የሰንደቅ ጋዜጣ… “መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” የሚሉ እና ሌሎችም አገራዊ ዜናዎች

በአገር ቤት የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በዛሬው ህዳር 25/2006 እትም የሚከተሉትን ርዕሶች ይዞ ወጥቷል። ዝርዝር ዜናውን ለማንበብ ከርእሶቹ በመጨረሻ ላይ ያለውን ሊንክ ይጫኑ።

-“መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም”

-በአዲስ አበባ በሥጋ ውጤቶች ላይ ሊጣል የታሰበው ግብር እያወዛገበ ነው
• የሥጋን ዋጋ እንዳያንረው አስግቷል

-ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስምንት ሺ ሰራተኞችን ገምግሞ ስምንቱን አባረረ

-በመጥረቢያ የግድያ ሙከራ የፈፀመው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
– ተከሳሹ ተሰውሯል

-ሼህ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ቃል ገቡ
sendek news
-መነኩሴው በግብረሰዶም ወንጀል በእስራት ተቀጡ

– የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባልደረባ በፈፀመው ወንጀል ተቀጣ

– 89 በርሜል ሬንጅ ተጭበርብሯል

– የኢትዮ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ዛሬ ይመረቃል

-ፕሮፌሰር ዮሐንስ ክንፉ የአፍሪካ አመራር 2013 ተሸላሚ ሆኑ

-ሴት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ እንዲሰሩ የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ሁሉንም ዜና ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ!!

(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 9ኛ ዓመት ቁጥር 430 ረቡዕ ህዳር 25/2006 )

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to የሰንደቅ ጋዜጣ… “መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” የሚሉ እና ሌሎችም አገራዊ ዜናዎች

 1. zabesha

  December 4, 2013 at 1:59 PM

  we all know that if EPRDF says I don’t that mean it does :)to me this reaffirm that Ginbot7 clime is true.

 2. hagere

  December 4, 2013 at 4:18 PM

  Kinfu,

  You are happy now that Shimelis Kemal said for you what you wanted to say in your article. Happy marriage between you and the Weyanes. When are going to go to Ethiopia and join Dawit Kebede?

  Good Luck!

 3. hagere

  December 4, 2013 at 4:20 PM

  በነገራችን ላይ ኤልያስ ክፍሌ አብርሃ በላይና የአቡጊዳ ድህረ ገጽ አዘጋጆች ችግራችሁ ምንድነው? ከኢሳትና ከግንቦት 7 የሚመጡ ወይም እነሱን የሚመለከቱ ዜናዎችን ለምንድነው ሳንሱር የምታደርጉት? እንደተራ ወሬዎች ህወሃት የግንቦት 7ን መሪዎች የግድያ ዘመቻንና አሁን ደግሞ የወያኔን የ”እንደራደር” ጥያቄን ወደ ጎን ትታችሁ ስለ ሱማሌ ጠቅላይ ሚኒስቴር መዘገብ ምን ዓይነት አባዜ ነው? ባትስማሙበትና ባትወዱት እንኳ እንደጋዜጠኛ የሆነውን እንኳ ብትዘግቡ ምን አለበት? ቅናት ነው ወይስ ምንድነው? ተቀደምን ነው? ወይስ የውስጥ አርበኝነት ሥራ ነው? ኤልያስ ክፍሌ ትልቅ ኢጎ እንጂ የፖለቲካ ብስለት እንደሌለው አውቃለሁ:: ያው ኤልያስ አለመብሰሉን በአደባባይ በደንብ ስላረጋገጠ ብዙ ክርክር አያስፈልገውም:: ኢሳይያስ አፈወርቅን ሁለት ጊዜ የአመቱ ኮከብ ሰው ብሎ የመረጠ ሞኝ ተላላ ሰው ነው:: አሁን ዶክተር ፍስሃ እሸቴን ከአባረሩ በሗላ ከኤርትራ በረሃ አንድ የኤርትራ ሴት ይዞ ከፈረጠጠ ቦቅቧቃ ለዛ ቢስ ጋዜጠኛ ተብዬ ጋር በሽግግር ሬድዮ ላይ ባዶ ወሬ ሲወቁና ሲደልቁ የቀድሞ ፍቅረኛቸውን ሻቢያን እያወገዙ በወሬ ብቻ ጊዜአቸውንና ገንዘባቸውን እያባከኑ ይገኛሉ::

