የሶርያ ስደትኞች ሰላይ በአሜሪካ ተያዘ – የዲያስፖራ ኢትዮጵያ ሰላዮችን እናጋልጥ!

EMF — የኢትዮሜዲያ ድረ-ገጽ “Bad news for Meles Zenawi spies in the U.S.” (ethiomedia.com..) ብሎ ባሰፈረው ዜና የቨርጂኒያው መሃመድ አናስ ሱኢድ ለሶሪያ አንባገነን መንግስት ሲሰልል ተይዞ መታሰሩን ገልጾ፤ ይህም በዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ካገኙ በኋላ ለአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳድር ለሚሰልሉ የገዢው ፓርቲ አገልጋዮች ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስፍሯል።

የ 47 አመቱ የሶርያ መሃመድ አናስ አሜሪካዊ ዜግነት ያለው ነው።

መሃመድ አናስ ሱኢድ በውጭ የሚኖሩ ሶርያውያንን የፖለቲካ እንቅስቃሴና ተቃውሞ ሰልፎችን በስእል እና በድምጽ በመቅረጽ፤ በማስፈራራት እና በልዩ ልዩ ዘዴዎች በማወክ፤ ሽብር በመፍጠር፤ እና መረጃዎችን ለባሻር አል አሳድ መንግስት በማቀበል ሲሰራ እንደነበር በአሜሪካ መንግስት ተደርሶበታል። ግለሰቡን ሊታሰር የቻለውም ጉዳዩን ይከታተሉ የነበሩ የሶርያ ተወላጆች ባደረጉት ክትትል እና ጥቆማ ነው።

እንደ ኢትዮሜዲያ ድረ-ገጽ ዘገባ በዩናይትድ ስቴትስ ለተመሳሳይ ስራ የተሰማሩት የአቶ መለስ ሰላዮች በመጀመሪያ በፖለቲካ ጥገኝነት የመኖርያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ) ያገኛሉ አዚያም ዜጋ ይሆኑና የስለላ ስራቸውን ይጀምራሉ። ይህንን ሲያደርጉ ጥገኝነት ሲጠይቁ የገቡትን ቃለ-መሃላ እንደዋዛ ችላ በማለት እንደሆን ድረ-ገጹ ዘግቧል።

የአንድን ሃገር ዜግነት ይዞ፤ በሚኖርበት ስፍራ ለለሌ ሀገር መሰለል እስከ በእድሜ ልክ እስራት እና በሞት ቅጣት የሚያስፈርድ ከባድ ወንጀል ነው።

የአቶ መለስ መንግስት በሰሜን አሜሪካ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ፤ በአውስትራሊያ እና በአፍሪካ ሀገሮችም በሚሊዮን ዶላር በጀት በመመደብ ሰላዮቹን እንዳስማራ ከኮበለሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ከአውሮፓ የኮበለሉ ከፍተኛ የኤምባሲ መልእክተኞች በተለይ በቤልጂየም እና በሆላንድ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንን እየሰለሉ ያሉትን ሰዎች ስም ዝርዝር ለዝግጅት እፍላችን ልከዋል።

የእነዚህን ሰላዮች ስም ዝርዝር ከህግ ባለሞያዎች ጋር ተማክረን ይፋ እናደርጋለን። ሰላዮቹ በከፊል በስደት ስም ወደ አውሮፓ የተላኩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በአዲስ አበባ የመኖርያ ቤት ቦታ ለማግኘት ሲሉ በዚህ ስራ እንደተሰማሩ የኤምባሲ ምንጮች ጠቁመዋል።

እንደሶርያውያን ሁሉ ኢትዮጵያውያንም በስደት ከሚኖሩበት ሃገር የሚያውኳቸውን ሰላዮች መጋለጥ እና ህግ ፊት ማቆም አለባቸው። ይህንን ለማድረግ ሁለት ነገሮች መሰራት አለባቸው። አንደኛ፤ እነዚህን ሰላዮች የሚከታተልና የስም ዝርዝራቸውን የሚሰበስብ አንድ አካል ማቋቋም፤ እና በሁለተኛ ደረጃ ሰላዮቹን ለሚመለከተው የፍትህ አካል የሚሰጥ የባለሞያዎች ቡድን መመስረት።

አስተያየት ስጡበት።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 25, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.