የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የ‹‹እሪታ ቀን›› እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ

semayawi1በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሰነበቱትና ቀሪዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ሳምንታዊ የወጣቶች የውይይት ፕሮግራም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) የ‹‹እሪታ ቀን›› በሚል የጠራውን ሰልፍ በግንባር ቀደምነት በመቀላቀል ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል፡፡

ወጣቶቹ ሰልፉን እንደሚቀላቀሉ ያስታወቁት ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ውጤታማ እንዲሆን በምን መልኩ ልናግዝ እንችላለን?›› በሚል አጀንዳ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከውህደት በዘለለ በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በሌሎች የትግል ስልቶች መተባበርና አብሮ መስራት እደግፋለሁ የሚል አቋም እንደሚያራምድ በተለያዩ ሚዲያዎች መግለጹ የሚታወቅ ሲሆን ወጣቶቹ በሰላማዊ ሰልፉ የሚያደርጉት ተሳትፎ ፓርቲው ለትብብር ያለውን አቋም ያሳያል ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ለሰላማዊ ሰልፉ ድምቀት የሚያገለግሉ ሜጋ ፎኖች፣ ጥሩምባዎችና ሌሎችም ሰልፉን ለማድመቅ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ይዘው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 3, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የ‹‹እሪታ ቀን›› እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ

 1. Dagmawi

  May 3, 2014 at 11:36 PM

  Way to go SEMAYAWI, unite to win this game. Ethiopia is bigger than every agenda you guys have. Work on things you agree. People are counting on you.

 2. much

  May 4, 2014 at 2:51 AM

  በጣም አስደሳች ዜና ነው እስካሁንም ይሄ ነበር የሚሆነው እባካችሁ በሌሎች ስራዎችም በመተባበር ልዩነታችሁን አጥቡ ግሩም።

 3. andnet berhane

  May 4, 2014 at 9:17 AM

  የእሪታን ቀን ለመቀላቀል የወሰዳችሁት ውሳኔ እጅጉን እታለመውን የነጻነት ጎዳና እውን መሆኑን የሚያበራ የኢትጵያን ሕዝቦች የጋራ የለውጥ ፍላጎት ዝግጁነት የሚያሳይ በመሆኑ ይበል እያልን ወደ ሁልንተና አንድ ድርጀት ለመሆን ጥርጊ በመጥረግ የጠላትን አንጀት የሚአኮማትር በመሆኑ መልካም ጅምር፡ ነገርግን የምታደርጉትን እቅድ ለሕዝብ እንጂ ለጠላት ማስታወቅ እቅዳችሁን ለማደናቀፍ ወያኔ ኢሓዴግ)እለታዊ ተግባር አርጎ የያዘ ደካማ አገዛዝ ሁልግዜም ትልሙ ጥፋት እንጂ የቡዙሃንን ጥያቄ ማስተናገድ አይቻለውም፡ ለተነሳችሁበት አላማ አንድነትና ጽናት ስኬት ከናንተ ጋር ይሁን

 4. ትዝብት

  May 4, 2014 at 9:36 AM

  ይህ ነው ኢትዮጵያዊነት!! ብራቮ ወጣት ሰማያዊዎች!!
  እኛም የፈለግነው ዋና ዓላማ ያለው የፋሽስት ናዚ ርዝፈራዥ ኢትዮጵያን እየቀበሯትና ተረት ተረት አድርገው አፈራርሰውና ገነጣጥለው እንዳልነበረች ሊያደርጉዋት የፈለጉትን በርኸኞች አውርዶ ለመጣል ከሆነ; ለሰላማዊ ሰልፍ አስፈላጊ ከሆነ እስከ ትጥቅ ድረስ በአንድ ላይ መተባበር አስፈላጊ ነው ። ከዚያ ባሻገር የፓርቲን ስራ በየፓርቲው መስራት ይቻላል።
  እስራኤልን እንደምሳሌ ባነሳ:— ሁሉም በየፓርቲው ተደራጅቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊው ዘርፍና በኢኮኖሚውም ሆነ በሃገር ጉዳይ ላይ ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅና ንትርክ ማየትና መስማቱ የዕለት ከዕለት ውሎና አዳራችን ነው። ነገር ግን የሃገሪቱን ደህንነት የሚያሰጋና የሽብር ድርጊት ከሆነ ግን ግራ ቀኝ ክንፍ ሳይሉ አንድ ላይ ተመካክረው ጠላትን ያጠቃሉ። ለውጭ ዜና ማሰራጫዎችም ሁሉም ሲጠየቁ አንድ አይነት እውነተኛ መረጃ ይሰጣሉ እንጅ፣ የኔ ፓርቲ አይደለም አይሉም።
  ታዲያ ለአንድ ለኢትዮጵያ ሲባል፣ አንድ መሆኑ ዛሬ እውነተኛ የኢትዮጵያን ልጆች ጮቤ ስንረግጥ ወያኔ አንገቱን የደፋበት ቀን ነው። በርቱ!! መገነጣጠል ለማንም አይበጅም!!!!
  ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!!!!!!