  የኢትዮሜዲያው አብርሃ በላይ እንኳን የራሱ አጀንዳ አለው:: አብርሃ የወያኔ ጠላት ቢሆንም ትግሬዎች ሥልጣን እንዲይዙ አበክሮ እንደሚታገል ምንም ጥርጥር የለውም:: ሻቢያ የሚታመን ድርጅት ባይሆንም ሻቢያን ሰብብ በማድረግ ለሁሉም ነገር መከራክሪያ የሚጠቀምበት ጆከሩ ነው:: በማንኛውም የፖለቲካ ትንተናው ላይ ሻቢያን አምጥቶ ቅርቅር ነው:: ቅጽል ስሙ “ሻቢያ ጆከሬ” ነው:: ለአብርሃ ከሻቢያ ጋር አብሮ ቡና የጠጣ ወይም የተነጋገረ ወይም ትንሽ ፍራንክ የተቀበለ ወይም ያበደረ ወይም የሻቢያ ሴት ያገባ ወይም የተወዳጀ ሁሉ ወዮለት:: ሽመልስ ከማልን ትንሽ አይመስልም አብርሃ ሻቢያን በሚመለከት? ምን መምሰል ብቻ ቁርጥ እንጂ::

  የአቡጊዳ ድህረ ገጽ አዘጋጆች ግን ዝም ብሎ የሞኝ ቅናት አለባቸው:: ለአቡጊዳ ዶክተር ብርሃኑ ያለበት ነገር ሁሉ ሃራም ነው:: በቃ የማሪያም ጠላት ማድረግ ነው :: ሁኔታውን አመዛዝኖ አብሮ የሚሰራበትን ነገር ከማጤንና ኢትዮጵያን ከማዳን ይልቅ የራሳቸውን ፍላጎትና ሃሳብ እያስቀደሙ በዲሞክራሲና ሃላፊነት በጎደለው የመብት ጥያቄን ሰበብ በማድረግ የውያኔን እድሜ እያራዘሙ ይገኛሉ:: በዚህ ከክንፉ አሰፋ ጋር ይመሳሰላሉ:: ክንፋ አሰፋ ለዳዊት ከበደ መድረክ እንደሰጠህ አውቃለሁ ለግንቦት 7 ከልክለህ ማለት ነው:: እንዲህ ያለ ፍቅር ካለህ ለምን አዲስ አበባ ሄደህ አብራችህ አትቆዝሙም?

  ለማንኛውም ክንፉም ሆነ ኤልያስም ሆነ አብርሃም ሆነ አቡጊዳ ከግንቦት7 ወይም ከኢሳት የሚመጡትን ሰበር ዜናዎች ዘገቡ አልዘገቡ ምንም ፋይዳ የለውም:: ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም ነው ነገሩ:: ለአገራቸው የሚሰዉ ጠንካራ የኢትዮጵያ ልጆች ግንቦት7 ውስጥም ሆነ ሌላ ድርጅት ውስጥ እስካሉ ድረስ ከጉግል አድሴንስ ቼክ እየጠበቁ ከማውራትና ከመንጫጫት በስተቀር ምንም ማድረግ የማይችሉ በኢጎ የተነፉ ግለሰቦች ቅንጣት ታህል በትግሉ ሂደት ላይ እንድምታ አይኖራቸውም:: በማውራት በመደንፋትና ጽሁፍ ሲለቀልቁ ቢዋል የትም አይደረስም:: በሻቢያ በግንቦት7 በዶክተር ብርሃኑና በሌላም እያሳበቡ ፍርሃትን መደበቅና ከመስዋእትነት መሸሽ አሳፋሪ ነው:: እነዚህ ሁሉ የፈሪዎች ዘዴዎች ናቸው:: የናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ ነገሩ:: ከፈሪ ጎራ እራሳችሁን አውጡ:: ብእር ወይም የኮምፕዩተር ቦርድን ትንሽ ለቀቅ አርጉና መሳሪያ መጨበጥ ተላማመዱ:: ህወሃት መሳሪያ ጨብጦ ነው ባርያ ያደረገን:: ለትግሉ እንቅፋት እየሆናችሁ ለህወያት መሳሪያ አትሁኑ::

 4. tokchaw

  December 4, 2013 at 10:43 PM

  Sendek wrote it based on shemeles kemal said.We knew Shemelis he is a liasr for the last 8 years He is the mouth of weyane.Do expect true thing from them.Dear EMF from whom do you expect from weyane or G7.I left message on your Owen article.l am not reapting it.Sendek can not refuse what weyane ordred him to do.He cannot write what Brehanu said because it is inside Ethiopia.

