የሳኡዲን ድርጊት በመቃወም ዋሺንግተን ዲሲ ሰልፍ ይደረጋል

(EMF) በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ኢሰብአዊ ድርጊት በመቃወም፤ በመጪ ሃሙስ፤ ኖቬምበር 19 ቀን በዋሺንግተን ዲሲ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። በሳኡዲ ኢምባሲ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ወደ ኢምባሲው ከመግባታቸው በፊት፤ ግፍ እና በደል የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንን ድምጽ ለማሰማት በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ፤ በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።
Stop violence
የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረገው ከሳኡዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት፤ ከጠዋቱ 9:00 AM ላይ ሲሆን፤ አድራሻውም 601 New Hampshire Ave. NW Washington, DC 20037 መሆኑን ለኢ.ኤም.ኤፍ በተላከው ማስታወሻ ላይ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና በጀርመን፣ በደቡብ ኮርያ በስዊድን በሳኡዲ ኢምባሲ አካባቢ የተቃውሞ ሰልፎች የሚደረጉ ሲሆን፤ በአትላንታ እና በሌሎች ከተሞችም የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት በማድረግ ግፍ የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያንን ለማሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከሚደርሱን ዜናዎች ለማወቅ ተችሏል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 12, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የሳኡዲን ድርጊት በመቃወም ዋሺንግተን ዲሲ ሰልፍ ይደረጋል

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  November 14, 2013 at 5:47 AM

  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን?
  +++++++++++++++++++++
  ዳውላና አህያን በፍርሃት ሲስሉ፤
  የአባቶች ትርጉሙ ጠሊቅ ነው አባባሉ።
  የዘመኑ አህያ ዳውላውስ ማነው?
  አይተን እንዳላየን በቀን የፈራነው።
  አህያው አጋዚ ዛሬም የመሸበት፤
  በቀን ሰው ይመስላል፣
  ቆዳው ዥብ አለበት።
  ችግራችን ደግሞ ተነግሮ ያላለቀው፤
  ዳውላው እኛ ነን የማንደብቀው።
  ጅቦቹ በቀትር ጅብ አህያም ናቸው፤
  ወቸገል ከሞተ አጡ የሚያናምናቸው።
  እርኩሶች በቀን-ፊት ሰዎች ይመስላሉ፤
  የሕዝብ ደም ሲመጡ ማታ እየገደሉ።
  የትናንቱን ታሪክ መዝግቦታል አለ፤
  እነማን ተገድለው ማን እንዳስገደለ።
  ወገን ሲሻ ርቆ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰርቀውት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?
  ይኸውና ደግሞ ግድያቸው ዘልቆ፤
  በስደትም ታየ ባደባባይ ታውቆ።
  እኮ ጀርባ ማከክ በስቃይ መማቀቅ፤
  ቅማሏ ደም መጥጣ ጥጉን ስትደበቅ፤
  እዚህ እዚያ ቢፎከት ሺህ ቢገላበጡ፤
  ቅማሎቹም በዝተው ደሙን እየጠጡ፤
  መፎከቱ ብሶ ቆዳን መላጥ ሲደርስ፤
  ደም መክፈሉ አይቀርም እስካልሞተች ድረስ።
  እናም እስከመቼ ችግሩን ስታዩ፤
  ምክንያት ከሰበብ ቀራችሁ ሳትለዩ።
  በሰበቡ ጮኸን ውግዝ ብንለውም፤
  በቁም መሞት እንጂ ፋይዳስ አይኖረውም።
  ምሥጢሩ ይሄው ነው የአህያ የዳውላው፤
  ፍርሃት ነፃነትን ባሪያ አድርጎ በላው።
  ወገን አርቆ-ሲሻ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰረቁት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?

  +++++++መታሰቢያነቱ+++++++++
  በሳውዲና በዓለም ላይ
  በስደት ላይ ለሞቱና አሁንም ለሚሰቃዩ ወገኖቼ።
  ተገጣጠመ፣
  ሕዳር ፬ ፳፻፮