የሰማያዊ ሰልፍ በኃይል ተበተነ፤ መድረክ ለፊታችን ዕሁድ ጠርቷል (ቪኦኤ)

የአዘጋጁ ማስታወሻ፡ ከሰልፉ ላይ ታግተው በእስር ላይ የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ትላንት ኅዳር 6/2006 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ላይ ተፈትተዋል። አብረዋቸው የታሰሩ በርካታ ሰላማዊ ሰልፈኞች ግን እስካሁን የት እንደደረሱ አልታወቀም።

የሰማያዊ ፓርቲ እና የመድረክ ምልክቶች
መለስካቸው አምሃ, እስክን ድር ፍሬው –  15.11.2013

አዲስ አበባ —

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ሣዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ “ተፈፅሟል፣ እየተፈፀመም ነው” ያለውን ግፍ በመቃወም ዕሁድ፤ ኅዳር 8/2006 ዓ. ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡

የሰልፍ ዕውቅና የሚሰጠው ክፍል ግን በቃል አሉታዊ መልስ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ፡፡

አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አቅራቢያ በተሰባሰቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ “ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እሥር ተፈፅሟል” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ድርጊቱን አውግዟል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል ሰልፉ “ሕገወጥ ነው” ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዘጋጆቹ “ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ አላገኙም” ሲሉ ለፈረንሣይ የዜና ወኪል የተናገሩት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሺመልስ ከማል ክሥ እንደሚመሠረትባቸው አመልክተዋል፡፡

የሰልፉ አዘጋጆች በኢትዮጵያዊያን መካከል “ፀረ-አረብ ስሜት እያነሣሱ ነበር – ያሉት ሚኒስትር ደኤታው – ሰልፉ ሕገወጥ በመሆኑ ፖሊስ አግባብ ያለው እርምጃ ወስዷል” ብለዋል፡፡

መለስካቸው አምሃና እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ያስተላለፏቸው ዘገባዎች አሉ፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.