የርዕዮት አለሙ ጉዳይ ዛሬ ይታያል

EMF – ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ሃሳቧን በነጻ ስለገለጸች፤ “አሸባሪ” ተብላ በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ መሆኗ ይታወቃል። ሆኖም የተፈረደባት ፍርድም ሆነ የፍርድ ሂደቱ ትክክል አልነበረም በሚል ጉዳይዋ በሰበር ችሎት እንዲታይ ዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶ ነበር። የርእዮት አለሙ ቤተሰብ ጠበቃ እና ደጋፊዎች ከጠዋት ጀምሮ ፍርድ ቤት ናቸው። ሆኖም ዳኞቹ ለምሳ በመውጣታቸው ምክንያት እስካሁን ጉዳይዋ አልታየም። እሷም ከጠዋት ጀምሮ በእስረኛ መኪና ውስጥ እየተጠበቀች ናት። እኛም ሂደቱን ከስፍራው እየተከታተልን እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 11, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.