የሳኡዲ ግፍና የኛ ሰልፍ (ተክለሚካኤል አበበ)

እንደመግቢያ፤ የፋና ነገር

ፋና፤ ኢትዮጵያዊ ካናዳዊት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፡፡ እሱዋ እንደምትለው ከሆነ ፖለቲካ አትወድም፡፡ በአባይ ቦንድ ሽያጭና በመሰል የመንግስት መርሀ ግብር ዝግጅቶች ላይ ግን ቀድማ የምትገኝ ጎበዝ ነች፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ ተቃዋሚዎች መፈክር ይዘው በኢህአዴግ ላይ ሲሰለፉ ስትመለከት ግን ደምዋ ይፈላል፡፡ ሰሞኑን በዚህ በሳኡዲአረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ግፍ ስላሳዘናት፤ ሳውዲዎችን ልክ ልካቸውን ልትነግራቸው ቆርጣ ተነስታለች፡፡ ስለዚህም በመጪው አርብ መሰል ጉዋደኞችዋን ይዛ ሰልፍ ልትወጣ ተፍ ተፍ ትላለች፡፡ በፋና እምነት በሳኡዲ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የሰልፉ እንዱ ደንብ በምንም አይነት መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ስም በክፉ አይነሳም የሚለው ነው፡፡ ሰናይም ወንዱ ፋና ነው፡፡ እንደፋና ያምናል፡፡ ከፋና ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር፤ ኢትዮጵያውኑን በግዜ ባለመርዳቱ የኢትዮጵያን መንግስት የሚመለከተው ቢሆንም፤ የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮች ማንገብ ይከፈፍለናል ባይ ነው፡፡ በተወሰነ በሰሞኑ ሰልፎች የገረመኝ፤ ያሳሰበኝ፤ ያቃጠለኝም ነገር ይሄ ነው፡፡  Read story in PDF:  …የኛ ነገር፡ ክፍል 20፤ ሰይፋችንን አጥተነው፤ ሰልፋችንንም ልንቀማ??

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 30, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.