የሰመጉ ይግባኝ በፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ሊታይ ነው

በቀድሞ አጠራር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ያለአግባብ የባንክ አካውንቴ ታግዶአል በማለት ከፍቶት የነበረው ክስ በፌደራል በከፍተኛ ፍ/ቤት ውድቅ በመደረጉ ለፌደራሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ይግባኝ ጠይቋል፡ ፡ ጉዳዩ “በይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም በማለት የተመለከተው ሠበር ችሎት ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም በማለት የተመለከተው ሠበር ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ብይን መስጠቱን” ከሰመጉ ያገኘነው መረጃ ይገልጻል፡፡
በዚሁ መሠረት በከፍተኛ ፍ/ቤት የተፈጠረውን የህግ ጥሰት በማንሳት በሰበር ችሎት ለመከራከር ሰመጉ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን” ገልጸዋል፡፡ ከሠመጉ ባገኘነው መረጃ መሠረት “የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)፣ በቀድሞ አጠራር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መንግስታዊ ያልሆነ፤ ከየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገነ ነፃ ድርጅት ነው፡፡ ጉባኤው የቆመው ለሕግ ልዕልና፤ ለዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች መከበር ነው፡፡ በቅርቡ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ሥራ እንቅስቃሴው በመድከሙ ጨርሶ ሥራውን ያቆመ የመሰላቸው በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተገንዘበናል፡፡ ሆኖም ለአላማው ፅኑ እምነት ባላቸው አባላቱ እና ጥቂት ሠራተኞቹ እየታገዘ አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ ለደጋፊዎቹ ሁሉ ለማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡
ቀደም ሲል ጉባኤው በአብዛኛው ድጋፍ ያገኝ የነበረው ከውጭ አገር ለጋሾች እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም አዋጅ 621/2001 በሰብአዊ መብቶች ማስከበር አኳያ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከአመታዊ ገቢያቸው ዘጠና በመቶ ማግኘት ያለባቸው ከአገር ውስጥ ምንጮች መሆን እንዳለበት በመደንገጉ ገቢው በእጅጉ ቀንሷል፡፡ ከአባላት ሊሰበሰብ የቻለው ገቢ አነስተኛ ከመሆኑም ሌላ ጉባኤው ለመቋቋሚያ ብሎ አሥራ ስምንት ዓመታት ሙሉ በማጠራቀም በባንክ ያስቀመጠው ገንዘብ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ኤጀንሲ ታግዶበት ለማስለቀቅ በክስ ላይ ይገኛል፡፡
`ሰመጉ` ላለፉት 20 ዓመታት በ12 ቅርንጫፎች እና ለሰብዓዊ መብት ዴሞክራሲ እና የህግ የበላይነት መስፈን ፅኑ ፍላጎት ባላቸው ሠራተኞቹ የሰብአዊ መብት ተጠቂዎች ለጉዳታቸው ድምፅ እንዲያገኙ እና አጥፊዎቹም እንዲታረሙ በሰፊው ተንቀሳቅሷል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አዋጅ እስከወጣበት ጊዜም `ሰመጉ` 58 ሠራተመፐች 3 የሥራ ሂደቶች እና 8 ንዑስ የሥራ ሂደቶች የነበሩት ሲሆን በ2001 ብቻ በ16 የሰብአዊ መብት ጥሰት መርማሪዎች እና በ12 ቅርንጫፎቹ በመንቀሳቀስ 1723 የሰብአዊ መብት ምርመራዎችን አድርጓል፤ 3 መደበኛ ሪፖርቶችን እና 6 ልዩ መግለጫዎችን አሳትሟል፡፡
አዋጅ 621/2001 ከወጣ ጊዜ ጀምሮም በተከተለው አሉታዊ ተጽዕኖ ምክንያት አቅሙ በመዳከሙ ዘጠኝ ቅርንጫፎቹን ለመዝጋት የተገደደ ሲሆን 85% ሠራተኞቹንም አጥቷል፡፡ ይህም `ሰመጉ`በመላው ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተጎጂዎችን ጩኽት በማሰማት እና ከጎናቸው በመቆም ሲያደርግ የነበረውን የማይተካ ሚና ያስተጓጎለበት ከመሆኑም በተጨማሪ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግሥት ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ ማህበር የማደራጀት መብት አለው የሚለው ድንጋጌ ከማጠናከር ይልቅ ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፁን ከማጠናከር ይልቅ ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው፡ ፡ በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፁን ሲያሰማበት የነበረውን `ሰመጉ`ን በማዳከም ዋናው የህጉ ተጎጅ `ሰመጉ` ሳይሆን ሲያገለግለው እና ድምፁን ሲያሰማለት የነበረው ህዝቡ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ሁኔታ ከፍተኛ ጫና ያሣደረብን ቢሆንም ሰመጉ በሰብአዊ መብት፣ ዲሞክራሲ እና በህግ የበላይነት ፅኑ እምነት ባላቸው ኢትዮጵያውያን በመታገዝ ሥራዎቹን ቀጥሏል ለወደፊትም ይቀጥላል፡፡ አሁንም ባሉት ሠራተኞ በመታገዝ 5 ልዩ መግለጫዎችን እና 1 መደበኛ ሪፖርት አውጥቷል፡፡
ጉባኤያችን እስካአሁን ሲታገል የቆየው ለህዝብ መብቶች መከበር እንደመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊደግፉት ይገባል የሚል እምነት አለን ስለሆነም ገቢ ለመሰብሰብ በምናደርገው ጥረት ሁሉ ተካፋይ እንድትሆኑ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡” ብለዋል፡፡
ምንጭ – ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 9, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.