የሰዓታት ቆይታ በዓድዋ! (አብርሃ ደስታ ከዓድዋ)

ህወሓት “የቀይ ኮኮብ ዘመቻ” ከፍቶብናል (የመጨረሻ እርምጃ መሆኑ ነው)። በዘመቻው ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ የዓረና አባላት ይበልጥ ለማደራጀትና ስለሚሰነዘርባቸው ቀጥተኛ ጥቃት ለመነጋገር በብዙ የትግራይ አከባቢዎች ተዘዋውሬ ነበር። በዓድዋ ከተማ ትንሽ ግዜ ለማረፍ ዕድል አግኝቼ ነበር።

Abraha Desta

Abraha Desta


በመልካም አስተዳደር እጦት የሚሰቃይ ህዝብ የዓድዋ ነው (ምናልባት እንደነገሩኝ ከሆነ ከሐውዜንም የባሰ ሳይሆን አይቀርም)። በዓድዋ በግለሰቦች ላይ ግፍ ይፈፀማል። እስካሁን ድረስ የኢሠፓና የኢዲዩ ወዘተ አባላት ነበሩ እየተባሉ ከሕብረተሰቡ የሚገለሉና ምንም ዓይነት የመንግስት አገልግሎት የተነፈጉ የቤተሰብ መሪዎች አሉ። በዚህ ምክንያት የዓድዋ ሰዎች መቃወም ያስፈራቸዋል፤ ምክንያቱም እንደ ኢሠፓና ኢዲዩ አባላት ከማሕበረሰቡ እንዲገለሉ ይደረጋል። በትግራይ “አይነኬ” ሰዎች ያሉበት ቦታ ዓድዋ ነው።

ሌላ ነዋሪዎቹ ያጫወቱኝ አስገራሚ ነገር አሁን ታማኝ ካድሬዎች ሁነው እያገለገሉ ያሉ ግለሰቦች የቅርብ ቤተሰቦቻቸው በህወሓት የተረሸኑባቸው ናቸው። የቅርብ ቤተሰቡ በህወሓት የተረሸነበት ሰው እንዴት ህወሓትን በታማኝነት ያገለግላል? በቃ ህወሓት የቤተሰቦቻቸው አባላት ሲገድልባቸው ደንግጠው አሁንም በታማኝነት ካላገለገሉ እነሱም (የተቀሩ) በህወሓት የሚገደሉ ይመስላቸዋል።

ባጭሩ ህወሓትን ስለሚፈሩ ህወሓትን ያገለግላሉ። ለማመን ይከብዳል። ግን ነዋሪዎቹ የነገሩኝ ነው። በህወሓት ስርዓት ባርነት አለ ማለት ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to የሰዓታት ቆይታ በዓድዋ! (አብርሃ ደስታ ከዓድዋ)

 1. andnet berhane

  October 24, 2013 at 11:38 PM

  አብርሃ ደስታ በጣም ደፍርና እውነትን ያነገብክ ኩሩ ሙሕር መሆንክን በተግባር እያሳየህ አንተን ተከትለው ከፍርሃት ወጥተው ራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ለመታደግ ያለ መቃጣታቸው ህሊናቸው የሚወቅሳቸው ብዙዎች ናቸው:: የሰው ልጅ በዚህ አለም የሚኖረው ለተውሰነ ጊዜ መሆኑን ዘንግቶ ለዚህ የማይረባ አፈር ለባሽ ስጋ በማሽሞንሞን ልኑር ብሎ: እሱን መሳይ ሰው በመፍራትና ለሆድ በማደር በተፈጥሮ የተለገሰውን ሰዋዊ መብት ሲነፈግና እሱነቱ ተዘንግቶ ቆሳቁስ (ናውቲ) ለማድረግ ሲሞከሩ: ዝምታው ምን ይሆን? ብልሎ ያለማሰብ በጣም የሚገርምና የሚያስድነግጥ ጊዜ በመድረሳችን: ወያነ ቆምኩለት የሚለውን ክቡር ሕይወቱን የከፈለ እንዳይራብ ያጎረሰው እንዳይሸነፍ የተጋፈጠለት ስልጣን ይዞ ውልውታ ይከፍላል ብሎ ሲጠብቅ በትግል ጊዜ በረሃብ ሲረግፍፍ በርዳታ የተገኘውን በገንዘብ በመሸጥ ለግል እርባናው ያደረገው:የተርሳ መስሏቸው ዛረእም በባሰ በልግዥም እንግዛህ ማለት ድፍረት ነው:: እንዳባቶች ያሉት እንዳናጠፋችሁ ልጆቻችን እኛንግን ከሳት አገባችሁን ብለዋል ይህን የማይገባው ከሆነ ሰው መሆኑን ዘንግቷል ማለት ነው:ወንድሜ አብርሃ ታሪክ መስራት ታላቅ የሕይወት መሰረት በመሆኑ ቅንና ለውገን ማሰብ አንዱ ዋነኛ በመሆኑ ያለህን ሁሉን ኃይልና መከታ ከፈጣሪ በመሆኑ በአካል ባንተያይ በመንፈስና በአላም አንድ በመሆናችን በጸሎት አምላክ ይርዳህ እያልኩ እማለዳለሁ:;
  ጥቂት ላልተረዳቸው ይረዳቸው ዘንድ ራሳቸውን እንድፈትሹ ቢያደርጋቸው ይህችን አጭር ግጥም ይድረሳቸው
  እኛን ላይጠቅም አተራምሰው
  ስበእናውን በገንዘብ ገዝተው
  ሲያሟሽቁት ወኔውን አሳስተው
  ሃሞት የለው የጊዘው ወንድ
  ለገንዘብ ብሎ የሚዋረድ
  ከሚስቱ ፊት ስድብ ዱላ
  ፍትህ አጥቶ የሚጉላላ
  ሌላው ቆሞ እንደ ጥንቸል
  ሆዱን ወዶ የሚለው ቸል
  ቤቱ ፈርሶ ከመሬት ተጥሏል
  የወገን ቢል ሰሚ ጠፍቷል
  ለቁር ለጸሃይ ለረሃብ ተጋልጧል
  ልጅ ከወላጁ በምንደኞች ተለይቷል
  አይ ግዜያችን መጥፎ ዘመን \
  በግለኝነት ተወግኖ የሚባዝን
  ድርጎ በልቶ የሚኩራራ
  ፍርሃት ለብሶ የሚጠብቅ ተራ
  አረ ይብቃህ 22 ዓመት መከራ
  እንድ ቀድሞው አያቶችህ በሃገርህ ኩራ