የቁልቁለት መንገድ! (ተመስገን ደሳለኝ)

…በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና፡፡ የግል ጥቅም አሳዳጅ፣ አፋሽ-አጎንባሽ በሞላበት፣ እንደ ቴዎድሮስ ለሀገር ቤዛ መሆን፤ እንደ ግርማሜዎቹ እና ወርቅነህ የራስን ምቾት ወዲያ ጥሎ በጠገበ ሆድ ከወገን ጋር መራብና ከጎኑ መቆም፤ እንደ አቶ ሽፈራው ደሳለኝ አስፈሪ ሞት ከከበበው ሸለቆ ውስጥ በህይወት ለመውጣት ሲባል የጠላትን ጫማ ከመላስና ያላመኑበትን ተናግሮ ምህረት ከመጠየቅ ይልቅ በድፍረት ሞትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ወይም ግንባርን ለአረር መስጠት እንደ ተረታ-ተረት ከተቆጠረ ዘመናት አልፏል (አቶ ሽፈራው ደሳለኝ ማን ናቸው? ለሚለኝ አንባቢዬ ‹‹የታኀሣሡ ግርግር እና መዘዙ›› የተሰኘውን የብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ ገፅ 302ን እንዲያነብ እጋብዘዋለሁ) አሊያም ደግሞ የሰው ዘር በመሆን ብቻ የሚገኘውን የሞራል ልዕልና ከትውልድና ሀገር ጥቅም አኳያ ለማጠየቅ በዚህ አውድ ለማነሳው ተጠየቅ በአንፅሮ ለማፍታታት ይጠቅመኝ ዘንድ እኔው ራሴ እዚሁ ጠቅሼው አልፋለሁ፡፡

የመጽሐፉ ደራሲ ‹‹በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጊዜ የድጋፍ ንግግር አድርጋችኋል በማለት በመንግስት ተይዘው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ከተላኩት አንዱ የሆኑት…›› ብለው ከአቶ ሽፈራው ደሳለኝ ጋር ከአስተዋወቁን በኋላ እንዲህ በማለት ትርክታቸውን ይቀጥላሉ፡- ‹‹…አቶ ሽፈራው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ተልከው ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ዳኛው ‹ሠርተሃል ለተባለው ወንጀል ጥፋተኛ ነህ፣ አይደለህም?› ይላቸዋል፡፡ ‹የቱን ወንጀል?› ሲሉ አቶ ሽፈራው ዳኛውን ይጠይቃሉ፡፡ (Read the full article in PDF)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 19, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የቁልቁለት መንገድ! (ተመስገን ደሳለኝ)

 1. Tom

  March 21, 2014 at 11:52 AM

  “በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና፡፡ የግል ጥቅም አሳዳጅ፣ አፋሽ-አጎንባሽ በሞላበት፣ እንደ ቴዎድሮስ ለሀገር ቤዛ መሆን፤ እንደ ግርማሜዎቹ እና ወርቅነህ የራስን ምቾት ወዲያ ጥሎ በጠገበ ሆድ ከወገን ጋር መራብና ከጎኑ መቆም፤ እንደ አቶ ሽፈራው ደሳለኝ አስፈሪ ሞት ከከበበው ሸለቆ ውስጥ በህይወት ለመውጣት ሲባል የጠላትን ጫማ ከመላስና ያላመኑበትን ተናግሮ ምህረት ከመጠየቅ ይልቅ በድፍረት ሞትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ወይም ግንባርን ለአረር መስጠት እንደ ተረታ-ተረት ከተቆጠረ ዘመናት አልፏል”
  መልካም አገላለጽ: መልካም እይታ!
  -ተቃዋሚውን መተቸት ከወያኔ ጋር እንደመወገን አድርገው ለሚያስቡ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚውን ከነህጸጹ መካብና ወያኔን ብቻ ማውገዝን እንደቁምነገር ለያዙ ዘባተሎወች
  -ተቃዋሚ ነን ብለው የተጎለቱ ግን የሚታገሉት አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ለሆነ ከንቱወች
  መልካም መልእክት ነው::
  ችግሩ ምን መሰለህ- እኒህ ሰወች ብትጠቅሳቸው የማያዩ ብትነግራቸው የማይሰሙ: የተቃዋሚ መሪ በመባላቸው ብቻ ኮርተው የሚኖሩ ራዕይ አልባ መሆናቸው ነው::