  example I

 5. andnet berhane

  December 5, 2013 at 12:51 PM

  ወያነ አሉባልተኛ መሆኑን አገር ያወቀው ጸሓይ የሞቀው በመሆኑ ብዙም የሚሰጡት መግለጫ የራሳቸውን ድክመት አቅም አጥነት መሸነፍን ለመቀበል የማይችሉ (pathology lie)መሆናቸው የዝንጀሮ የወይን ፍሬ ለመብላት ስትንጠራራ አይቷት ተተራርትሽ አልደርስ አልሽ ቢላት አይ ቄምሸው መራራ በመሆኑነው ስትል ዋሸች እንዲሁም የሽመልስ ከመአል የሰጠው ምላሽ የሱ ሳይሆን አዛዦቹ ይጎረሱትን ስለሚያናፋ ጊዜው እስኪ መጣ ይቀጥልበት እንዲህ ያሉ ዘጎች (አጉል ሰባዊነት)የተላበሱ በማስመሰል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው: ለመሆኑ እውነት ለድርደር አልጠየቅንም ሲሉ ሕዝቡን ለማሳመን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም ታድያ እውነተኞችና ሃገር ጠባቂዎች ቢሆኑ ኖሮ ሃገር አዋርደውና ወርደታቸው የስለላ መዋቅራቸው በሙሉቀን መስፍን ተልእኮ ሊፈጽሙት የሞከሩት ተልካሻ የግድያ ሙከራ አለን ብለው እሚሏቸው የደህንነት ባለስልጣኖች ይሁን ጋሻጃግሬዎቻቸው: በፍርሃአት ተውጠው ያለሙትን ግድያ መሳርያ ማቀበል ያቃታቸው የመንደር አውደልዳይ ሁላ ያሰቡት የሽብር ተግባር እጅ ከፍንጅ ተይዞ የቀረበውን በምስል በቃል የቀረበውን ለምን መግለጫ አልሰጡም እንዲሁም ደካማና ሃገር ማስተዳደር አለመቻላቸውንና በደላላነት ያሰማርቕቸው የንጹሃን ዜጎችን ከየገተሩና ከየሰፈሩ ስራ መንግስት ይሰጣል እያሉ ያላቸውን ንብረት በማሸጥ ወደአረብ አገር በዘመናዊ ባርነት በመሸጥ ከሚያገኙት በመበዝበዝ በስቃይና በመከራ መኖራቸው አንሶ በሳአኡዲ መንግስት እየተፈጸመ ያለው ኢሰባዊ ድርጊት ተባባሪ በመሆን ዘጎችን መታደግ ያልቻለ አሳፋሪ አቸባሪ መንግስት ምን እውነት ያወራል ተብሎ ይጠባቃል:: እንዲሁም በታሪካችን ከቀድሞው መሪዎቻችን አንድም ቀን ርእስቢሄሮቻችን ተደፍረውና ተዋርደው አያውቁም ነገርግን ኃይለማርያም ደሳለኝ አደርድሩኝ በማለት የክዌትን መንግስት በመጠየቅ የግብጹ ጊዚያዊ ፕረዘደንት ለመምጣት ስላልፈለገ ግማሽመንገድ እንገናኝ ምሎ መጠየቅ እንደ ሃገር መሪ እንዱሁም የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነት በጊዚያዊ የተቀመተ መንግስት ዝቅ ብሎ መታየት የሱን ክብር ብቻ ሳይሆን ሃገራችንን አዋርዷል: ይህንንስ ለመዘገብና እውነቱን ለማውጣት ሽመልስ ከማል ምን አልክ?
  ለመሆኑ የናንተ ማሾፍ ማን ይነካናል የምትሉት የታ ጠቃችሁት የጦር መሳርያ ሳይሆን የሕዝብ ኃይል መሆኑን በመዘንጋት ሕዝብ ድምጹን በውጭም በውስጥም እየመከራችሁ አልሰማ ካላችሁ የምትሰሙበትን መንገድና በትር የማይቀር መሆኑን ለናንተም ግልጽና ዋነኛ ስልታችሁ በመሆኑ ነገርግን ይህ ጭዋና ትእግስተኛ ኢትጵያዊና/ዊት የሃገሩን ጥቅምና ማንነት እድገትና መብት ነጻነትን የሕግ በላይነትን ለማስፈን ያለፈውን የርስ በርስ ጦርነት እልቂትና የሃብት መባከን በመረዳት በሰላማዊ ትግል በተረጴዛ ዙርያ ላለፉት ሁለት ዘመን ቢሞክርም በ እምቢተኝነት በትምክህት ሃገር አልባ ለማድረግ ያደረጋችሁት የጥፋት የእስራት የግድያ የስደት አንገሽግሾት በቃኝ ማለቱን በሰላማዊ መንገድ አድርስ ል ምርጫውንም ለናንት ሰጥቷል ስለዚህም የናንተን ፍላጎት ለማሟላት ግፊት በማድረጋችሁ የግድ የኃይል ሚዛን ስለሚጠይቅ እንግዲህ አማራጩን ወስደናል ምክንያቱም በሃገራችን በመርጫና በድርድር የተገኘ ስልታን የለም ለወደፊቱ ግን ከናንት በኅውላ በዲሞክራሳዊ መንገድ በሕዝብ ድምጽና ፍላጎች የተመሰረተ ሃገራዊ ህገ ሕዝብ የሚተዴርበት የሚቀርጽበት በእኩልነት የሚኖርበት ሀገር ለማድረግ ይህን የግፍ ዘመን ማብቃቱን እናንተም ለፍርድ እንድምትቀርቡ አትጠራተሩ ትግራይ መሸሻ እንድማትሆናችሁ ልብ በሉ::
  ውድቀት ለግፈኖችና ሃገር አስወጊዎች
  ድል ለኢትዮጵያ ሕዝቦች