዚያዉ ለግዜው ባሰራችው በቆርቆሮ የተሰራ ግዜያዊ የኣጽም ማከማቻ ለማቆየት ምዋች ቤተሰቦቻቸውን ኣስቆፍረው ለመውሰድ ተገደዋል። …የኣይን አማኞቹምጨምረዉ አንደተናገሩት ይህ ቁፋሮ መሚካሄድበት ሰኣት በቦታው ረብሻ እንዳይነሳ በሚል ስጋት ሲቪል የለበሱ ወታደሮች የነበሩ ሲሆን የቁፋሮውን ማሽን የሚያንቀሳቅሰው ግለሰብ ደግሞ፤ ፊቱ የማይታይ አንደ ኣጥፍቶ ጠፊ የተሸፋፈነ አንደነበርም ኣክለው ገልጸዋል።

ከሁሉም የሚያሳዝነው ይላሉ ፥በስፍራው ድርጊቱን ሲመለከቱ የነበሩ ታዛቢዎች፥ ከሁሉ የሚያሳዝነው፥ ከኣፈር ጋር ኣብሮ ሲቆፈር እና በገልባጭ መኪኖች ላይ ሲጫን የነበረውን የሰዉ ልጅ ቅሪት የተቀላቀለበትን ኣፈር፥ ኣንዳንድ የኣካባቢው ነዋሪዎች ለጭቃ ቤታቸው ማሳደሻ አና ማሰሪያ በሚል ባለማወቅ፥በየ ቤታቸው በራፍ የማስደፋታቸው ጉዳይ ነበር ይሉና፤ በተለይም ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት፣ በተልምዶ ኣርባ ቀበሌ መንደርተኞች፥ ይህን ነገር ሲያደርጉ አንደነበር እና፥በህዋላም ከመጣው ኣፈር ጋር የሰው ልጅ ፥ራስ ቅልን ጨምሮ ረጃጅም ኣጥንቶች ከኣፈሩ ጋር ተደባልቆ በማየታቸው፤ በሁኔታው በመደናገጥ፥ የመጣውን ኣፈር መልሶ ለማስወሰድ ለማን ኣቤት አንደሚሉ ግራ ተጋብተውም አንደነበር እማኞቹ መስክረዋል።
“የኣስራስድስት ኣመት ወጣት ነኝ። ትንሽ ከእናቴ ቤት ኣጠገብ ተጨማሪ ቤት ለመቀጠል ኣስቤ፥ ለኣንድ የሰፈሩ ደላላ፤ ኣፈር አንዲያስደፋልኝ የነገርኩት ከሳምንታት በፊት ነበር፥፥ማምሻው ላይ ያልኩትን አንዳደረልገ ነገረኝ። ለወሮታው ብር ሃምሳ ከፍዬ፥ ሲነጋጋ ሰራተኛ በመፈለግ፤ የቤቴን ስራ ለመጀመር ሳስብ፥ኣፈሩ ከ ቂርቆስ መካነ መቃብር በቀጥታ አንደመጣ እና በውስጡም የሰው ልጅ ቅሪተ ኣካል ኣጽም ተቀላቅሎ አንዳለበት ሰዎች ነገሩኝ። በሁኔታው ባዝንም … ምንም ማድረግ ኣልችልም። ኣፈሩን ከቅሪቱ በማጽዳት የጀመርኩዋትን ቤት እጨርሳለሁ” ብሎናል። በነገራችን ላይ፥ ይህ የሰው ልጆችን መካነ መቃበር ያለ ቤተሰብ አውቅና ተቆፍሮ የትም ሲጣል አና ዘግናኝ ስራ ሲሰራ፥ በስፍራው ማንኛውም ኣይነት ሚዲያ ያልነበረ እና ይልቁንም የግሉም ተብዬ ሆኑ የመንግስት ሚዲያዎች በዕለቱ፤ ሙዚቃ በማሰማት እና ኣርሰናል፣ ባርሴሎና ወሬ ላይ ተጠምደው አንደነበርም ለማወቅ ተችልዋል። “ወያኔ አንኳን ኖረን፤ ሞተንም ኣያስኖረንም!” ብለዋል ታዛቢዎች።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የቂርቆስ መካነ መቃብር ስፍራ እየፈረሰ ነው

  1. Hile

    March 15, 2013 at 8:21 AM

    “…ከፒያሳ የጎፋ ካምፕን መንገድ ኣያይዞ ለመስራት መሚል ሰበብ…”. ይህን ‘ሰበብ’
    ከሆነ፤ ዋናው ምክንያት ልትነግረን ትችላለህ? ወይስ “Whatever It Is, I’m Against It!” የሚለውን የGroucho Marx የተለመደ አስተሳሰብህ መሆኑ ነው?