የቀድሞ ደህንነት ሹም እየተገረፈ ነው! (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምንጮች አሁን በደረሰኝ መረጃ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው አረመኔው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መገረፉን አስታውቀዋል። የአዜብና መለስ ቀኝ እጅ የነበረው ይህ ጨካኝ የደህንነት ሹም በስልጣን በነበረበት ወቅት እነ ጄኔራል አሳምነውን በመደብደብ፣ አይናቸውን በቦክስ በመምታት ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ምንጮች አስታውሰዋል። በ1997-98 ዓ.ም በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖች እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ያደረገው ወ/ስላሴ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። በርካታ ሰዎች ከመግረፍና ከማሰቃየት ባለፈ በጥይት ደብድቦ ይገድል እነደነበረ አመልክተዋል። የቤተመንግስት የጥበቃ ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ አንገታቸውን በስለት በማረድ እንዲሁም የመንገድ ት/ሚኒስትሩን አቶ አየነው ቢተውልኝን በገመድ አንቆ የገደለው ወ/ስላሴ መሆኑን ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ወ/ስላሴ በትላንትናው እና በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ መገረፉን ምንጮች አረጋግጠዋል።

ወልደስላሴ

ወልደስላሴ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

6 Responses to የቀድሞ ደህንነት ሹም እየተገረፈ ነው! (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

 1. Defaru Beza

  September 6, 2013 at 6:48 AM

  የወልደሥላሴ መታሰርና እስካሁን ለፈጸማቸው ጥፋቶች (ወንጀልና ፍትሀ-ብሔር)ተገቢውን ቅጣት መቀበሉ በፍርድ ቤት የሚወሰን መሆን ሲገባው ድብደባን ምን አመጣው:: በሥልጣን ላይ ያሉ ሁሉ የወንጀል ምርመራ ከሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲታቅብ መታገል እንደሚኖርባቸው የሚሳይ ይመለኛል:: ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉት ሲታሰሩ አይደለምን::

 2. AyzoshAgere

  September 6, 2013 at 9:51 AM

  …Too good to belive though….

 3. kebede

  September 6, 2013 at 10:42 AM

  የፍትሕና የሰብአዊነት መሠረተ-ሐሳብ ከውስጣቸው ታጥቦ ስለወጣ የዛሬዎቹ ገራፊዎች ነገ እንደሚገረፉ ለማወቅ እንኳን አይቻላቸውም። በመሆኑም…….

  እየተመዘነ፤ እየተቆጠረ
  በሠፈሩት ቁና እየተሠፈረ
  በሽፍቶች ከተማ ዕዳ ‘ሚከፈለው
  አፈር በሕልና ዱላ በዱላ ነው

 4. Gudeta

  September 6, 2013 at 11:02 PM

  This murderer deserves a life sentence.

 5. Abebe

  September 8, 2013 at 5:07 AM

  Beseferut kuna Mesfer alikerim yanisewal

 6. ሰለሞን

  September 12, 2013 at 10:40 AM

  ወያኒ አንዳንዲ ዲሞክራት መሆኑን የሚያሳየን የራሱን አመራር እና ባለስልጣን ነን ባዮችን ሁሉ አለ መማሩ ነው። ወልደስላሲም የዚሁ እጣ ደርሶታል ።ብራቮ ወያኒ ብለናል። አይደርስ መስላት የሚባለው እንደዚህ አይነቱ አይደል አቶ ወልደስላሲ ቻለው ከማለት ውጭ ምን ይባላል መማር የፈለገ አረመኒ ሁሉ የሚያስተምር ትልቅ ትምህርት ነው።