የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ጉዳይ… (እያያ አረጋ ተባረረ)

(EMF) የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ለሁለት መከፈሉ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከዋናው የስፖርት ፌዴሬሽን የተለየው ቡድን፤ እነ እያያ አረጋን ጨምሮ… በሼኽ መሃመድ አላሙዲን እና በአቶ አብነት በመደገፍ የመላው ኢትዮጵያ ስፖርት በሚል አዲስ ማህበር አቋቁሞ ነበር። ይህ አዲስ የተቋቋመው ማህበር ነው፤ አዲስ ሹም ሽር ውስጥ በመግባት… እርስ በርስ መጣላት የጀመረው።

የነገሩ ዋና መነሻ የሆነው… ባለፈው አመት በዋሺንግተን ዲሲ ተደርጎ የነበረው ቀዝቃዛ ዝግጅት ነው። ብዙዎች እንደሚያስታውሱት በሼኽ አላሙዲን የሚረዳው ወገን ያዘጋጀው የስፖርት ፌስቲቫል ድምቀትን የተላበሰ አልነበረም። በሁኔታው አቶ አብነትም ሆኑ ሼኽ መሃመድ ደስተኛ አልነበሩም። ስለሆነም እንደአማራጭ የተወሰደው እነ እያያ አረጋን በአማካሪነት ወደጎን ገለል በማድረግ፤ ከጁላይ 2014 ጀምሮ ስራውን የሚሰሩ እንደነሱ አባባል “አዳዲስ ወጣቶች” ተተክተዋል። (አዲስ የተመደቡት አክሊሉ ግደይ፣ መሳይ አንበርብር፣ ቢንያም ረታ፣ ተሾመ ጅሩ፣ እስክንድር ኃይሌ እና ኤልያስ ድንበሩ ናቸው)

ይህ ለውጥ የተደረገው ለማህበሩ የተመደበው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በከንቱ በመባከኑ ነበር። ለዚህ እንደዋና ምክንያት የተጠቀሰው ደግሞ የነ እያያ አመራር በመሆኑ፤ እያያ እና አብረው የነበሩት የቀድሞ አመራሮች ወደጎን ተደርገው፤ በአዳዲስ ሰዎች ተተኩ። “የገንዘብ ኪሳራ እና ጥሩ ውጤት እንዳይመጣ የሆነው በነ እያያ ምክንያት ነው” የሚለው አባባል ለ እያያ አረጋ ደስ ያሰኘው አይመስልም። በመሆኑም ጥፋተኛ እሱ ለመሆኑን የሚያስረዱለትን፤ የማህበሩን የሂሳብ እና ሌሎች መረጃዎች በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ይሄዳል። ካረፈበት ሼራተን ሆቴል በመቆየት ሼኽ መሃመድን አላሙዲንን በማግኘት ጉዳዩን ለማብራራት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። (ሼኽ መሃመድ አላሙዲት አሉት የተባለውን እዚህ ላይ ለመጥቀስ አልፈለግንም) ነገር ግን እያያ አረጋ መረጃውን እንደያዘ፤ ሼኹም ሳያናግሩት ይቀራሉ። እኛ በመረጃ አልደገፍነውም እንጂ በወሬ ደረጃ፤ ካረፈበትም ሆቴል እንዲወጣ ተደረጓል ተብሏል።

ከዚህ ሁሉ መጉላላት በኋላ እያያ አረጋ ወደ አሜሪካ ተመለሰ። ወደ’ዚህ ሲመለስ የጠበቀው ደግሞ፤ የነአቶ አብነት ገብረመቀል ቡድን ነው። ይህ ቡድን ደግሞ የሚመራው በአቶ አብነት ወንድም ብስራት ገብረመስቀል ነበር። በዲሴምበር መጨረሻ 2013 ላይ… ይህ አካል በአዲስ መልክ ከተዋቀረው ስራ አስፈጻሚ ጋር በአስቸኳይ በመነጋገር እያያ አረጋ፣ መኮንን ደምሰው፣ ሳሙኤል ተክሌ፣ ወንደሰን አስራት፣ ዮሃንስ መዝገቡ፣ ፀጋዬ ልዑል፣ ከበደ ጌታነህ፣ ታምሩ አበበን ከማህበሩ ሙሉ ለሙሉ ያባረራቸው መሆኑን ገልጿል። ማህበሩ በመጪው ፌብሩዋሪ አጋማሽ ላይ ቺካጎ ከተማ ስብሰባ በማድረግ፤ ቀጣዩ ጨዋታ የት እንደሚደረግ ውሳኔ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 24, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to የሰሜን አሜሪካ ስፖርት ጉዳይ… (እያያ አረጋ ተባረረ)

  1. Tuffaa bekele.

    January 24, 2014 at 10:50 PM

    Kinfu Asefa .you are trying to confuse the public as usual by giving a wrong heading to to your article .the weyane and alaumudin fake sport federation is not the north America sport federation .you are purposely giving this heading to confuse Ethiopians.no body know except you the alamudin and weyane supported fake sport association as a federation .so please stop your under cover weyane jornalizem.Aesa one ye alamudin ashkeroch sebseb new.

  2. much

    January 26, 2014 at 6:16 AM

    አየ ጉድ አይይይይ እረ እንዴት ያለ ዘምን ላይ ነው የደረስነው እንደው ለከርስ መሙላት ሲባል ህሊናን እየሸጡ መኖር:: ድሮም የወያኔ ታክቲክ ነው አንድን ነገር ከሁለት ከከፈለ በሆላ የሱ መገልገያ የሚሆነውን ወዲያውኑ የሰዎች ለውጥ ማድረግ ነው ምክኔያቱም እናዛ አበቃ የተሰጣቸውን አላማ አስፈጽመዋል ማለት ፊዴሪሽኑን ከሁለት ከፍለዋል ካሁን በሆላ አይጠቅማዋቸውም ትንሽም ቢሆን የሃገር ስሜት ሊኖራቸው ይችላል ተብሎ ስለሚገመት ነው:: በቦታቸው የወያኔ ካድሪዎች ይተኩበታል:: እነዛ ፊዴሪሽኑ ከሁለት እንዲከፈል ያደረጉ ግለሰቦች አሁን የሚያጋጥማቸው ነገር ወይም ያተረፍት ቢኖር በኢትዮጵያውያን ጥላችን እና ንቀትን ሲሆን በወያኔ ደግሞ ጭራሽ እንደማሽን ወይም ነብስ ያለው መገልገያ እቃ ይቆጠራሉ:: እግዚኦ ማሃረነ ክርስቶስ ከዚህ ሁሉ ቅለት